የምግብ ሱስ አለ? ምን ዓይነት ምግቦች ሱስ ሊሆኑ ይችላሉ?

ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ አንዳንድ በተለይም ጣዕማቸውን በምንወዳቸው ምግቦች ሱሰኛ ልንሆን ሰለመቻላችን ጥናት ሲደረግ ቆይቷል።

ለምሳሌ ስኳር ሱስ እንደሚያስይዝ ሰምተው ይሆናል።

ለመሆኑ ሳይንስ ስለምግብ ሱስ ምን ይላል?

ሱስ በንጥረ ነገሮች (እንደ አልኮል ወይም ካናቢስ ያሉ) ወይም በልማድ እና በባህሪ (እንደ ቁማር ያሉ) ላይ ሊያተኩር ይችላል።

በአልኮል እና በዕጽ ሱስ ላይ በማተኮር የአሜሪካ የሥነ አዕምሮ ሕክምና ማኅበር ለምርመራ የሚሆን መስፈርት በዝርዝር ያስቀምጣል።

እነዚህም የማኅበራዊ ግንኙነት መበላሸት እና የምንጠቀመውን ፍጆታ መጠንን ቁጥጥር አለመኖርን ያካትታሉ።

የምግብ ሱሰኝነት ከዕፅ ሱስ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ተመልክቷል። ለምሳሌ በጣም በሚወደዱ ምግቦች ምክንያት ራስን መቆጣጠር አለመቻል ወይም ምግብ የመመገብ ከፍተኛ ፍላጎት መነቃቃት ይኖራል።

እንደ ከፍተኛ መጠን ያለው ሶዲየም ወይም ቅባት ያላቸው ምግቦችን ከሌሎች በበለጠ እንደምንወዳቸው በዚህ መንገድ እንገልፃለን።

አንጎል ደግሞ ለአደገኛ ዕጾችም ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ሊሠራ ይችላል።

ችግር ያለበት ምርመራ

የምግብ ሱስ ጽንሰ-ሐሳብ ብዙ ጥያቄዎች ይጭራል። አንደኛው ደግሞ መብላት ፊዚዮሎጂካል (በሕይወት ለመቆየት የሚደረግ) በመሆኑ ተገቢ የሆነውን እና ያልሆነውን መለየት ውስብስብ ሊሆን ይችላል የሚል ነው።

በሌላ በኩል ምግብን እንደ ዕጾች ማስወገድ የሚቻል አይደለም። ምክንያቱም ለመኖር መብላት አለብን።

በተጨማሪም ደግሞ የምግብ ሱስ ብዙውን ጊዜ እንደ ውፍረት፣ ከመጠን በላይ የመመገብን ወይም ቡሊሚያ [ከመጠን በላይ የመብላት በሽታ] ከመሳሰሉት ሌሎች ችግሮች ጋር ይደባለቃል። እነዚህን ችግሮች ደግሞ በሕክምና መለየት አስቸጋሪ ነው።

አንድ ሰው የምግብ ሱስ ሊያዳብር እንደሚችል ካሰብን፤ በሽታውን ማከም ይቻላል ብሎ ማሰቡም ምክንያታዊ ይመስላል።

የአሜሪካ የሥነ አዕምሮ ሕክምና ማኅበር መስፈርት መሠረት የምግብ ሱስ እንደ ችግር አይቆጠርም። ለሱስ ከሚደረገው የተለየ የምርመራ መስፈርቶችም የሉትም።

ከአሜሪካ የሥነ-አእምሮ ሕክምና ማኅበርም በተጨማሪ የዓለም ጤና ድርጅትም እንደ ችግር አይቆጥረውም።

ታዲያ እንዴት ልንታከም/ድጋፍ ልናገኝ እንችላለን?

ለዚህ ዋናው መሳሪያ የሚሆነው ከጥቂት ዓመታት በፊት በየል ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ዋይኤፍኤኤስ ተብሎ የሚጠራው የሳይኮሜትሪክ መስፈርት ነው።

ከዚያን ወዲህ የምግብ ሱስን ለመለየት እና ለመመርመር በብዛት ጥቅም ላይ የዋለው ይህ ዘዴ ነው።

የሚደግፉ ሐሳቦች

አንዳንድ የሱስ ባህሪያት በምግብ አወሳሰድ ላይም ያሉ ይመስላሉ።

ለምሳሌ ከመጠን በላይ ወፍራም የሆኑ ሰዎች ይህ ለጤና ችግር እንደዳረጋቸው ቢያውቁም የሚበሉትን የምግብ መጠን መቆጣጠር የማይችሉ ሰዎች አሉ። ይህ ደግሞ በአደገኛ ዕፅ ሱሰኞች ላይ ከሚከሰተው ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው።

በማዕከላዊ ነርቭ ላይ በማተኮር የምግብ ሱስ በአንጎል ላይ የሚያደርሱትን ለውጦችን ለመመልከት ችለዋል። ለምሳሌ በአደንዛዥ እፅ ሱስ ውስጥ ባሉ ሰዎች አንጎል ላይ ለውጦች ተለይተዋል።

በተለይም በሁለቱም ጊዜ በማዕከላዊው የነርቭ ስርዓት ላይ ለውጦች አሉ።

በዚህ ክፍል ያለው የዶፓሚን መጠን መለዋወጥ እንደ ምግብ ወይም ዕጽ የመሳሰሉ የመፈለግ ስሜታችንን ሊያበረታታ ይችላል።

ሌላኛው ሐሳብስ

በምግብ ሱስ ላይ የተካሄደው አብዛኛው ምርምር እንደ አይጥ ባሉት እንስሳት ላይ ነው።

በእነዚህ ጥናቶች ለአንድ ወይም ለሌላ የምግብ አይነት ስላለሚሆነው ነገር መግለጹ አነስተኛ ነው። ይህ በእውነተኛ ህይወት የማይከሰት ነገር ነው። በበለጸጉ ማህበረሰቦች ዘንድ የሰው ልጅ በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም አይነት ምግብ ማግኘት ይችላል።

ሁለተኛው ነገር የምግብ ሱሰኝነት ከሌሎች መዛባቶች (በተለይም ከመጠን በላይ የመብላት ችግር) ጋር መደራረቡ ችግሩን ለብቻው ለመለየት በጣም ከባድ ያደርገዋል። ለምሳሌ ከመጠን ያለፈ የአመጋገብ ችግር ያለባቸው እና የምግብ ሱስ ያለባቸው ሰዎች በዋጥኤፍኤኤስ ምዘና ተመሳሳይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በመጨረሻም ደግሞ ችግሩ የምግቡ ወይም የመብላት ስለመሆኑ ምንም ስምምነት የለም። ይህም ችግሩን ጽንሰ-ሃሳብ የበለጠ ያወሳስበዋል።

የስኳር ሱስስ?

የስኳር ሱስ እንዳለብን ከአንድ ጊዜ በላይ ሰምተው ይሆናል። ይህ የምግብ ሱስ ንዑስ አካል ዓይነት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

ከፍተኛ የስኳር ይዘት ያላቸውን እና በባህሪው ምክንያት ሱስ ስለሚያሲዙ እጅግ በጣም የተቀነባበሩ ምግቦችን ከመጠን በላይ መጠቀምን ያካትታል። ይሁን እንጂ በሰዎች ላይ እንደአደገኛ ዕጽ በአንጎል ደረጃ ላይ ስለመሥራቱ ግልጽ አይደለም።

ከስኳር ጉዳይ ጋር በተገናኘ አንዳንድ ጥናቶች የቸኮሌት ወይም የፈጣን ምግብ ሱስ ሊኖር ይችላል ስለመቻሉ ተመልከተዋል። በዚህ ረገድ ግን ገና ብዙ የሚጠኑ ነገሮች አሉ።

ማጠቃለያ

ምንም እንኳን በምግብ ላይ የሆነ ነገር እየተከሰተ እንዳለ ግልጽ በምግብ አወሳሰድ ላይ ስላለው ሱሰኝነት ግን አሁንም በምርምር ሊገለጹ የሚገባቸው ብዙ ብዥታዎች አሉት። ዛሬ ቢያንስ በሕክምና ደረጃ አሻሚ ቃል ነው።

አንዳንድ ምግቦች ከሌሎች የምንመርጠው ሰዎች ሁሉ የምንጋራው እና የተማርነው ነገር ነው።

ማወቅ ያለብን ለምን አንዳንድ ምግቦችን መውሰድ ለተወሰኑ ሰዎች በጣም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል የሚለው ነው። ከዚያ በኋላ ብቻ እነዚህን ችግሮች መከላከል እና በዚህ የሚሠቃዩትን ሰዎች መርዳት የምንችለው ማለት ነው።