ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ይሆን? ለኤፍኤ ዋንጫስ እነማን ለፍጻሜ ይደርሳሉ? የሳምንቱ ጨዋታዎች ግምት
ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ለመሆን ከጫፍ ቢደርስም የኤፍኤ ዋንጫ አሸናፊውን ለመገመት ግን ከባድ ሆኗል።
በኤፍኤ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶን ቪላ ሲገናኙ፤ ኖቲንግሃም ፎረስት እና ማንቸስተር ሲቲም ግጥሚያቸውን ያከናውናሉ።
የኤፍኤ ዋንጫው ለቀሪዎቹ አራት ቡድኖች "ክፍት ነው" ሲል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ገልጿል።
ሱተን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ጨዋታዎችን ጨምሮ የኤፍኤ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ገምቷል።
ቅዳሜ
ቼልሲ ከ ኤቨርተን
ለኤቨርተን መጥፎው ዜና ጀምስ ታርኮውስኪ በጉዳት ከውድድር ዘመኑ ውጭ መሆኑ ቡድኑ የነበረውን የመከላከል ጥንካሬ ያሳጣዋል።
ኤቨርተን አጥቂውን አርማንዶ ብሮያን ማሰለፍ ባይችልም የፊት መስመሩን ቤቶ ይመራዋል።
ኤቨርተን ራሱን እያሻሻለ ቢሆንም ቼልሲ ግን በውጤት መዋዠቅ ውስጥ ይገኛል።
ደጋፊው በአሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ አጨዋወት የተደሰተ አይመስልም።
ግምት፡ 1 – 1
ብራይተን ከዌስት ሃም
ሁለቱም ቡድኖች ወደ ማሸነፍ መመለስ ይኖርባቸዋል።
ብዙ የዌስት ሃም ደጋፊዎች ቡድኑ ከሳውዝሃምፕተን ጋር አቻ በመለያየቱ ደስተኛ አልሆኑም።
ብራይተን በተመሳሳይ በጥሩ አቋም ላይ አይገኝም።
ቡድኑ ጥሩ መንቀሳቀስ ቢችልም ውጤቱ መውረድ በመጀመሩ በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ በሚያደርገው ጉዞ ላይ እንቅፋት ሆኗል።
ግምት፡ 2 – 1
ኒውካስል ከ ኢፕስዊች ታወን
የኒውካስሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ህክምናቸውን አገባደው ወደ ጅራቸው ተመልሰዋል።
ባለፈው ሳምንት ኢፕስዊች ካሳየው አቋም አንጻር ኒውካስል የሚቸገርበት ጨዋታ አይሆንም።
ኒውካስል በሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ ሰፊ ዕድል ሲኖረው የኢፕስዊች የመውረድ ነገር ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ሆኗል።
ጨዋታውን በቀላሉ ኒውካስል ያሸንፋል።
ግምት፡ 3 – 0
ሳውዝሃምፐተን ከ ፉልሃም
ሳውዝሃምፐተን ከሊጉ መውረዱን አረጋግጧል።
የቡድኑ ደጋፊዎች በዚህ አስቸጋሪ ጊዜም ከቡድኑ ጎን ተልፈውሲደግፉት ታይተዋል።
በዚህ ጨዋታ የበላይነቱን የሚይዘው ፉልሃም ይሆናል፥
ግምት፡ 0 – 2
ዎልቭስ ከ ሌስተር ሲቲ
ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ካየን በሊጉ ጠንካራ ቡድን መሆኑን ያሳየው ዎልቭስ ነው።
ቡድኑ ባለፈው ሳምንት በፓብሎ ሳራቢያ የቅጣት ምት ኳስ ማንቸስተር ዩናይትድ አሸንፏል።
ሌስተር ከሊጉ መውረዱን በሊቨርፑል ከተሸነፉ በኋላ ተረጋግጧል።
ግምት፡ 2 – 0
ክሪስታል ፓላስ ከ አስቶን ቪላ (ኤፍኤ ዋንጫ)
ፓላስ በዘንድሮው ውድድር ዓመት ከቪላ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች ጥሩ ውጤቶችን አስመዝግቧል።
ቡድኑ ከአርሰናል ጋር እንደነበረው ከተጫወተ የማሸነፍ ዕድል አለው።
የኡናይ ኤምሬ ቡድን ካል ጥንካሬ አንጻር ፓላስ ዘንድሮ ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡ የቡድኑን ጥንካሬ ያሳያል።
ቪላ ከኤፍኤፍ ዋንጫ በተጨማሪ በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ጥሩ ዕድል አለው።
ቪላ ማክሰኞ ዕለት በማንቸስተር ሲቲ ቢሸነፍም በሻምፒዮንስ ሊግ ያሳየውን ጥንካሬ ይደግማል ወይ የሚል ጥያቄ ይነሳል።
ግምት፡ 2 – 3 (ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ)
እሑድ
በርንመዝ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
በርንመዝ ዘንድሮ ማንቸስተርን 3 ለምንም ያሸነፍ የቻለ ሲሆን በዚህ ጨዋታም የማሸነፍ ሰፊ ዕድል አለው።
ዩናይትድ ለዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ በሳምንቱ አጋማሽ ወደ አትሌቲክ ቢልባኦ ያቀናል።
አሞሪም ወጣት ተጫዋቾችን የሚያሰልፉ ሲሆን በርንመዝ ደግሞ በተነጻጻሪነት በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።
በዚህ ጨዋታ ለበርንመዝ ግምቴን የምሰጥ ሲሆን ዩናይትድ ከቢልባኦ ጋር የሚቸገር ይመስላል።
ግምት፡ 2 – 1
ሊቨርፑል ከ ቶተንሃም
ሊቨርፑል ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት አንድ ነጥብ ብቻ ነው የሚፈልገው።
ቶተንሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሊጉ ጠንካራ ቡድናቸውን አሰልፈው የጨዋታ መንፈሳቸውን ማነሳሳት አለባቸው የሚሉ አሉ።
ቶተንሃም በሚቀጥለው ሳምንት ከቦዶ/ግሊምት ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት ይህንን ያደርጋል ተብሎ አይጠበቅም።
ሊቨርፑል እንደዚህ ቀደሙ በጥሩ ብቃት ላይ ባይገኝም ዋንጫውን ለማንሳት በቁርጠኝነት ወደ ሜዳ ይገባሉ።
ግምት፡ 4 – 1
ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ማንቸስተር ሲቲ (ኤፍኤ ዋንጫ)
የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አመራረጥ ለዚህ ጨዋታ ወሳኝ ይሆናል።
ቡድኑ ባለፈው ሳምንት ተቀይረው በገቡት ኦማር ማርሙሽ እና ዠርሚ ዶኩ ጎሎች አስቶን ቪላን አሸንፏል።
ጋርዲዮላ ክንፍ ተጫዋቾችን ከመጠቀም ይልቅ የመሐል ሜዳውን የሚቆጣጠሩልትን ተጨዋዋቾችን እያስቀደመ ነው።
ይህ ደግሞ ጨዋታውን ለመገመት ከባድ ያደርገዋል።
ፎረስት ሰኞ ዕለት ሁለቱ ከመመራት ተነስቶ ቶተንሃምን ከከማሸነፉም በላይ በመልሶ ማጥቃት መጫወቱ ለሲቲ ፈተና ይሆንበታል።
ግምት፡ 1 – 2