ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በቻይና ባለመስታወት ድልደይ ላይ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ ካጋጠመው አደጋ ተንጠልጥሎ ተረፈ
በቻይና ባለመስታወት ድልደይ ላይ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ ካጋጠመው አደጋ ተንጠልጥሎ ተረፈ
የመስታወት መርግጫ ያለውና በቻይና የሚገኘው ድልድይ ላይ እየተጓዘ ነበረ - ግለሰቡ። ሆኖም በጉዞው መካከል በተፈጠረ ሀይለኛ ንፍስ መስታወቶቹ መርገፍ ጀመሩ። ይሄኔ መርገጫ ያጣው ግለሰቡ የድልድዩን ሌላ አካል የሙጥኝ ብሎ በመንጠልጠል ነው የተረፈው።
100 ሜትር ከፍታ ባለውና በቻይና ሰሜን ምስራቅ የሚገኘውን ፒያን ተራራን መሰረት አድርጎ የተገነባው የመስታወት ድልድይ ላይ የተፈጠረው ክስተት የገጠመው ባለፈው አርብ ነበር።
ታዲያ በተከሰተው ንፋስ የድልድዩ ልዩ መገለጫ የሆኑትን የመስታወት ወለሎች በሰዓት 150 ኪሎ ሜትር በሚገመት ፍጥነት በታትኗቸዋል።
ቻይና 2300 የሚጠጉ የመስታወት ወለሎች ያሏቸው ድልድዮች እንዳሏት ይታመናል። ድልድዮቹ በቻይና እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ይበልጥ ለማስፋፋት ያለሙ ናቸው።
በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት የተጋራ አንድ ምስል አንድ ጎብኚ ወለሉ የረገፈ በባለመስታወት ድልድይ ላይ ትንጠልጥሎ ይታያል።
የአደጋ መከላከል ሰራተኞች ድልደዩ ላይ የነበረውን ቱሪስት ለማዳን ደርሰው እያየረዱት ራሱን መትረፉ መቻሉን ተገልጾል።
ሰውዬው ለማንኛውም በሚል ወደ ሆስፒታል የተወሰድ ሲሆን አሁን "አካሉም ስነልቦናውም ተረጋግቷል" ተብሏል።
አደጋ የደረሰበት አካባቢ ዝግ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተሰምቷል።
በቻይና እንዲህ አይነት አደጋ ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 ሄቢ የተሰኘችው የቻይና ግዛት የድህንነት ፍተሻዎችን በማድረግ መረማመጃዎችን ጨምሮ ከመስታወት የተሰሩ የቱሪስት መስህቦችን ዘግታ ነበር።
በሌላ የሀገሪቱ ክፍል በ2019 በመስታወት በተሰራ የቱሪስት መስህብ ላይ የተፈጠረው አደጋ አንድ ሰው ሲሞት ስድስት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በ2019 በመስታወት ድልድይ ላይ በደረሰ አደጋ አንድ ቱሪስት ተጎድቷል።