ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ የገባው መኪና እየተፈለገ ነው
ከኬንያ ሞምባሳ ወደብ ወደ ባህር ዳርቻው የእቃና የሰው ማሻገሪያ መርከብ ላይ ሆኖ ሲያቋርጥ የነበረ መኪና ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ገብቶ እየተፈለገ መሆኑ ተገለፀ።
መኪናው ውስጥ ሦስት ሰዎች ሳይኖሩ እንዳልቀረ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
አደጋው ትናንት ያጋጠመ ሲሆን ከሞምባሳን ወደ ሊኮኒን በማቋረጥ ላይ ሳለ መሃል ላይ ሲደርስ ወደ ኋላ በመንሸራተቱ አደጋው እንዳጋጠመው ታውቋል።
አደጋው ሲደርስ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስልም በትዊትር ላይ በስፋት ተሰራጭቷል።
የዓይን እማኞች ለዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ እንደተናገሩት እንዲት ሴትና ሕፃን መኪናው ውስጥ ነበሩ።
"አንዲት ሴትና ወንድ ልጅ መኪናው ውስጥ ሆነው ተመልክቻለሁ፤ መኪናው ሲገለበጥ ሴትዮዋ ስትጮህና እርዳታ ስትጠይቅ ነበር። ከዚያም የነፍስ አድን ሠራተኞችን እንዲደርሱላቸው ላኩላቸው" ብለዋል።
ዴይሊ ኔሽን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በመኪናው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቁጥር አራት ነው።
የኬንያ የመርከብ አገልግሎት ባለሥልጣን ፍለጋውና የነፍስ አድን ሥራው እንደቀጠለ አስታውቋል።
የሰው እና ዕቃ ማሻገሪያ መርከቡ ኦፕሬተር እስካሁን በፍለጋው ምንም ፍንጭ አለመገኘቱን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።