"ቻይና በአፍሪካ የጦር ሰፈር ለመክፈት አራት አገራትን እያማረጠች ነው" አሜሪካ

የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ቻይና በአፍሪካ ወሳኝ የጦር ሰፈር አስፈልጓታል አለ። አራት አገራትንም ለዚሁ ዓላማ በቻይና ታጭተዋል ብሏል።፡

ከአሜሪካ መከላከያ ሚንስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ኬንያ፣ ሲሼልስ፣ ታንዛኒያና አንጎላ ናቸው ቻይና የጦር ሰፈር ልትከፍትባቸው ያሰበቻቸው አገራት።

ሆኖም ግን ሌሎችም አገራትም በቻይና እቅድ ውስጥ ቢኖሩም ለጊዜው ስማቸውን አልተገለም።

ይህን የአሜሪካንን መግለጫ በተመለከተ አራቱ አገራት ምላሽ አልሰጡም።

ይህ ሪፖርት የወጣው ባለፈው ሳምንት ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በስፋት ሪፖርቱ በየአገራቱ ሚዲያዎች ሲናፈስ ቆይቷል።

ዘገባው እንደሚለው ቻይና አሁን በጂቡቲ ካላት የጦር ሰፈር ሌላ በሌሎች ቢያንስ አራት አገራት፣ የአየር፣ የባሕር፣ የእግረኛ ጦር ማቀነባበርያ የጦር ሰፈር ለመክፈት ከጅላለች፣ ንግግርም ጀምራለች።

ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ በማያንማር፣ በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በኢንዶኒዢያ፣ በፖኪስታን፣ በሲሪላንካ፣ በዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ በአንጎላና በታጃኪስታን ሌሎች ጦር ሰፈሮችን ለመክፈት ቻይና ስለማሰቧ ተነግሯል።