ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ
የኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን በትናንትናው ጥቃት መገደላቸውን ተነገረ።
መቀሌ የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር ድምፂ ወያነና የትግራይ ቴሌቪዥን የጄኔራል ሰዓረን መገደል ዘግበው የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሃዘን መግለጫ መልእክትንም አቅርበዋል።
ከጄኔራል ሰዓረ በተጨማሪ ጄኔራል ገዛኢ አበራም ህይወታቸው ማለፉን በተጨማሪ ዘግበዋል።
በአማራ ክልል በተሞከረው መፈንቅለ መንግሥትም ሁለት የክልሉ ባለስልጣናት መሞታቸው የተገለፀ ሲሆን ማንነታቸው እስካሁን አልታወቀም።