ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የሩስያው የተቃዋሚ መሪ ሳይመረዝ እንዳልቀረ የጀርመን ሐኪሞች ገለፁ
የሩሲያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆነው አሌክሴ ናቫልኒን እያከመ የሚገኘው የበርሊን ሆስፒታል መመረዙን አረጋገጠ።
ቻሪቴ ሆስፒታል ያወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው፤ በጽኑ ታምሞ በሕክምና ላይ የሚገኘው ናቫልኒ ላይ የተደረገው ምርመራ እንደሚያሳየው "በኮላይኔስትሬስ አጋጅ ኬሚካል ተመርዟል"።
በተጨማሪም "ክፉኛ የታመመ ቢሆንም ለሕይወቱ አያሰጋውም" ብሏል መግለጫው።
አሌክሴ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ በሚገኝ አንድ ካፌ ውስጥ ያዘዘው ሻይ ላይ መርዝ ሳይሰጠው አልቀረም ተብሏል። አውሮፕላን ውስጥ እንደገባ ነው ተዝለፍልፎ የወደቀው።
ናቫልኒ ከሰርብያዋ ቶምስክ ወደ ሞስኮ እየበረረ ሳለ ክፉኛ ታምሞ ሲያጣጥር የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል።
ደጋፊዎቹ በጠጣው ሻይ እንደተመረዘ ይጠረጥራሉ።
"በምን እንደተመረዘ እቅጩን መናገር አይቻልም" ያለው ሆስፒታሉ፤ "ሰፋ ኣለ ምርመራ ተጀምረወል። የመርዙ- ያም ማለት ኮላይኔስትሬስ አጋጅ ኬሚካል በኦርጋኒዝም ውስጥ ያለው ተጽዕኖ በበርካታ የግል ቤተ ሙከራዎች በተደጋጋሚ ተረገግጧል።"
ናቫልኒ አትሮፓይን የተሰኘ አንቲዶት እየተሰጠው መሆኑ ተገልጿል።
ሆስፒታሉ እንደገለፀው ምናልባት ግለሰቡ የተመረዘበት ኬሚካል ቀጣይ ያለው ተጽዕኖ በሚገባ ያልተለየ ሲሆን ምናልባት የነርቭ ስርአቱ ላይ ቋሚ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።