'የሮያል ሶሳይቲ' ውድድር አሸናፊ ፎቶዎች

በአህጉረ አንታርክቲካ በቅርፅ በቅርፅ የተቀመጡ በረዎችን እንዲያሳይ አድርጎ ከከፍታ ሥፍራ የተነሳው ፎቶ የ2017 የሮያል ሶሳይቲ ፎተ ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

'ሮያል ሶሳይቲ' የተሰኘው የፎቶ ውድድር ስነ-ጠፈር፣ የአካባቢ ሳይንስ የምድር ሳይንስን ጨምሮ ሰባት የመወዳደሪያ ዘርፎችን አካቶ የነበረ ሲሆን 1100 ፎቶዎችም ለፉክክር ቀርበዋል።

ፒተር ኮንቬይ ያነሳው ይህ ፎቶ በምድር ሳይንስና በአየር ንብረት ዘርፍ ከማሸነፉም በላይ የጠቅላላ የውድድሩ አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል። ፎቶው በአውሮፓውያኑ በ1995 በደቡባዊ አንታርክቲካ የተነሳ ነው።

ኒኮ ዴብሩይን ያነሳው ይህ ፎቶ ደግሞ በአንታርክቲካው ማርዮን ደሴት ዳርቻ በምትገኝ አነስተኛ ሰርት ላይ ገዳይ ዌሎች ሰብሰብ ብለው ያሉ ፔንግዊኖችን ለማደን ሲሞክሩ ያሳያል። ፎቶው በኢኮሎጂና በአካባቢ ሳይንስ ዘርፍ ማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።

አንቶኒያ ዶንሲላ ያነሳቸው ይህ ፎቶ ደግሞ አንድ በንፍቀ ክበብ አካባቢ የሚገኝ ድብ ግሪንላንድ ባህር ዳርቻ ላይ ተቀምጦ ውሃ ውሃ እያየ ሲተክዝ ያሳያል። በባህርይ ጥናት ዘርፍም ሽልማቱን ማንሳት ችሏል።

በሱሚታ ዳታ የተነሳው ፎቶ ኢንዲያን ሮለር የተሰኘች የወፍ ዝርያ ጊንጥ ስትበላ ያስመለክተናል፤ በባህርይ ጥናት ዘርፍ ሁለተኛ ለመውጣትም ችሏል።

በሃዋይ ከሚገኝ እሣተ ገሞራ ላይ ሲፈስ የሚታየው ይህ ቀላጭ እሣት በሳብሪና ኮለር የተነሳ ሲሆን በምድር ሳይንስ ዘርፍ የክብር ሽልማት ማግኘት ችሏል።

አሜሪካንና ሌሎች ሃገራትን የሸፈነው የዘንድሮው የፀሐይ ግርዶሽ በዌይ-ፌንግ ዡ ተነስቶ በስነ-ከዋክብት ዘርፍ ሁለተኛ ወጥቷል።

ዳቪድ ኮስታንቲኒ በባህርይ ጥናት ዘርፍ ከላይ በሚታየው ፎቶ ሁለተኛ መውጣት ችሏል።

በኢኮሎጂና በአካባቢ ሳይንስ ዘርፍ የክብር ሽልማቱን ማግኘት የቻለው ካርሎስ ጃሬድ ያነሳውና ሁለት አረንጓዴ እንቁራሪቶች ተደራርበው የሚየሳየው ፎቶ ነው።

'የማይታዩት ጉንዳኖች' የሚል ስያሜ የተሰጠው የቶማስ ኢንድሌይን ፎቶ በኢኮሊጂና በአካባቢ ሳይንስ ዘርፍ ሁለተኛ መውጣት ችሏል።