ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ፔሌ ያለፈባቸው የእግር ኳሱ ድንቅ ጊዜያት ሲታወሱ
በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ጎልተው ከሚታወሱት የኳስ ጠበብተኞች መካከል ቀዳሚው ፔሌ በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የሦስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ፔሌ፣ ጥቅምት ወር ላይ እዚህ በመድረሱ ደጋፊዎችን እና ፈጣሪን በሆስፒታል ውስጥ ሆኖ አመስግኖ ነበር።
በፈረንጆቹ 1940 በደቡብ ምሥራቅ ብራዚል ከድሃ ቤተሰብ የተወለደው ፔሌ፣ ድህነትን ከማሸነፍ በላይ በእግር ኳሱ የማይረሳ ታሪክ ጽፏል። ፔሌ ከሚታወስባቸው አይረሴ ክስተቶች መካከል የተወሰኑት በዚህ ቪዲዮ ተካተዋል።