ቻርለስ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉሥ መሆናቸው በይፋ ታወጀ

የፎቶው ባለመብት, PA Media
በሴንት ጄምስ ቤተ መንግሥት በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ቻርለስ ሳልሳዊ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉሥ መሆናቸው ታወጀ።
ቻርለስ የእናታቸው ንግሥት ኤልዛቤጥ ዳግማዊት ሞትን ተከትሎ ወዲያውኑ ንጉሥ ቢሆኑም፣ታሪካዊ በተባለለት ጉባኤ በይፋ ንጉሥነታቸው ዛሬ ቅዳሜ ተረጋግጧል።
ንግሥናውን ባወጀው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ምንም እንኳን እስካሁን የንግሥቲቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበት ዕለት ባይታወቅም፣ ንጉሡ የቀብሩ ዕለት ሥራ ዝግ የሚሆንበት ዕለት እንዲሆን አጽድቀዋል።
ይህ ንግሥናው የጸደቀበት ጉባኤ ሥነ ሥርዓት በቴሌቪዥን ተላልፏል። ይህም በታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
በጉባኤው መጀመሪያ ላይ ንጉሡ ያልተገኙ ሲሆን፣ ነገር ግን በሁለተኛው ክፍል ላይ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የምክር ቤቱ አባላት እና የተለያዩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ታድመው ነበር።

የፎቶው ባለመብት, PA Media
የምክርቤቱ ፀሐፊ የሆኑት ሪቻርድ ቲልብሩክ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ከማለታቸው በፊት ቻርለስን “ንጉሥ፣ የኮመንዌልዝ የበላይ፣ የእምነት ጠባቂ” በማለት አውጀዋል።
በለንደንቤተ መንግሥትውስጥ ባለው አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ታድመው የነበሩት ከፍተኛ ፖለቲከኞች፣ ዳኞች እና ባለሥልጣናት “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ሲሉ በጋራ ተሰምተዋል።
ንጉሡምበበኩላቸው “በጣም አሳዛኝ ኃላፊነት” ያሉትን የእናታቸውን ሞት አውጀዋል።
ንጉሥቻርለስ “እናንተ፣ አጠቃላይ አገሩ እንዲሁም አጠቃላይ ዓለም ለደረሰብን የማይጠገን ሐዘን ያሳየንን ጥልቅ ርህራሔ አውቃለሁ። ይህም ለእህቴ እና ለወንድሞቼ ታላቅ መጽናኛ ነው” ብለዋል።
ንግሥናውየታወጀበት ሥነ ሥርዓት ላይ የቀድሞዎቹን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቦሪስ ጆንሰንን፣ ቴሬሳ ሜይን፣ ዴቪድ ካሜሩንን፣ ጎርደን ብራውንን እና ጆን ሜጀርን ጨምሮ 200 የምክር ቤቱ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በኋላምከሴንት ጄምስ ቤተ መንግሥትውጪ ተሰብስቦ የነበረው ሕዝብ በጋራ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” ካሉ በኋላ የአገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር ተዘምሯል።
ይህ ሥነ ሥርዓት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን ለሕዝብ የተላለፈ ሲሆን፣ይህንንም የወሰኑት ንጉሡ ቻርለስ ሳልሳዊ ናቸው።













