ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ዕውቁ ሴኔጋላዊ ቲክቶከር ካቢ ላሜ የጣልያን ዜግነት ተሰጠው
ዕውቁ ሴኔጋላዊ የቲክቶክ ኮከብ ካቢ ላሜ የጣልያን ዜግነት ተሰጠው።
በቲክቶክ ላይ በተከታዮች ብዛት ቁጥር አንድ ነው።
የ22 ዓመቱ ካቢ ከልጅነቱ ጀምሮ ጣልያን ቢኖርም የጣልያን ዜግነት የተሰጠው ገና አሁን ነው።
ትውልደ ሴኔጋላዊው ካቢ ላሜ በቲክቶክ 148 ሚሊዮን ተከታዮች አሉት።
አሁንም የሴኔጋል ፓስፖርት ያለው ሲሆን፤ የጣልያን ዜግነት ስለተሰጠው “ኩራት እንደሚሰማው” ለመገናኛ ብዙኃን ተናግሯል።
የጣልያን ዜግነት ከማግኘት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ብሔራዊ ቃል የመግባት ሥነ ሥርዓት በመፈጸሙ ለአገሪቱ “ትልቅ ኃላፊነት” እንደሚሰማውም አክሏል።
ለዓመታት ጣልያን የኖረው የቲክቶክ ኮከብ ገና ባለፈው ሳምንት የጣልያን ዜግነት ቢሰጠውም፣ “ሁሌም ጣልያናዊ እንደሆንኩ ይሰማኛል” ብሏል።
ስሜቱ ዜግነቱን ከማግኘቱ በፊትም እንደነበረና ዜግነቱን ካገኘ በኋላ ስሜቱ እንዳልተለወጠ ገልጿል።
ዝነኛው ቲክቶከር
አሁን የቲክቶክን መንደር በተከታዮች ብዛት በበላይነት የሚመራው ትውልደ ሴኔጋላዊው ካቢ ላሜ ነው።
የ22 ዓመቱ ወጣት በቲክቶክ ላይ ቃል ሳያወጣ፣ በአካል እንቅስቃሴ ብቻ ትዝብቱን በማጋራት አሜሪካዊ ቲክቶከሮችን በልጦ የመተግበርያው ማማ ላይ ተቀምጧል።
ከዚህ ቀደም የአንደኝነቱ መንበር ተይዞ የነበረው በቻርሊ ዲ አሚሊዮ ነበር።
ላሜ በአሁን ሰዓት 142.8 ሚሊዮን ተከታዮች ሲኖሩት፣ ዲ አሚሊዮ ደግሞ 142.3 ሚሊዮን ተከታዮች በመያዝ ይከተላል።
በ2020 ኅዳር ላይ ዲ አሚሊዮ 100 ሚሊዮን ተከታዮችን በማስከተል የቲክቶክ መንደር አጋፋሪ ሆኖ ነበር።
ላሜ ወደ ቲክቶክ አምባ የተቀላቀለው በሚኖርባት ጣልያን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እግር ተወርች ተይዛ ማጣፍያው ባጠራት ወቅት ነበር።
በወቅቱ ዓለም ለኮሮናቫይረስ ወረርሽን እጇን ስትሰጥ ካቤ ከሥራው ተሰናበተ። እናም በሩን ዘግቶ ሞባይሉን አነሳ።
በተዘጋው የመኝታ ቤቱ ክፍል ውስጥ ቲክቶክ እጁን ዘርግቱ ተቀበለው።
ሰዎች ነገሮችን ሲያወሳስቡ ሲመለከት በቀላሉ እንዴት መከወን እንደሚቻል እጁን በመጠቆም ቃል ሳያወጣ በማሳየት ዝናን አጋበሰ።
ዛሬ የቲክቶክ መንደር ሰዎች ስሙን አንስተው የማይጠግቡት፣ የሠራው ሁሉ በአዕላፍ የሚታይለት፣ በዓለም አቀፉ ድግስ ላይ የሚጋበዝ ቱጃር ወጣት ነው።አሁን የቲክቶክን መንደር በተከታዮች ብዛት በበላይነት የሚመራው ትውልደ ሴኔጋላዊው ካቤ ላሜ ነው።
የ22 ዓመቱ ወጣት በቲክቶክ ላይ ቃል ሳያወጣ፣ በአካል እንቅስቃሴ ብቻ ትዝብቱን በማጋራት አሜሪካዊ ቲክቶከሮችን በልጦ የመተግበርያው ማማ ላይ ተቀምጧል።
ከዚህ ቀደም የአንደኝነቱ መንበር ተይዞ የነበረው በቻርሊ ዲ አሚሊዮ ነበር።
ላሜ በአሁን ሰዓት 142.8 ሚሊዮን ተከታዮች ሲኖሩት፣ ዲ አሚሊዮ ደግሞ 142.3 ሚሊዮን ተከታዮች በመያዝ ይከተላል።
በ2020 ኅዳር ላይ ዲ አሚሊዮ 100 ሚሊዮን ተከታዮችን በማስከተል የቲክቶክ መንደር አጋፋሪ ሆኖ ነበር።
ላሜ ወደ ቲክቶክ አምባ የተቀላቀለው በሚኖርባት ጣልያን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እግር ተወርች ተይዛ ማጣፍያው ባጠራት ወቅት ነበር።
በወቅቱ ዓለም ለኮሮናቫይረስ ወረርሽን እጇን ስትሰጥ ካቤ ከሥራው ተሰናበተ። እናም በሩን ዘግቶ ሞባይሉን አነሳ።
በተዘጋው የመኝታ ቤቱ ክፍል ውስጥ ቲክቶክ እጁን ዘርግቱ ተቀበለው።
ሰዎች ነገሮችን ሲያወሳስቡ ሲመለከት በቀላሉ እንዴት መከወን እንደሚቻል እጁን በመጠቆም ቃል ሳያወጣ በማሳየት ዝናን አጋበሰ።
ዛሬ የቲክቶክ መንደር ሰዎች ስሙን አንስተው የማይጠግቡት፣ የሠራው ሁሉ በአዕላፍ የሚታይለት፣ በዓለም አቀፉ ድግስ ላይ የሚጋበዝ ቱጃር ወጣት ነው።
ለምን ዝነኛ ሆነ?
የ22 ዓመቱ ወጣት ካቢ ቲክቶክን መጠቀም የጀመረው በመጋቢት ወር 2020 ነው፤ ኮሮናቫይረስ ዓለምን በተዋወቀበት ጊዜ እርሱ ቲክቶክን ተዋወቀ።
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ክፉኛ በደቆሰበት ወቅት እርሱም ከሚሠራበት ፋብሪካ ተሰናበተ። ካቢ በቀጥታ ወደ ቤተሰቦቹ አመራ።
ሌላ ሥራ ይፈልጋል ተብሎ ሲጠበቅ እርሱ ግን በየቀኑ ቲክቶክ ላይ ቪዲዮዎችን መለጠፍ ጀመረ።
ታዲያ ያኔ የቲክቶክ አካውንቱ ላይ ፈገግ የሚያሰኙ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ሲያጋራ እንዲህ በአንድ ጊዜ ስሜ በመላው ዓለም ይናኛል፤ ተግባሬ ብዙዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ብሎ ያሰበ አይመስልም።
ተንቀሳቃሽ ምስሎቹ የሚያተኩሩት እንዴት ሰዎች ያለምንም ተጨባጭ ምክንያት ነገሮችን እንደሚያወሳስቡ በማሳየት ነው።
እርሱ እንደሚለው በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎች የእርሱን ቪዲዮዎች የወደዱት ሳቅን በሚያጭረው የፊት ገጽታው የተነሳ ስለሚያስቃቸው ነው።
ሌላው ደግሞ የእርሱን ሐሳብ ለመረዳት ቋንቋ ማወቅ ወይንም መናገር ፈጽሞ አለመጠየቁ እንደሆነ ያስረዳል።
ካቢ የእግር ኳስ አድናቂ ሲሆን በቪዲዮዎቹ ላይ የስፖርት ክለብ ቲሸርቶችን ለብሶ ይታያል።
የጁቬንተስ ደጋፊ የሆነው ካቢ፣ ኤዲ መርፊ እና ዊል ስሚዝም ከሚያደንቃቸው የሆሊውድ ከዋክብት መካከል ናቸው።