ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አውስትራሊያዊው ቤት ውስጥ በሚያሳድጉት ካንጋሮ ተገደሉ
አንድ አውስትራሊያዊ ቤት ውስጥ በሚያሳድጉት ካንጋሮ በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
የ77 ዓመቱን አዛውንት ለመጠየቅ ዘመዳቸው ሬድመንድ ወደሚገኘው ቤታቸው ያቀናሉ። አዛውንቱን ያገኟቸው ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ውስጥ ሆነው ነው።
የህክምና ባለሙያዎችን ተጠርተው በገጠር አካባቢ ከሚገኘው መሪያ ቤት በፍጥነት መድረስ ችለዋል። ካንጋሮው ግን ሰውየው ህክምና እንዳያገኙ ተከላክሏል ተብሏል።
በዚህ ምክንያት ፖሊሶች ካንጋሮውን ተኩሰው ለመግደል ተገደዋል። ግለሰቡም ወደ ህክምና ሳያቀኑ በመኖሪያ ቤታቸው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋገጧል።
ካንጋሮው አዛውንቱን ቀደም ብሎ ጥቃት አድርሶባቸዋል ብለን እናምናለን ሲሉ የፖሊስ ቃል አቀባይ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።
አውስትራሊያ ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ካንጋሮዎች መኖሪያ ናት።
ተመሳሳይ ጥቃቶች ግን እምብዛም ናቸው።
ከአውሮፓውያኑ1936 ወዲህ በካንጋሮ ጥቃት ህይወት ማለፉ ሪፖርት ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።