የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች ግምት፡ ሲቲ በዚህ ሳምንት የዋንጫ ባለቤት ይሆናል? እነ ማን ይወርዳሉ?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
እርግጥ ነው ሌይስተር ሲቲ በፈረንጆቹ 2016 የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን አንስቷል። ዘንድሮ ግን ከፕሪሚዬር ሊጉ ተሰናባች ይመስላሉ።
ሰኞ ዕለት ከኒውካስትል የሚጫወቱት ቀበሮዎቹ ውጤት ካልቀናቸው ኃያሉን ሊግ በእንባ ሊሰናበቱ ይገደዳሉ።
ይህን ጨዋታ ጨምሮ ሌሎች የቅዳሜ እና የእሑድ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ግጥሚያዎችን ግምት ክሪስ ሱቶን እንዲህ አስቀምጧል።
ቅዳሜ
ቶተንሃም ከ ብሬንትፈርድ
ምንም እንኳ ቶተንሃም ያደረጋቸውን ያለፉት ሦስት ጨዋታዎችን በትክክል ብገምትም በዚህ ጨዋታ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም።
ቶተንሃም በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ መሳተፍ ይፈልግ ይሆን? ሰባተኛ ሆነው ካጠናቀቁ የሚገጥማቸው ዕጣ ይሄ ነው።
ቁማር ተጫውተሃል ተብሎ ከእግር ኳስ መታገዱን ተከትሎ ብሬንትፈርድ ያለ ኢቫን ቶኒ ነው ወደ ሜዳ የሚገባው።
ግምት፡ 2 - 2
ቦርንመዝ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
የውድድር ዘመኑ ሲጀመር ማንቸስተር ዩናይትድ እንኳን የካራባዎ ዋንጫን እና ሦስት ጨዋታ እየቀረው ለአራተኛ ደረጃ ይፋለማል ብሎ ያሰበ አልነበረም።
አልፎም በኤፍ ኤ ዋንጫ ፍፃሜ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ሊፋለም እየተዘጋጀ ይገኛል።
ምንም እንኳ ቦርንመዝ ከመውረድ አደጋ ቢተርፉም ለማንቸስተር ዩናይትድ ይተኛሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም።
ነገር ግን በዚህ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸንፋል ብዬ አስባለሁ። ዩናይትድ ከመጨረሻዎቹ ሦስት ጨዋታዎች ሁለቱን ካሸነፈ በሚቀጥለው ዓመት በቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር እናየዋለን።
ግምት፡ 1 - 2

ፉልሃም ከ ክሪስታል ፓላስ
የፓላሱ አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሃ በጉዳት ምክንያት በዚህ ጨዋታ አይሳተፍም። ነገር ግን ኤቤሬቺ ኤዜ ጥሩ አቋም ላይ መገኘቱ ለፓላስ መልካም ዜና ነው።
ቢሆንም ይህን ጨዋታ ፉልሃም ያሽንፋል የሚል ግምት አለኝ። ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሌይስተርና ሳውዝአምፕተንን የረቱት ፉልሃሞች ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ ዕድል ይቀናቸዋል ብዬ አስባለሁ።
ግምት፡ 2 - 1
ሊቨርፑል ከ አስተንቪላ
ኡናይ ኤሜሪ ወደ አንፊልድ አቅንተው የየርገን ክሎፕ ቡድንን ይፈትናሉ የሚል እምነት አለኝ። ምንም እንኳ ለአስተን ቪላ ጥሩ ግምት ብሰጥም ሊቨርፑል ያለፉትን ሰባት ጨዋታዎች አሸንፎ በዚህኛው ድል ይርቃቸቀዋል ብዬ አላስብም።
ሊቨርፑል በመጨረሻው ጨዋታው ከሳውዝአምፕተን ይገናኛል። ይህ ማለት አራተኛ ሆኖ ለማጠናቀቅ ማንቸስተር ዩናይትድ አሊያም ኒውካስትል በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች ነጥብ መጣል አለባቸው።
ግምት፡ 3 - 1
ዎልቭስ ከ ኤቨርተን
ኤቨርተን የመጨረሻው ከሜዳ ውጭ የሚያደርገውን ጨዋታ አጥቂው ካልቨርት ሌዊን ሳይሰለፍ ሊያደርግ ይችላል።
ኤቨርተን ከብራይተን ጋር በነበረው ጨዋታ 5 ለ 1 ሲረታ በተጫዋቹ እየተመራ ነበር።
ነገር ግን ዎልቭስም በቀላሉ ይበገራል ብዬ አላምንም። ለዚህ ነው ይህ ጨዋታ አቻ ይጠናቀቃል የሚል ግምት ያለኝ።
ግምት፡ 1 - 1

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ አርሰናል
አርሰናሎች ዋንጫውን ቻው ቻው ያሉት ይመስላል። በተለይ ደግሞ ባለፈው በሜዳቸው በብራይተን ሲረቱ ነው ሕልማቸው የጨለመው።
የውድድር ዘመኑ እየተገባደደ ሲመጣ አርሰናሎች ጠንካራ አቋማቸውን ማሳየት ሲገባቸው በተቃራኒው ወደኋላ አፈግፍገዋል።
ኖቲንግሃም የደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ከሚገኙበት ሥፍራ አንፃር ለአርሰናል ይተኛሉ ተብሎ አይታሰብም።
ግምት፡ 1 - 1
እሑድ
ዌስትሃም ከ ሊድስ ዩናይትድ
ዌስትሃም ለጊዜው ከመውረድ አደጋ ተርፏል። ሌይስተር እና ሳውዝአምፕተን አይደርሱባቸውም። ሊድስ ከዌስትሃም እኩል ነጥብ ይዘው ሊጨርሱ ይችላሉ።
ምንም እንኳ ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አራቱን ቢረቱም የዴቪድ ሞዬስ ትኩረታቸውን ለአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ አድርገው ለፍፃሜ በቅተዋል።
ሊድሶች በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከሜዳ ውጭ ካደረጓቸው ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ ነው በድል ያጠናቀቁት።
ግምት፡ 0 - 0
ብራይተን ከ ሳውዝአምፕተን
ሳውዝአምፕተን ከፕሪሚዬር ሊግ መውረዳቸውን አረጋግጧል። ስለዚህ ከብራይተን ጋር አንገት ለአንገት ይተናነቃሉ የሚል እምነት የለኝም።
አሁን ጥያቄው የሳውዝአምፕተን መጨረሻ ምን ይሆናል የሚለው ነው። አሠልጣኙ አብረዋቸው ይቀጥላሉ ወይስ ይለቃሉ? እንደ ዋርድ-ፕራውዝ ያሉ ተጨዋቾችስ ዕጣ ፈንታ?
ግምት፡ 2 - 0

ማንቸስተር ሲቲ ከ ቼልሲ
ማንቸስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ለመድረስ ያደረጉትን ፍልሚያ ኢቲሃድ ተገኝቼ ተመልክቻለሁ። ሲቲ ደንቅ ነበር።
አርሰናል በፎረስት ከተሸነፈ ማንቸስተር ሲቲ ቅዳሜ ዕለት የሊጉ ባለድል መሆኑን ያረጋግጣሉ። ነገር ግን የፈለገው ቢሆን በሜዳቸው ቼልሲን ከመረምረም ይመለሳሉ ብዬ አላስብም።
ቼልሲ፤ መለያ ቀለምም ሆነ ዕቅድ ያለው ቡድን አይደለም። ምንም እንኳ አስደናቂ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች ቢካተቱም ቡድን ሆነው ሲጫወቱ አላየንም።
ማንቸስተር ሲቲ እንደ ፎደን፣ ማህሬዝ እና ጁሊያን አልቫሬዝ ያሉ ተጫዋቾችን አሰልፎ ግጥሚያውን በድል ያጠናቅቃል እላለሁ።
ግምት፡ 5 - 0
ኒውካስትል ከ ሌይስተር
ሌይስተር በደረጃ ሰንጠረዡ ከግማሽ በታች ካሉ ክለቦች የተሻለ ጎል ያለው ነው። አልፎም ስምንተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው አስተን ቪላ በላይ ጎል አስቆጥሯል።
ምንም እንኳ ቀበሮዎቹ ድንቅ አጥቂዎችን ቢይዙም የተከላካይ መሥመራቸው እጅግ ደካማ ነው። ጆኒ ኢቫንስ ከጉዳት ቢመለስም ቡድኑን መታደግ አልቻለም።
ለዚህ ነው በሚቀጥለው ዓመት በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ እየተፋለመ ያለውን ኒውካስትልን ይገዳደራሉ ብዬ ማላስበው።
ግምት፡ 3 - 1












