በጆርጅያ ግዛት ፅንስ ማቋረጥን የሚከለክለው ሕግ በሆሊውድ አድማ አስከተለ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ውርጃን አስመልክቶ የተደነገገው የጆርጅያ ሕግ ብዙ የሆሊውድ ተዋናዮችን አስቆጥቶ አድማ አስነስቷል። ይህንን ተከትሎም የ'ሚ ቱ' ተሟጋች የሆነችው አሊሳ ሚላኖ እና ሌሎችም የሆሊውድ ተዋንያን በጆርጅያ ውርጃን አስመልክቶ በተደነገገው ሕግ ምክንያት የወሲብ አድማ ጠርተዋል።
እስከ 6 ሳምንታት ያስቆጠረን ፅንስ ማቋረጥ የሚከለክለው ሕግ ቢፀድቅ ተዋናዮች ሥራ ለማቆም ዝግጁ እንደሆኑ በፊርማቸው አሳውቀው ነበር።
ፅንስ ማቋረጥ የከለከሉትን የአሜሪካ ግዛቶች ጆርጅያ ተቀላቅላለች።
'ሚ ቱ' በተሰኘው እንቅስቃሴ የምትታወቅ ተዋናይ አሊሳ ሚላኖ ሴቶች በቅዳሜ ዕለት የወሲብ አድማውን እንዲቀላቀሏት ጠይቃለች።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 1

በትዊተር ገጿ ያሰፈረችውም የብዙዎችን ትኩረት ከመሳቡም ባሻገር የተከፋፈሉ ሃሳቦችንም አስተናግዷል።
ሕጉ ምንድን ነው ? ጥያቄስ ለምን አስነሳ?
በታህሳሥ 22 ቀን 2012 ዓ. ም ሥራ ላይ የሚውለው ሕግ በጆርጅያ ገዢ ብራየን ኬምፕ ባለፈው ማክሰኞ የፀደቀ ሲሆን ስሙም "ሃርትቢት" ወይም የልብ ትርታ ነው።
ይህም ሆኖ ህጉ በፍርድ ቤት ብዙ ተቃውሞዎችን ያስነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ኬንታኪ በተሰኘችው ግዛት ተመሳሳይ ሕግ በፌዴራል ዳኛ እንዲወጣ የተደረገ ሲሆን በሚሲሲፒ ደግሞ ከሁለት ወር በኋላ ሥራ ላይ ይውላል የተባለው ሕግ ብዙ ተቃውሞ ማስነሳቱ ይታወቃል።
የማቅለሽለሽ ስሜት ብዙውን ጊዜ ከ9ኛው ሳምንት በመጀመሩ ብዙ ሴቶች በ6ኛ ሳምንታቸው ማርገዛቸውን ላያውቁ ይችላሉ።
የፊልምና የቴሌቪዥን ዘርፉ ባለፈው ዓመት ብቻ ለጆርጅያ ግዛት 2.7 ቢልየን ዶላር አስገብቷል። ታዋቂ የሆኑት እንደ ብላክ ፓንተር፣ ሃንገር ጌምዝ፣ ዘ ዎኪንግ ዴድና ስትሬንጀር ቲንግስ የተሰኙት ፊልሞች በጆርጅያ ነው የተቀረፁት።
አድማው ምንድን ነው?
ሕግ ከመደንገጉ በፊት ወደ 50 የሚሆኑ ተዋንያን በጆርጅያ የሚሠሩ ፊልሞች ላይ እንደማይሳተፉ በደብዳቤ አሳወቁ። ከእነርሱም መካከል አሊሳ ሚላኖ፣ ኤሚ ሹመር፣ ክሪስቲና አፕልጌት፣ አሌክ ባልድዊንና ሾን ፔን ይገኙበታል።
ደብዳቤውም "እኛ ጆርጅያ መሥራት እንፈልጋለን፤ ቢሆንም ግን ይህ ሕግ የሚፀድቅ ከሆነ ዝም ብለን ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም፤ የሴቶች ደህንነት ወደ ተጠበቁባቸው ግዛቶች መሄዳችን አይቀርም። " ብለዋል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 2

'ኢንሳቲየብል' በተሰኘው የኔትፍሊክስ ፊልም ላይ የምትተውነው አሊሳ "ኢንሳቲየብልን መብታችንን ወደሚያከብር ቦታ ለማዘዋወር እንጋደላለን" ስትል ለባዝፊድ ተናግራለች።
በስምምነቷ መሠረት የቀረፃ ተጨማሪ አንድ ወር ቢቀራትም ሦስተኛውን ክፍል ግን በጆርጅያ የመቅረፅ ሃሳብ እንደሌላት ትናገራለች። ብዙ ተዋናዮችም ድጋፋቸውን አሰምተዋል።
ክሪስቲን ቫሾ ኪለር ፊልምስ የተሰኘው የፕሮዳክሽን ድርጅቷ ከአሊስ ጋር እንደሚቆም "ይህ ሕግ እስኪቀር ድረስ" ጆርጅያ ውስጥ ለመሥራት አላስብም ትላለች።
ዘ ዋየር የተሰኘው ፊልም ደራሲ ዴቪድ ሳይመን እና ሌሎችም አድማውን ተቀላቅለዋል።
የአሜሪካ ደራስያን ማህበር ሕጉን ከመተቸቱም ባሻገር "በፊልም ዘርፉ ለተሰማሩት አባሎቻችን ጆርጅያ ከባድ ቦታ ሊሆን ነው" ብሏል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 3

ጄጄ አብረሃምና ጆርደን ፒል የተሰኙት የፊልም ዳይሬክተሮች 'ላቭ ክራፍት' የተሰኘውን ፊልም በጆርጅያ መሥራታቸውን ባያቆሙም ከአሁን ወዲህ ከሚሠሯቸው የፊልሙ ክፍሎች የሚያገኙትን ሙሉ ገቢ ሕጉን ለሚዋጉት ሰዎች እንደሚለግሱ ተናግረዋል።
የጆርጅያ 'ፊታል ሃርትቢት' ወይም የፅንስ ልብ ትርታ ሕግ አግባብ እንዳልሆነና የሴቶችን መብት ከመጋፋቱም በላይ በራሳቸው ጤና ላይ ለመወሰን የሚያስችላቸውን አቅም የሚጋፋ ነው በማለት አስረድተዋል።
"አትሳሳቱ ይህ ሆን ተብሎ ሴቶች ላይ ዒላማ ያደረገ ሕግ ነው" ብለዋል።
ይህም ሆኖ የሕግ ድርድሩ ምን ላይ እንደሚደርስ ለማየት እየተጠባበቁ ያሉ አድማውን ያልተሳተፉ ብዙዎች አሉ።
የሞሽን ፒክቸር አሶሲዬሽን ቃል አቀባይ የሆኑት ክሪስ ኦርትማን "የፊልምና የቴሌቪዥን ዘርፉ ወደ 92 ሺህ ሠራተኞችን የሚቀጥር በመሆኑ የማሕበረሰቡን ቤተሰብ እና ኢኮኖሚያቸውን የቻለ ነው" ሲል ያስረዳል።
ጆርጅያ ላይ አድማ ከማድረግ ይልቅ ሕጉን በፍርድ ቤት መገዳደሩ የተሻለ ነው የሚል ሃሳብም ያንፀባርቃል።
"በመላው ግዛት የሚሠሩትስ ሠራተኞች? ለእነርሱ አድማው እንዴት ሊጠቅማቸው ነው?" ስትል ተሟጋቿ ኦሪዬል ማሪ በትዊተር ገጿ ላይ አስፍራ ተዋናዮቹ ከዚህ ይልቅ ለሃገር በቀል ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ቢያደርጉ ይሻላል ብላለች።












