ኬንያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች

የፎቶው ባለመብት, SOPA Images
ኬንያ የመጀመሪያውን በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች። የኬንያው ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታይ ካግዌ እንደገለፁት በኮሮና ቫይረስ መያዟ የተረጋገጠው ሴት ከሳምንት በፊት ከአሜሪካ ወደ ኬንያ የመጣች ነች።
ግለሰቧ ከአሜሪካ ወደ ኬንያ የመጡት በለንደን አድርገው ሲሆን መጀመሪያ ኬንያ ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ ምርመራ ተደርጎላቸው ነበር።
ሚኒስትሩ እንደገለፁት በወቅቱ የተገኘባቸው ነገር ያልነበረ ቢሆንም አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በሚገኝ የለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ተደርጎ ከቀናት በኋላ በትናንትናው እለት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
ሚኒስትሩ እንዳሉት ህመምተኛዋ ያሉበት ሁኔታ ደህና የሚባል ሲሆን ምግብም ይበላሉ፤ ትኩሳታቸውም እየወረደ ነው ብለዋል።
በሽተኛዋ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በኬንያ ብሄራዊ የኢንፈሉዬንዛ ላብራቶሪ እስኪረጋገጥ ድረስም በለይቶ ማከሚያው ተገልለው እንደሚቆዩ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
የኬንያ መንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት ሲሪስ ኦጉና በትናንትናው ዕለት እንዳስታወቁት የመንግሥት ሰራተኞች ወደ ውጭ አገራት ጉዞ እንዳያደርጉ እገዳ ተላልፏል።
ሚስተር ኦጉና አክለውም ቫይረሱ ከተገኘባቸው አገራት ሚመጡ ኬነንያውያን ራሳቸውን ለተወሰነ ጊዜ ከማንኛውም ንክኪ አግልለው እንዲቀመጡ መክረዋል።












