ኢትዮጵያውያኑ ጎተይቶም ገብረ ስላሴና ጉዬ አዶላ በበርሊን ማራቶን አሸናፊ ሆኑ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ጎተይቶም ገብረ ስላሴና ጉዬ አዶላ በዛሬው ዕለት በጀርመኗ መዲና በርሊን በተካሄደውን የማራቶን ውድድር በሴቶችና በወንዶች ዘርፍ በአንደኛነት አጠናቀዋል።
በሴቶች የማራቶን ውድድር ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ስፍራ የያዙት ኢትዮጵያውያን ናቸው።
በወንዶች የማራቶን ውድድር ከፍተኛ ግምት የተሰጠውና ከወራት በፊት ከኮሮናቫይረስ ህመም ያገገመው ቀነኒሳ በቀለ በሶስተኛነት አጠናቋል።
ጉዬ አዶላ በ2፡05፡45 ሰዓት የአሸናፊነቱን ስፍራ ሲይዝ ኬንያዊው የጎን ቤትዌል ሁለተኛ፣ ቀነኒሳ በቀለ ሶስተኛ፣ ታዱ አባተ አራተኛ ስፍራን ይዟል።
የ30 አመቱ ጉዬ አዶላ ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የመጀመሪያ በሆነው ውድድን የአለም ክብረ ወስንንና ሁለት ጊዜ የአለም ሻምፒዮና ከሆነው ኢሉይድ ኪፕቾጌን በመከተል ሁለተኛ ወጥቷል።
በሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነችው ጎተይቶም ገብረሥላሴ የበርሊን የማራቶን ውድድር የመጀመሪያዋ ነው።
ጎተይቶም ይህንን ውድድር በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ09 ስታጠናቀቅ ሕይወት ገብረ ኪዳን በ2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ሁለተኛ በማሸነፍ የብር ሜዳሊያዋን አሸንፋለች። በሶስተኛ ደረጃም ኢትዮጵያዊቷ ቶላ በሶስተኛነት ውድድሩን አጠናቃለች።
ጉዮ ማነው?
ብዙ ያልተባለለት የ26 አመት እድሜ ያለው ጉዬ አዶላ ድንገት ከየት ተገኘ?
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ቢሉ በምትባል አካባቢ የተወለደው ጉዬ፤ እንደ ቀደሙት አትሌቶች ሩጫን የጀመረው በህፃንነቱ ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ነው። ዕድሜው 17 ሲሞላ ለቀጣይ ስልጠናዎች አዲስ አበባን መዳረሻው አደረገ። የአምቦ አትሌቲክስ ክለብ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ተፈሪ መኮንን በሩጫ ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ አበክሮ የሚናገረው ጉዬ፤ የሩጫ ህይወቱ ግን ማንሰራራት የጀመረው በኦሮሚያ የውሃ ሥራዎች ክለብ ቆይታው ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የመጀመሪያው ትልቅ ውድድር የነበረው ከሦስት ዓመታት በፊት ማራኬሽ ከተማ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ነው። ይህም ለቀጣይ ውድድሮቹ ፈር የቀደደለት ሲሆን፤ በዚያው ዓመትም በተመሳሳይ ርቀት እንዲሁም በ10 ኪ.ሜ ብዙ ውድድሮችን አድርጓል። ነገር ግን ብዙ የሚያስደስት ውጤት ማምጣት አልቻለም።
"የጤና እክል ደርሶብኝ ስለነበር ምግብ መመገብ ከብዶኝ ነበር" በማለት የሚናገረው ጉዬ፤ "ሰው ካልበላ ደግሞ መሮጥ ከባድ ነው፤ ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ ቀላል የማይባሉ የእግር ጉዳቶች ደርሰውብኝ ነበር" ይላል። ብዙዎች አትሌቶች ከድህነት በመውጣት የተሻለ ህይወትን ለማግኘት ሩጫን እንደ መውጫ መንገድ ያዩታል። የጉዬም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም።
"ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ምን አይነት ህይወት እንደሚመሩ ከዚያው የመጡ ያውቁታል። ከደሃ ቤተሰብ ነው የመጣሁት፤ ሩጫ ከጀመርኩ በኋላ ግን የቤተሰቦቼ ህይወት ላይ መሻሻል አለ" በማለት ይናገራል።
- የትውልድ ቀን፡ ጥቅምት 27 1984
- የትውልድ ቦታ፡ ኦሮሚያ ክልል ቢሉ በሚባል ቦታ
- ሙሉስም፡ ጉዮ አዶላ ኢደማ
- ቁመትና ክብደት፡ 1.8 ሜትር፣ 60 ኪ.ግ
- ወኪል/ማኔጀር፡ ጂያኒ ዲማዶና የአትሌቲክስ ፕሮሞሽን (ጣልያን)
- ስፖንሰር፡ አዲዳስ
ከእሱ በፊት የመጡ የሩጫ ጀግኖች የሚላቸውን የእነ ቀነኒሳ በቀለ እንዲሁም የጥሩነሽ ዲባባን ስኬት ማየቱ ትምህርቱን ዘጠነኛ ክፍል ላይ አቋርጦ ለሩጫ ሙሉ ትኩረቱን እንዲሰጥ አደረገው። የእሁድ ዕለቱ ድልም በሩጫ ዘመኑ ሁለተኛ የሚባለውን የ24 ሺህ ዶላር ሽልማትን አስገኝቶለታል። ከሦስት ዓመታት በፊት ከፍተኛ የሚባለውን ብር ያገኘው ህንድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ሲሆን፤ ከማሸነፉ በተጨማሪ አዲስ ክብረ-ወሰንም አስመዝግቧል። በወቅቱ የተከፈለውም 35 ሺህ ዶላር ነበር። ከበርሊን ውድድር በኋላ ጣልያናዊው ማኔጀሩ ዝናውም ሆነ የሚያገኘው ብር ይቀየራል በማለትም አስተያየቱን ይሰጣል።
"በዚህ ውድድር ላይ ያሸንፋል ተብሎ ስላልተጠበቀ፤ በአዘጋጆቹ የተሰጠው ክፍያ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።" በማለት የሚናገረው ጂያኒ ዲማዶና "ከዚህ በኋላ ግን ጠቀም ያለ ክፍያ ይሰጡታል" ይላል።
ተጨማሪ የማራቶን ተስፋዎች
ጉዬ የእራሱ ቤት የለውም፤ አላገባም። ነገር ግን በበርሊን ላይ ካሸነፈ በኋላ ብሩህ ተስፋ እንደሚታየው ተናግሯል። ጂያኒ ዲማዶናም የአሁኑን የጉዬን ድል እንደ ትልቅ ስኬት በማየት፤ ቀጣዩ ዝግጅታቸው በሚያዝያ ወር ላይ ለሚካሄደው ትልቁ የለንደን ማራቶን መሆኑን ይናገራል።












