ጭምቅ ሀሳብ

  • የሕዳሴ ግድብ ዛሬ ማክሰኞ፣ ጳጉሜ 4/ 2017 ዓ.ም የጎረቤት አገራት መሪዎች በተገኙበት ተመረቀ።
  • በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በ30 ቢሊዮን ዶላር ሜጋ ፕሮጀክቶች እንደሚጀመሩ አስታወቁ።
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዳሴው ግድብ ምረቃ ላይ ባደረጉት ንግግር ግድቡ ለጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ሆኖ የሚቆይ ነው አሉ።
  • የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምህንድስና ምኞት ብቻ ሳይሆን አፍሪካ እጣ ፈንታዋን እንደምትወስን ደማቅ ማረጋገጫ ነው ብለዋል።
  • የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ በበኩላቸው ግድቡ የዓድዋ ድል ተምሳሌት በምህንድስና ጥበብ ዳግም ተገልጦ ነው ሲሉ አሞካሽተዋል።
  • የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ 233 ቢሊየን ብር ወጥቶበታል።