ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው ከነበሩ ቻይናውያን የማዕድን ሰራተኞች መካከል አስራ አንዱ በሕይወት ወጡ

600 ሜትር ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው ከነበሩ ቻይናውያን የማዕድን ሰራተኞች መካከል አስራ አንዱ በሕይወት መውጣት ችለዋል።

የቻይና ብዙሃን መገናኛዎች እንደዘገቡት 6 መቶ ሜትር ጥልቀት ካለው ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ለሁለት ሳምንታት ከቆዩት የማዕድን ሰራተኞች መካከል አስራን አንዱንን በሕይወት ከጉድጓዱ ማውጣት ተችሏል።

ባለፈው ጥር 2፣ በቻይና ሻንዶንግ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ሁሻን የወርቅ ማዕድን ማውጫ የመውጫ ዋሻ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ነበር የመውጫ በሩ ተዘግቶ የማዕድን ሰራተኞቹ ውስጥ እንዳሉ ታፍነው የቀሩት።

11 ሰራተኞች ወዲያውኑ ከፍንዳታው መትረፍ ቢችሉም አንደኛው ከቆይታ በኋላ ሕይወቱ አልፏል።

ጉድጓዱ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ቴሌኮሙኒኬሽን የተሰራላቸው ሲሆን ምግብ እና መድሃኒትም በትንሽ ቀዳዳ እየተላከላቸው ነው።

የፍንዳታው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። በሕይወት የተረፈው ሰው ብርሃን እንዳያስቸግረው በሚል ዓይኑ ተሸፍኖ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል ተብሏል።

ይህ ሰው ምግብ እና ውሃ ከሚደርሳቸው 10 ሰዎች ካሉበት ቡድን በተለየ ሁኔታ ለብቻው የነበረ ነው። መጀመሪያው ሰው ከወጣ ከአንድ ሰዓት በኋላ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች መውጣታቸውን የቻይና ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ ለማግኘት የሚደረገው ቁፋሮ ሳምንታትን ሊወስድ እንደሚችል ይጠበቃል። በሌላ በኩል ለአንደኛው ቡድን የሚላከው ምግብ እና መድሃኒት እንዳለ ሆኖ በሌላ ቦታ የሚገኙት የ11 ሰዎች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ግን እስካሁን አልታወቀም።

የእነዚህ ሰዎች በሕይወት መኖር የታወቀው አንድ ከእነሱ በ1 መቶ ሜትር ዝቅ ብሎ ከሚገኝ ሰው ጋር በነበራቸው ግንኙነት አማካኝነት ነው። ነገር ግን ከቆይታ በኋላ ከእዚህ ሰው ጋር የነበረው ግንኙነትም ተቋርጧል።

እንዴት ወጥመድ ውስጥ ገቡ?

ወደ ማዕድን መገኛው ውስጥ የሚወስደው ዋሻ ክፉኛ ተጎድቷል፤ ምክንያቱ ባልታወቀ ፍንዳታ ሳቢያም ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ ተቆራርጠዋል።

ለአንድ ሳምንት ያክል በሕይወት ስለመኖራቸው የሚያሳይ ምንም ዓይነት ምልክት አልነበረም። የዛሬ ሳምንት እሁድ ግን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቀጭን ቀዳዳ ውስጥ የላኩት ገመድ ሲጎተት ተሰማቸው።

ከዚያም ማስታወሻ የተጻፈበት ቁራጭ ወረቀት ከ12 የማዕድን ሰራተኞች [11ዱ አንድ ቦታ አንደኛው ደግሞ ትንሽ ዝቅ ብሎ] በሕይት መኖራቸውን በመግለጽ መልዕክት ወደ ላይ ላኩ።

ከዚያ በኋላ ግን 12ኛው ሰው ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋረጠ። በሌላ በኩል ከ11ዱ መካከል ደግሞ አንደኛው ግለሰብ በፍንዳታው ወቅት ራሱ ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት ስለነበር ባለፈው ሐሙስ በዚሁ ምክንያት መሞቱ ታውቋል።

በቻይና የማዕድን አደጋ ያልተለመደ አይደለም። የደኅንነት ቁጥጥሮች አተገባበር የላላ ነው። ባለፈው ታኅሥስ በከሰል ማዕድን ውስጥ በደረሰ የካርቦን ሞኖክሳይድ ልቀት ሳቢያ 23 ሰዎች ሞተዋል።

በተመሳሳይ ችግር በመስከረም ወርም 16 ሰዎች ሞተዋል። በ2019 በደቡብ ምዕራብ ቻይና በደረሰ የከሰል ማዕድን ማውጫ ፍንዳታም እንዲሁ 14 ሰዎች ሞተው ነበር።

የማዕድን ሰራተኞቹ በምን ሁኔታ ናቸው ያሉት?

አስሩ ሰዎች 600 ሜትር ጥልቀት ውስጥ ባለው የጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ነው ያሉት። እነዚህ ሰዎች ከአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ውስጥ ይገኛሉ። መድሃኒትም ሆነ ምግብ በትንሽ ቀዳዳ ውስጥ ይላክላቸዋል።

ገንፎ እና አልሚ የሆኑ ፈሳሽ ነገሮች እየተላኩላቸው ሲሆን ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ባሕላዊ ምግብ እና ወጣወጥ ነገር እንዲላክላቸው ጠይቀው ነበር።

ስምንቱ ደህና መሆናቸው ሲታመን ሁለቱ ግን ከፍተኛ ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዳልቀረ ተገምቷል።

የመጀመሪያው ሰው ከወጣ ከአንድ ሰዓት በኋላ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በሕይወት መትረፋቸው እና መውጣታቸው ተረጋግጧል። ምናልባት በሙሉ ጤንነት ውስጥ ነበሩ ተብለው የተገመቱት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ይታመናል።