ቲክቶክ ለሕጻናት ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ቪዲዮዎችን እንደሚገፋ አንድ ሪፖርት አመለከተ

የቲክ ቶክ አልጎሪዝም ልቅ ወሲቦችን እና በጣም ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን ቪዲዮዎች በልጆች ወደተከፈቱ አካውንቶች እንደሚገፋ የሰብዓዊ መብት ዘመቻ ቡድን ባወጣው አዲስ ሪፖርት ጠቆመ።

ተመራማሪዎች ሐሰተኛ የልጆች አካውንቶችን ከፍተው የደህንነት ሴቲንጋቸውን ቢያስካክሉም ግልጽ የሆኑ የወሲብ ይዘት ያላቸውን ቪዲዮዎች እንዲመለከቱ እንደሚመጣላቸው ተናግረዋል።

እንዲመለከቷቸው በቲክቶክ ከመጡላቸው ቪዲዮዎች መካከል ግልጽ የወሲብ ግንኙነትን ሲፈጸም የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ጨምሮ ወደ ሌሎች ወሲባዊ ይዘት ወዳላቸው ቪዲዮዎች የሚመሩ ናቸው።

ቲክቶክ ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ እና ከእድሜ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ቪዲዮዎች ለማጋራት ቁርጠኛ መሆኑን እና ችግሩን ካወቀ በኋላ አፋጣኝ እርምጃ መውሰዱን ተናግሯል።

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ እና በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ግሎባል ዊትነስ የተባለ የተመራማሪዎች ቡድን የ13 ዓመት ታዳጊዎችን በማስመሰል በቲክ ቶክ ላይ አራት አካውንቶችን ከፍቷል።

የተወለዱበትን ቀን አሳስተው የሞሉት እነዚህ ተመራማሪዎች ማንነታቸውን ለማረጋገጥ ሌላ መረጃ እንዲሰጡ አልተጠየቁም።

የልቅ ወሲብ ፊልሞች

የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ልቅ የሆኑ የወሲብ ይዘቶችን ማየት የማይፈልጉ ከሆነ "የተገደበ ሁነታ" የሚለውን ሴቲንግ እንዲያበሩ ስለሚጠይቅ ያንን አድርገዋል።

እንደ ማኅበራዊ ድረገፁ ከሆነ ይህንን ሴቲንግ ያስተካከሉ ተጠቃሚዎች "ለአዋቂዎች የሚሆን ወይንም ውስብስብ ይዘት ያላቸውን ለምሳሌ. . . ወሲባዊ ስሜት ቀስቃሽ ይዘቶችን" ከማየት እንደሚገድብ ይናገራል።

ተመርማሪዎች ራሳቸው ምንም ዓይነት ፍለጋ ሳያደርጉ በመተግበሪያው "ሊወዱት ይችላሉ" በሚለው ክፍል ውስጥ ግልጽ ወሲባዊ ይዘት ያላቸው የፍለጋ ቃላትን ሲያቀርብላቸው ነበር።

እነዚያ የፍለጋ ቃላት ሴቶች ራሳቸውን በራሳቸው ማርካትን ወደሚያሳዩበት ቪዲዮዎች እንደመራቸውም ተናግረዋል።

በሌሎች ቪዲዮዎች ላይ ደግሞ ሴቶች ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ የውስጥ ሱሪያቸውን ሲያሳዩ ወይም ጡታቸውን ሲያጋልጡ ይታያል።

በጣም ጽንፍ በወጣ መልኩ ልቅ የሆነ ወሲብ ሲፈጸም የሚታይባቸው ቪዲዮዎችን መመልከታቸውንም ተናግረዋል።

እነዚህ ቪዲዮዎች የይዘት እገዳን ለማለፍ በተሳካ ሁኔታ በሌላ ምንም ተመሳሳይ ይዘት በሌላቸው ቪዲዮዎች ውስጥ ተደብቀው ገብተዋል።

የግሎባል ዊትነሷ ተመራማሪ አቫ ሊ ግኝቱ ለተመራማሪዎች "በጣም አስደንጋጭ" እንደሆነ ተናግራለች።

"ቲክ ቶክ ልጆች ተገቢ ያልሆነ ይዘት ያላቸውን ቪዲዮዎች እንዳያዩ መከልከል አለመቻል ብቻ ሳይሆን አካውንት እንደከፈቱ እንዲያዩ ያቀርብላቸዋል።"

ግሎባል ዊትነስ ስለ ሰብዓዊ መብቶች፣ ዲሞክራሲ እና የአየር ንብረት ለውጥ በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ግዙፍ ቴክኖሎጂዎች ምን ያህል ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ምርምር የሚያደርግ ቡድን ነው።

ተመራማሪዎች በዚህ ዓመት በሚያዝያ ወር ሌሎች ጥናቶችን ሲያካሂዱ ይህንን ችግር ማስተዋላቸውን ተናግረዋል።

ቪዲዮዎቹ ተነስተዋል

ተመራማሪዎቹ ግኝታቸውን ለቲክቶክ እንዳሳወቁ ችግሩን ለመፍታት አፋጣኝ እርምጃ መውሰዱን ተናግሯል።

ነገር ግን ባለፈው ዓመት በሐምሌ እና ነሐሴ ወር መገባደጃ ላይ ቡድኑ ተመሳሳይ አካውንቶችን የከፈተ ሲሆን መተግበሪያው ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን ቪዲዮዎች አሁንም ወደ ልጆች እንደሚገፋ ደርሰውበታል።

ቲክ ቶክ የታዳጊዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የተዘጋጁ ከ50 በላይ መንገዶች እንዳሉት ተናግሯል።

"ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ከእድሜያቸው ጋር የሚስማሙ ቪዲዮዎችን ለማቅረብ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነን" ብሏል።

መተግበሪያው መመሪያዎቹን ከጣሱ 10 ቪዲዮዎች ዘጠኙን ከመታየታቸው በፊት እንደሚያነሳቸው ተናግሯል።

ግሎባል ዊትነስ ግኝቶቹን በሚያቀርብበት ወቅት ቲክቶክ "መመሪያዎቻችንን የሚጥሱ ይዘቶችን ለማንሳት እና የፍለጋ ጥቆማ ባህሪያት ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ" እርምጃ እንደወሰደ ተናግሯል።

ታዳጊዎችን የሚከላከሉ ሕጎች

ባለፈው ዓመት ሐምሌ 25 ላይ ታዳጊዎችን የሚከላከሉ የኦንላየን ደህንነት ሕጎች በሥራ ላይ ውለው በኦንላየን ላይ ልጆችን ለመጠበቅ ሕጋዊ ግዴታን አስቀምጧል።

መተግበሪያዎች አሁን ልጆች የወሲብ ምስሎችን እንዳያዩ ለማስቆም "በጣም ውጤታማ የዕድሜ ማረጋገጫ" መጠቀም አለባቸው።

ራስን መጉዳት፣ ራስን ማጥፋትን ወይም የአመጋገብ መዛባትን የሚያበረታታ ይዘትን ለማገድ ቀመሮቻቸውን ማስተካከል ይኖርባቸዋል።

ግሎባል ዊትነስ ሁለተኛውን የምርምር ፕሮጀክቱን ያከናወነው የሕፃናት ሕጎች ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ነው።

ከግሎባል ዊትነስ የመጣችው አቫ ሊ "በኦንላየን ላይ የልጆችን ደህንነት መጠበቅ እንዳለብን ሁሉም ይስማማሉ… ተቆጣጣሪዎች ወደ ሥራ የሚገቡበት ጊዜ አሁን ነው።"

በምርምር ሥራቸው ወቅት፣ ተመራማሪዎች ሌሎች ለሚቀርብላቸው የወሲባዊ ይዘት ያላቸው ቪዲዮዎች አማራጭ ተጠቃሚዎችን የሚሰጡትን ምላሽ ተመልክተዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ "አንድ ሰው ምን እንዳለ ሊያስረዳኝ ይችላል?" ሲል ጽፏል።

ሌላው ደግሞ "ይህ መተግበሪያ ያለበት ችግር ምንደን ነው?"