አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች

ዴቪዶ፣ ዊዝኪድ፣ በርና ቦይ ከአፍሪካ ማህፀን የተገኙ ሙዚቀኞች ሲሆኑ፤ ድንበር፣ ቋንቋ ፣ ባህል ሳይገድባቸው በአለም አቀፉ የሙዚቃ መድረክም ስመ ጥር ሊሆኑ ችለዋል።
ለዚያም ነው ምዕራባውያኖቹ መዚቀኞችም ሆነ ፕሮዲውሰሮች አይናቸውን ወደ አፍሪካ ሙዚቀኞች እያማተሩ ያሉት።
በዚህ አመት በወጣው 'ላየን ኪንግ' የካርቱን ፊልም ተነሳስታ ቢዮንሴ አልበሟን ስትሰራም ታዋቂ አፍሪካዊ ሙዚቀኞችን አካታለች።
ሚስተር ኢዚና በርና ቦይም በሙዚቃው ዓለም ከፍተኛ ስፍራ በተቸረው በአመታዊው የኮቼላ ሙዚቃ ፌስቲቫል ተሳትፈዋል።
ሊጠናቀቅ አንድ ወር በቀረው የአውሮፓውያኑ ዓመት የአድማጮችን ቀልብ መያዝ ከቻሉት ጥቂት አፍሪካውያን ሙዚቀኞች አምስቱ እነሆ፡
ሺባህ ካሩንጊ (ኡጋንዳ)

በእናት ሃገሯ ኡጋንዳ በሙዚቃው ዘርፍ ተደማጭነት ያገኘችው ሺባህ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሃገሯን አልፎ ሙዚቃዋ ወደሌሎች ሃገራት ደርሷል።
በሚስረቀረቅ ድምጿ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለችው ሺባህ ከተለያዩ አርቲስቶችም ጋር በመጣመር ትስራለች።
ሙዚቃውን ከዳንስና ከፋሽን ጋር በማጣመር ለራሷም ሆነ ለሃገሯ ስም ማትረፍ ችላለች።
በመድረክም ላይ ባላት ድንቅ ችሎታ እንዲሁ ታዳሚውን ወደ ሙዚቃዋ ጠልቃ የምታስገባበበት መንገድ ብዙዎችን እንዲደመሙ አድርጓቸዋል።
ይህ ጽሑፍ በGoogle YouTube. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የGoogle YouTube ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ YouTube ይዘት መጨረሻ, 1
ጆቦይ (ናይጀሪያ)

ናይጀሪያዊው ጆቦይ 'ቤቢ' በሚለው የፍቅር ዘፈኑ የብዙ አድማጮችን ጆሮ ማግኘት የቻለ ሲሆን፤ ይህ ሙዚቃውም በዩቲዩብ ላይ አስራ አምስት ሚሊዮን ተመልካቾችን ማግኘት ችሏል።
በስሜት በተሞላ አዘፋፈኑና በሚንቆረቆረው ድምፁ የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን ማጣመር የቻለ አርቲስት ነው። አፍሮ ቢትንና ፖፕን በማጣመር የሰራው ሌላኛው ዘፈኑ 'ቢጊኒንግ' ከፍተኛ ተቀባይነትን ማትረፍ ችሏል።
በነዚህ ነጠላ ዘፈኖቹ እውቅናን ማትረፍ የቻለው ጆቦይ በተለያዩ ሃገራትም በሚገኙ ፌስቲቫሎች ላይ ከሚጋበዙ ሙዚቀኞች አንዱ መሆን ችሏል።
ይህ ጽሑፍ በGoogle YouTube. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የGoogle YouTube ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ YouTube ይዘት መጨረሻ, 2
ብሪያን ናድራ (ኬንያ)
ከሁለት ዓመታት በፊት ባወጣው ነጠላ ዘፈን 'ሊዮ' የሙዚቃው ዓለም ላይ ስሙን የጣለው ብሪያን ሙዚቃውን "ከሚሊኒየሙ ባህል የተገኘ፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ ዘመንን ያማከለ፤ የከተማ ድምፅ" በማለት ይገልፀዋል።
ኬንያዊው ሙዚቀኛ፣ ገጣሚና የሙዚቃ ፀሐፊ የምስራቅ አፍሪካ የፖፕ ሙዚቃ ስልት አምባሳደር እየተባለ እየተጠራ ሲሆን፤ በዓለም አቀፉ ደረጃ ኬንያ የሙዚቃውን ገበያ ሰብሮ መግባት የቻለ ሙዚቀኛ የሌላት ሲሆን ብሪያን ይህንንም ሊቀይር ይችላል እየተባለ ነው።
ለየት ያለ የአዘፋፈን ዘዬ ያለው ብሪያን ለስለስ ካሉ ዘፈኖቹ በተጨማሪ ራፕ ማድረግን እንዲሁም የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን እንደ ሬጌና ሌሎችም ሙዚቃ ስልቶችን ማጣመር ችሏል።
ይህ ጽሑፍ በGoogle YouTube. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የGoogle YouTube ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ YouTube ይዘት መጨረሻ, 3
ኢኖስ ቢ (ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ)
መነሻውን የኮንጎ ባህላዊ ሙዚቃ ያደረገው የ22 አመቱ ኢኖስ ሌሎች የሙዚቃ ስልቶችን በመጨመር ሙዚቃውን አንድ ደረጃ ወደፊት ሊያራምድ ይችላል እየተባለ ነው።
ከታንዛንያው ሙዚቀኛ ዳይመንድ ጋር የተጣመረበት 'ዮፔ' የተባለው ነጠላ ዘፈኑም ብዙዎችን አስደስቷል። የሙዚቃ ቪዲዮው በወጣበት በሶስት ወራትም አስራ አራት ሚሊዮን ተመልካቾች አይተውታል።
ኢኖስ ቢ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መለያ የሆነውን ሩምባ የሙዚቃ ስልትንም ከሪትም ኤንድ ብሉዝና አፍሮ ቢትስ ጋር ማቀላቀል ችሏል።
ይህ ጽሑፍ በGoogle YouTube. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የGoogle YouTube ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ YouTube ይዘት መጨረሻ, 4
ሾ ማድጆዚ (ደቡብ አፍሪካ)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በአለም የሙዚቃ መድረክ ዝናዋ እየናኘ ያለው ደቡብ አፍሪካዊቷ የሂፕ ሆፕ አርቲስት ሾ በዚህ ዓመት የቢኢቲ (ብላክ ኢንተርቴይንመንት) አዲስ ዓለም አቀፍ አርቲስት በሚል ዘርፍ ሽልማትን ማግኘት ችላለች።
በታላቅ ስሜት የምትዘፍነው አርቲስቷ መድረክ ላይ ሲሆን ያ ስሜቷ በሰው ላይ ይሰርፃል ይሏታል።
የደቡብ አፍሪካ ግኮም የሙዚቃ ስልት በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበረ ቢሆንም ሾ ግን ራፕ ታደርግበታለች፤ በአንድ ሳይሆን በተለያዩ ቋንቋዎች።
ምንም እንኳን ብዙዎቹ የደቡብ አፍሪካ አርቲስቶች የሙዚቃ ገበያ ትኩረት ሃገራቸው ላይ ቢሆንም ሾ ግን የአለም አቀፉን ገበያ እያማተረች ነው።