'የሮያል ሶሳይቲ' ውድድር አሸናፊ ፎቶዎች

በአህጉረ አንታርክቲካ በቅርፅ በቅርፅ የተቀመጡ በረዎችን እንዲያሳይ አድርጎ ከከፍታ ሥፍራ የተነሳው ፎቶ የ2017 የሮያል ሶሳይቲ ፎተ ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

'ሮያል ሶሳይቲ' የተሰኘው የፎቶ ውድድር ስነ-ጠፈር፣ የአካባቢ ሳይንስ የምድር ሳይንስን ጨምሮ ሰባት የመወዳደሪያ ዘርፎችን አካቶ የነበረ ሲሆን 1100 ፎቶዎችም ለፉክክር ቀርበዋል።

Plane and its shadow with ice below

የፎቶው ባለመብት, Peter Convey/PA

ፒተር ኮንቬይ ያነሳው ይህ ፎቶ በምድር ሳይንስና በአየር ንብረት ዘርፍ ከማሸነፉም በላይ የጠቅላላ የውድድሩ አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል። ፎቶው በአውሮፓውያኑ በ1995 በደቡባዊ አንታርክቲካ የተነሳ ነው።

Group of penguins next to water with two killer whales visible

የፎቶው ባለመብት, Nico de Bruyn/PA

ኒኮ ዴብሩይን ያነሳው ይህ ፎቶ ደግሞ በአንታርክቲካው ማርዮን ደሴት ዳርቻ በምትገኝ አነስተኛ ሰርት ላይ ገዳይ ዌሎች ሰብሰብ ብለው ያሉ ፔንግዊኖችን ለማደን ሲሞክሩ ያሳያል። ፎቶው በኢኮሎጂና በአካባቢ ሳይንስ ዘርፍ ማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።

Polar bear lying on ice next to water

የፎቶው ባለመብት, Antonia Doncila/PA

አንቶኒያ ዶንሲላ ያነሳቸው ይህ ፎቶ ደግሞ አንድ በንፍቀ ክበብ አካባቢ የሚገኝ ድብ ግሪንላንድ ባህር ዳርቻ ላይ ተቀምጦ ውሃ ውሃ እያየ ሲተክዝ ያሳያል። በባህርይ ጥናት ዘርፍም ሽልማቱን ማንሳት ችሏል።

A bird with a scorpion suspended in the air above its beak

የፎቶው ባለመብት, Susmita Datta/PA

በሱሚታ ዳታ የተነሳው ፎቶ ኢንዲያን ሮለር የተሰኘች የወፍ ዝርያ ጊንጥ ስትበላ ያስመለክተናል፤ በባህርይ ጥናት ዘርፍ ሁለተኛ ለመውጣትም ችሏል።

Lava flow

የፎቶው ባለመብት, Sabrina Koehler/PA

በሃዋይ ከሚገኝ እሣተ ገሞራ ላይ ሲፈስ የሚታየው ይህ ቀላጭ እሣት በሳብሪና ኮለር የተነሳ ሲሆን በምድር ሳይንስ ዘርፍ የክብር ሽልማት ማግኘት ችሏል።

Eclipse with clouds in the sky

የፎቶው ባለመብት, Wei-Feng Xue/PA

አሜሪካንና ሌሎች ሃገራትን የሸፈነው የዘንድሮው የፀሐይ ግርዶሽ በዌይ-ፌንግ ዡ ተነስቶ በስነ-ከዋክብት ዘርፍ ሁለተኛ ወጥቷል።

Two birds sitting on a spade

የፎቶው ባለመብት, David Costantini/PA

ዳቪድ ኮስታንቲኒ በባህርይ ጥናት ዘርፍ ከላይ በሚታየው ፎቶ ሁለተኛ መውጣት ችሏል።

Two frogs

የፎቶው ባለመብት, Carlos Jared/PA

በኢኮሎጂና በአካባቢ ሳይንስ ዘርፍ የክብር ሽልማቱን ማግኘት የቻለው ካርሎስ ጃሬድ ያነሳውና ሁለት አረንጓዴ እንቁራሪቶች ተደራርበው የሚየሳየው ፎቶ ነው።

Pitcher plant

የፎቶው ባለመብት, Thomas Endlein/PA

'የማይታዩት ጉንዳኖች' የሚል ስያሜ የተሰጠው የቶማስ ኢንድሌይን ፎቶ በኢኮሊጂና በአካባቢ ሳይንስ ዘርፍ ሁለተኛ መውጣት ችሏል።