ፑቲን ለ70ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው ትራክተር ተበረከተላቸው

የፎቶው ባለመብት, PRESIDENT OF REPUBLIC OF BELARUS
70ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን እያከበሩ የሚገኙት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ብዙም ያልተለመደ ነው የተባለ ስጦታ ከቤላሩሲያው አቻቸው ተበርክቶላቸዋል።
የቤላሩሱ ፕሬዝዳንት እና የፑቲን አጋር የሆኑት አሌክስአንደር ሉካሼንኮ በአገራቸው የተመረተ ትራክተር ነው ለልደታቸው የተሰጣቸው።
ሉካሼንኮ ይህ ስጦታውን ስለማበርከታቸው በፑቲን የትውልድ ስፍራ ሴንት ፒተርስበርግ ለምክክር ባቀኑበት ወቅት አረጋግጠዋል።
ዩክሬንን በመውረር የቀሰቀሱት ጦርነት እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት ፕሬዝዳንት ፑቲን በትውልድ ከተማቸው ውስጥ ከቤላሩሱ ፕሬዝዳንት በተጨማሪ ሌሎች የቀድሞ ሶቪየት ኅብረት አካል የነበሩ አገራት መሪዎችን አስተናግደዋል።
ከዩክሬን ጦር በኩል ከባድ መልሶ ማጥቃት እየገጠማቸው ያለው ፑቲን፣ በዚህ ሳምንት “አስጨናቂ” ሲሉ ከገለጹት ከዩክሬን ከጠቀለለሏቸው ግዛት ጋር በተያያዘ ስለገጠሟቸው ችግር ፍንጭ ሰጥተዋል።
ሆኖም ትላንት አርብ የቤላሩሱ አጋራቸው በጠቅላይ ሚኒስትርነት እና በፕሬዝዳንትነት ለሁለት አስርት ዓመታት በሥልጣን ላይ ለቆዩት ፑቲን ውዳሴና ስጦታን አቅርበዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ በ1994 ሥልጣን የያዙት የአውሮፓ “የመጨረሻ አምባገነን” እየተባሉ የሚጠሩት እና አስተዳደራቸው በምዕራባውያን ማዕቀብ ስር የሚገኘው ሉካሼንኮ በአገራቸው የተመረተ ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ ለፑቲን ማበርከታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ይዘው ተገኝተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ይህ ለፑቲን በስጦታ የተበረከትረ ‘ሚኒስክ’ የተኘው የቤላሩስ ትራክተር በአገሪቱ ኢንደስትሪ ውስጥ እንደ ብሔራዊ ኩራት የሚታይ ነው።
ፑቲን ይህንን ስጦታ ጨምሮ ከታጃኪስታኑ ፕሬዝዳንት ኢሞማሊ ራህሞን በስጦታ የቀረቡላቸውን ትላልቅ ሃባቦችን በተመለከተ የሰጡት ምላሽ የለም።
ከተወሰነ ዓመታት ወዲህ ፑቲን ትራክተሮች ሲያሽከረክሩ በተደጋጋሚ እየታዩ ነው።
በተጨማሪም ፑቲን ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክ ኪሪል “የሩሲያን ገጽታ ስለቀየሩ፣ ሉአላዊነቷን ስላጠናከሩ እና የመከላከል አቅሟን ስላሳደጉ እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅሟን ስለጠበቁ” በሚል ውዳሴ ቀርቧላቸዋል።
በሩሲያ የሚደገፉት የቼቺኒያው መሪ ራምዛን ካዲሮቭ ደግሞ ፑቲንን “በዓለም ላይ ቁጥር አንዱ አገር ወዳድ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
በሌላ በኩል የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት በላኩት መልዕክት “ከአሜሪካ የተሰነዘሩ ስጋቶችን እና ፈተናዎችን ስላሸነፍ” እንኳ ደስ አለዎት ብለዋል።
የፑቲን ተጻራሪዎች ደግሞ የልደት በዓላቸውን የራሳቸው አገር እየገነበቡ የሌሎችን የሚያፈርሱ የጦር ወንጀለኛ እንደሆኑ ዳግም ለመግለጽ ተጠቅመውበታል።
የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ኦልስኪ ሬዝኮሊቭ የሩሲያ ወታደሮች የፕሬዝዳንቱን ጥሪ ውድቅ እንዲያደርጉ እና ከዩከሬን ጋር መዋጋት እንዲያቆሙ የጠየቁ ሲሆን፣ ፑቲን ከወታደሮቻቸው ጋር “ከመቆም ይልቅ ምሽግ ውስጥ ተደብቋል” ብለዋል።
አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የቤላሩሱን ፕሬዝዳንት የትራክተር ስጦታ በምጸት ተመልከተው፣ የወደሙ የጦር ተሽከርካሪዎችን ሲጎትቱ ለታዩት የዩክሬን አርሶ አደሮችን እንቢ ባይነት ለማሳየት ምልክት ተርጓል።
በቼክ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ፕራግ ውስጥ ተቃዋሚዎች በፑቲን ላይ የሚሳለቅ ምስል ይዘው በአደባባይ ታይተዋል።












