ራሽፈርድ አዲስ ውል የሚፈርመው መቼ ነው? የቡካዮ ሳካ ውልስ ለምን አጭር ሆነ?

የማንቸስተር ዩናይትዱ አሠልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ የ25 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ በቅርቡ ፊርማውን እንደሚያራዝም ይጠብቃሉ።

የማርከስ ራሽፈርድ ውል በሚቀጥለው የውድድር ዓመት መገባደጃ ላይ ይጠናቀቃል ሲል ማንቸስተር ኢቭኒንግ ፅፏል።

ሰንደይ ሚረር ደግሞ ሪያል ማድሪድ እንግሊዛዊውን አማካይ እንደሚያስፈርም እርግጥ ነው ብሏል።

የቦሩሲያ ዶርትመንዱ ጁድ ቤሊንግሃም በጠቅላላ ዋጋ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ስፔን ክለብ ያቀናል ተብሎ ይጠበቃል።

በቅርቡ ወደ ክለቡ የሚመጡት አዲሱ የቼልሲ አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲንሆ ቤልጂየማዊውን አጥቂ ማየት እንደሚፈልጉ የጣልያኑ ዴሎ ስፖርት ዘግቧል።

በውሰት ወደ ኢንተር ሚላን ያቀናው ሮሜሉ ሉካኩ ጣሊያን መቆየት ቢሻም ፖቼቲንሆ አጥቂውን መገምገም ይሻሉ።

በሌላ ጭምጭምታ ቼልሲ የስፖርቲንግ ሊዝበኑን የተከላካይ አማካይ ለማስፈረም ተቃርቧል።

ኤክስፕረስ እንዳስነበበው የ22 ዓመቱ ኡራጓያዊ ማኑዌል ኡጋርቴ በቼልሲ ብቻ ሳይሆን በሊቨርፑልም ይፈለጋል።

ሊቨርፑል ከዚህ ተጨዋች በተጨማሪ የዎልቭስ አማካይ ሩበን ኔቬስን ዜና በቅርበት እየተከታተለ ነው።

የ30 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ ከዎልቭስ ጋር ያለው ውል እየተጠናቀቀ ሲሆን፣ ስሙ ከባርሴሎና ጋር በተደጋጋሚ እየተነሳ ነው።

አስተን ቪላ፣ ኒውካስል፣ ቶተንሃም እና ሮማ ደግሞ ሌላኛውን የዎልቭስ ተጫዋች ለማስፈረም አቆብቁበዋል።

ሰንደይ ሚረር እንደዘገበው ሁዋንግ ሂ-ቻን በሚመጣው የዝውውር መስኮት ለሽያጭ ሊቀርብ ይችላል።

አትሌቲክ የተሰኘው ድረ-ገፅ እንደዘገበው ደግሞ ቶተንሃም እስራኤላዊውን አጥቂ ከፉልሃም ለማምጣት ፍላጎት አለው።

ማኖር ሶሎሞን ከዩክሬኑ ሻክታር ዶኔትስክ በውሰት ለፉልሃም እየተጫወተ ሲሆን ሻክታር ከፊፋ ባገኘው ፈቃድ መሠረት ተጫዋቹን አሳልፎ መስጠት ይችላል።

ሌላኛው የለንደን ክለብ አርሰናል የ22 ዓመቱ ፈረንሳዊ ተከላካይ ሻሻ ቦይን ከጋላታሳራይ ማምጣት ይፈልጋል።

መድፈኞቹ ኮከቡ አጥቂያቸው ቡካዮ ፊርማውን ሲያራዝም የውል ማፍረሻ አንቀፅ ማስገባት እንዳልፈለጉ ተሰምቷል።

የ21 ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ብዙዎች እንደጠበቁት የረዥም ጊዜ ውል አልገባም። ሜይል እንደዘገባው አዲሱ ውል በክለቡ እስከ 2027 የሚያቆየው ነው።

በቅርቡ ወደ ፕሪሚዬር ሊግ ያደገው በርንሊ የሊቨርፑሉን አማካይ ፋቢዮ ካርቫልሆን በውሰትም ይሁን በቋሚነት ማምጣት ይሻል።

የ28 ዓመቱ ዲቮክ ኦሪጊ ኤሲ ሚላንን ለቆ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መምጣት ቢፈልግም የቱርክ ክለቦች ዐይናቸውን እንደጣሉበት የጣልያን ጋዜጦች ጽፈዋል።