ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የነጻነት ቅርጫት: የሴቶች መጽሄት
በእንግሊዝ 1693 ይታተም የነበረው ''ዘ ሌዲስ ሜርኩሪ'' የተሰኘው መጽሄት ለሴቶች ታስቦ የታተመው የመጀመሪያው መጽሄት ሳይሆን እንደማይቀር ይነገራል።
ይህ መጽሄት ''ለሴቶች ቅርብ'' ናቸው የሚላቸውን ፍቅር፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና አለባበስን በመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደርግ ነበር።
ዛሬ ላይ የሚታተሙት የሴቶች መጽሄት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ቢዳስሱም በብዛት ግን ርዕሰ ጉዳዮቻቸው ስለ ፋሽን እና ዝነኛ ሰዎችን የሚመለከቱ ሃሜት ላይ የተጠመዱ ይመስላሉ።
ውጤታማ የሆኑ የመጽሄቶቹ ባለቤቶች እና አርታዒዎች የስኬታቸው ምንጭ አንባቢዎቻቸው የሚፈልጉትን ማቅረብ በመቻላችን ነው የሚል መከራከሪያ ይዘው ሊቀርቡ ይችላሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በታዋቂ ግለሰቦች ፍቅር መውደቅ በወጣቶች ላይ የዓይምሮ ህመም እያስከተለ ነው። በቅርቡ የተካሄደ ጥናት ይፋ እንዳደረገው ዕድሜያቸው ከ11-16 የሚሆኑ የዓይምሮ ህመም ያጋጠማቸው ታዳጊዎች፤ እንከን የለሽ መስለን ለመታየት ግፊት ያሳደሩብን ታዋቂ ግለሰቦች ናቸው ብለዋል።