እግር ኳስ፡ 2021 ታላቅ የእግር ኳስ ዓመት ሊሆን የሚችልበት አምስት ምክንያቶች

የጎርጎሮሳዊያኑ 2020 ብዙ ውጣ ውረድ ነበረበት። 2021 የበለጠ አዎንታዊ ተስፋ እንደሚሰጥ እናምናለን፡፡

በጉጉት የምንጠብቃቸው አምስት ነገሮች እነሆ ...

የደጋፊዎች መመለስ

ከጓደኛዎ ጋር ወደ ሜዳዎች መሄድ እና በተጨናነቁ ስታዲየሞች መሆን በአሁኑ ጊዜ ሩቅ ይመስል ይሆናል፡፡

ሆኖም የኮሮናቫይረስ ክትባት በሚቀጥሉት ወሮች ውስጥ ወደ ስታዲየሞች መመለስን ብሩህ አድርጓል።

እኤአ ከታህሳስ 2 2021ወዲህ ውስን ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ሜዳ ተመልሰው እግር ኳስን ለመመልከት መቻላቸው ዕድለኛ አድረጓቸዋል፡፡

ከረቡዕ ጀምሮ ግን የኮቪድ-19 ገደቦችን ድጋሚ መታወጁን ተከትሎ ሁሉም ጨዋታዎች በዝግ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

ክትባቶች በመላ እንግሊዝ መሰጠት የጀመሩ ሲሆን የጤና ሚንስትሩ ማት ሀንኮክ የፕሮግራሙ ቅልጥፍና የሚወሰነው ክትባቶቹን በሚመረቱበት ፍጥነት ነው ብለዋል፡፡

ይህ ሂደት ሲሆን ብቻ ነው ለእግር ኳስ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ስለመመለስ ማውራት የሚቻለው። ነገር ግን 2021 ደጋፊዎች ከትኬቶቻቸው ላይ አቧራ በማራገፍ የሚወዱትን ቡድን በአካል ይመለከቱ ይሆናል።

የበለጠ ክፍት የሆነው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር?

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሰኔ ወር ሲጀመር ማን ያሸንፋል ጉዳይ ብዙም የሚያስደስት ነገር አልነበረም፡፡

ሊቨርፑል አናት ላይ በ25 ነጥቦች በልጦ ተቀምጦ በ 30 ዓመት የመጀመሪያውን የሊግ ሻምፒዮና ያማሸነፋቸው ጉዳይ ኢምንት ነው፡፡

2020 መጀመሪያ ላይ እንኳን ቀዮቹ አንድ ጨዋታ እየቀራቸው ሁለተኛ ከነበረው ሌስተር ሲቲ በ 13 ነጥቦች ርቀው ነበር፡፡

ከአሥራ ሁለት ወራት በኋላ ነገሮች በጣም የተጠናከሩ ሆነዋል፡፡ አሁንም አሸናፊ በሚመስለው ሊቨርፑልን እና 9ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ሳውዝሃምፕተን የሚለያዩት በሰባት ነጥቦችን ብቻ ነው፡፡

ቀዮቹ ልክ እንደ ባለፈው ዓመት አይደሉም። ባለፈው የውድድር አመት ከ16 ጨዋታዎች በኋላ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር አቻ ተለያይተው አንድ ጊዜ ብቻ ነጥብ ጥለው ነበር።

በዚህ የውድድር ዘመን ከተመሳሳይ ጨዋታዎች በኋላ የየርገን ክሎፕ ቡድን በሰባት ጨዋታዎች ነጥብ ጥለዋል-ስድስት አቻ ሲወጡ አንድ ጊዜ ደግሞ ሽንፈት ቀምሰዋል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት ማንችስተር ሲቲ በ 2017-18 ከነበረው የ 100 ነጥብ ድል በቀረበ 98 ነጥብ በማግኘት ሻምፒዮን መሆን ችሏል፡፡

"ሊቨርፑል እና ሲት እንደዚህ ቀደሙ አይደሉም። ይህም አጓጊ አድርጎታል" ሲል የቀድሞው የእንግሊዝ ተከላካይ ጋሪ ኔቪል ገልጾ ነበር።

"ወቅቱ እንዲህ እያደረገን ነው፡፡ ሁለቱ ከዚህ በፊት አይቼው የማላውቀውን መስፈርት አስቀምጠዋል። አሁን ግን የተለመደ ነገር እያየን ነው" ብሏል።

በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት አነስተኛ እረፍት ስለሚኖር የታጨቀው የደረጃ ልዩነት ሊቀጥል ይችላል፡፡

አዲስ ምዕራፍ በስኮትላንድ?

ሴልቲክ በስኮትላንድ እግር ኳስ ላይ የበላይነት ማማ ላይ መቆም ለአንዳንዶች በአዎንታዊ አይታይም- የተቀረው የአገሪቱ ክፍል ግን እንደዚያ ሊያስብ ይችላል።

ሴልቲክ ያለፉትን 12 የአገር ውስጥ ዋንጫዎችን በሙሉ በማሸነፍ ለአራት ዓመታት የስኮትላንድ እግር ኳስን በብቸኝነት ተቆጣጥሯል፡፡

የዘንድሮው የስኮትላንድ ፕሪሚየርሺፕ ለሚተነበይ ግን የተለየ ውጤት የሚኖር ይመስላል።

በቀድሞው የእንግሊዝ አማካይ ስቲቨን ጄራርድ የሚመራው ሬንጀርስ በግላስጎው ተፎካካሪዎቹን በ 16 ነጥብ ልዩነት ይመራል።

እሁድ ሬንጀርሶች ካሸነፉ ለ10ኛ ተከታታይ ዓመት የሊጉን ዋንጫ አንዳያሸንፉ እንቅፋት ይሆናሉ፡፡

ከተሸነፉ ግን ሦስት ጨዋታ ለሚቀራቸው የኒል ሌነን ልጆች ተስፋ የሚሰጥ ይሆናል።

በተከታታይ 10 ዋንጫ ማሸነፍ በብሉይ የማይደረስ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ዘንድሮ ፌሽታ በግላስጎው ብቻ የሚካሄድ አይደለም፡፡ ሂበርኒያን፣ ሊቪንግስተን፣ ሴንት ጆንስተን እና ሴንት ሚረን የስኮትላንድ የሊግ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ስለደረሱ ለዋንጫው ይፎካከራሉ፡፡

በዩሮ 2020 ያሉት ስት የብሪታኒያ ተስፋዎች

ለሌላ ጊዜ በተላለፈው ዩሮ 2020 ደጋፊዎች ወደ ሜዳ መመለሳቸው ወደፊት ይታያል። ይህ ግን የሚወሰነው በኮሮናቫይረስ ክትባቶች ስኬት እና ፍጥነት ላይ ሊሆን ይችላል፡፡

ሻምፒዮናው ሰኔ 11 ቀን የሚጀመር ሲሆን በ12 የአውሮፓ ከተሞች ይካሄዳል፡፡

ዩኤፋ ውድድሩን በሙሉ ደጋፊ፣ በከፊል ወይም በዝግ ስለማካሄዱ ለመወሰን በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ይሰበሰባል፡፡

"አሁን ባለው መልኩ መጫወት መቻሉን ማረጋገጥ አንችልም። ነገር ግን ውድድሩ ይካሄዳል። እኛም የሚያስደስት ነገር እናገኛለን" ሲል የቀድሞው የእንግሊዝ ግብ ጠባቂ ሮብ ግሪን ለቢቢሲ ራዲዮ 5 ተናግሯል።

ያም ሆነ ይህ ውድድሩ እንግሊዝ፣ ስኮትላንድ እና ዌልስን ስላሳተፈ በብሪታንያ ጠንካራ ፍላጎት ይስባል፡፡ እነዚህ ሶስት ሃገራት ለውድድሩ የበቁት ከ1958ቱ የዓለም ዋንጫ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

"እንደ ህብረተሰብ እንደዚህ አይነት ነገር እንፈልጋለን" ብሏል።

የስኮትላንድ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከ1998ቱ የዓለም ዋንጫ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በትልቅ ውድድር የሚሳተፈው፡፡

የቀድሞው የስኮትላንድ ተጫዋች ፓት ኔቪን "የስኮትላንድ ደጋፊ መሆን አስቸጋሪ የሆኑባቸው 22 ዓመታትን አሳልፈናል" ብሏል፡፡

"በስታዲየሞችም ይሁን በቴሌቪዥን፣ ምንም ይሁን ምን እኛ በጉጉት እየተጠባበቅነው ነው" ሲልም አክሏል።

እንግሊዝም የ55 ዓመታት የዋንጫ ጥሟን የምታረካበት ዕድል ያለ ይመስላል ፡፡

አዲስ ምዕራፍ ለእንግሊዝ እና ለስኮትላንድ ሴቶች

ከወንዶቹ ወገን አንዳቸውም ዋንጫ ማሸነፍ ካልቻሉ በሴቶቹ ሊሳካ ይችላል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት ለታላቋ ብሪታንያ በኦሎምፒክ ወርቅ መልክ ሊመጣ የሚችልበት ተስፋ አለ፡፡ ካልሆነ ግን እንግሊዝ እና ስኮትላንድ በተለያዩ አሰልጣኞች በተናጠል እየተዘጋጁ ናቸው፡፡

ባለፉት ሶስት ታላላቅ ውድድሮች የእንግሊዝ ሴቶች እስከ ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ ሆነዋል፡፡ የኔዘርላንድ አሰልጣኝ ሳሪና ዊግማን ሥራቸውን ሲረከቡ አዲስ ምዕራፍ ይመጣል፡፡

ዊግማን ኔዘርላንዶችን በዩሮ 2017 ለዋንጫ አብቅተዋል። ለ2019 የሴቶች የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ሲደርሱ ያንን የሚያሻሽሉበት መልካም አጋጣሚ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

በአሜሪካ የ 2 ለ 0 ሽንፈት ቢገጥማቸውም ዊግማን "የተረጋገጠላቸው አሸናፊ" የሚለው ዝናቸው የቀጠለ ሲሆን፣ ለእንግሊዝም ስኬት ማምጣት እንደሚችሉ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡

የቀድሞዋ የእንግሊዝ አማካይ ኬቲ ቻፕማን "እንዴት አሸናፊ መሆን እንደምትችል ታውቃለች" ስትል ገልጻቸዋለች።

"ሁልጊዜም ለማየት የሚመረጡ ቡድኖች አሏት፡፡ መንፈስን የሚያድስ ሲሆን ሥራዋን በማየቴ በጣም ተደስቻለሁ" ብላለች።

በሌላ በኩል ስኮትላንዶች በታሪካቸው እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የአሰልጣኝነት ሹመት ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡

የሼሊሊ ኬር በታህሳስ ከቡድኑ መለያየት አዲስ ምዕራፍን የፈጠረ ነው። ከአውሮፓ ሻምፒዮና ተሳትፎ በኋላ ለመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ብቁ እንዲሆኑ ያደረጉ አሰልጣኝ ናቸው፡፡