ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የኑሮ ውድነትን ለማቅለል መንግሥታት መውሰድ የሚችሏቸው እርምጃዎች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመላው ዓለም ከባድ ምጣኔ ሀብታዊ ተጽእኖን አስከትሏል። እሱን ተከትሎ በተለያዩ ስፍራዎች የተከሰቱት ጦርነቶች እና ፍጥጫዎች ደግሞ ችግሩን አባብሰውታል።
እነዚህ ክስተቶች ደግሞ በምርቶች እና በአገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ እጥረትና የዋጋ ጭማሪን አስከትለዋል። በተለይ ነዳጅ እና የምግብ ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በመናሩ በውጤቱ የሌሎችም ዋጋ ጨምሯል።
ይህ ሀብታም ከድሃ ሳይል በሁሉም የምድራችን አገራት ላይ ውጤቱ የታየው የኑሮ ውድነት፣ በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ሕዝብ እየጎዳ ነው።
ነገር ግን ይህንን ቀውስ ለማስታገስ እና ለማቃለል መንግሥታት ተለያዩ አመራጮችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይመክራሉ። ምን ማድረግ ይችላሉ?