ኢትዮጵያዊው ጀማል ይመር በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ

ኢትዮጵያዊው ጀማል ይመር በአፍሪካ የአዋቂዎች የአትሌቲክስ ውድድር በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አንዱአምላክ በልሁ እና ዩጋንዳዊውን ቲሞቲ ቶሮቲችን አስከትሎ ነው አሸናፊ የሆነው።

በናይጄሪያ አሳባ ዴልታ እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር ጀማል 29 ደቂቃ ከ08 ደቂቃ በማስመዝገብ ለሃገሩ በውድድሩ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ትላንት ለሀገሩ አስመዝግቧል።

በተጨማሪም በቀጣይ ወር ኦስትራቭ ቼክ ሪፐብሊክ ውስጥ በሚካሄደው አህጉር አቀፍ ውድድር ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።

ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያው ያገኘው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አንዱአምላክ በልሁ ነው።