ኳታር ለሶማሊያ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ለገሰች

የፎቶው ባለመብት, MOHAMED ABDIWAHAB
የኳታር መንግሥት ለሶማሊያ 68 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ለገሰች።
የሶማሊያ መከላከያ ሚንስትር ሀሰን አሊ ሞሀመድ እና የሶማሊያ መከላከያ ሚንስትር ኃላፊ ዳሂር አዳን ኤልሚ፤ ሞቃዲሾ ውስጥ በተካሄደ የርክክብ ስነ ስርዐት መኪኖቹን ተቀብለዋል።
ጎብጆግ የተባለው የሶማሊያ ሚዲያ የኳታር አመራሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የተለገሱት አል ሸባብን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ነው።
ጎብጆግ የሶማሊያ የመከላከያ ሚንስትር የኳታርን መንግሥትን ለልገሳው ማመስገናቸውንም ጨምሮ ዘግቧል።
የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?
ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላልይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
የሶማሊያ መከላከያ ሠራዊት ከኳታር ወታደራዊ ኃላፊዎች ጋር በሞቃዲሾ በቅርቡ ተገናኝተው ነበር።
ኳታር የሶማሊያ መንግሥትን ከሚደግፉ ሀገሮች አንዷ ናት።












