ኒውካስል ከማንቸስተር ዩናይትድ እና የሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

29ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ እንዲካሄዱ መርሐ ግብር ወጥቶላቸዋል።

ኒውካስል ከማንቸስተር ዩናይትድ፤ አስቶን ቪላ ከቼልሲ እና ብራይተን ከአርሴናል ጋር የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ትልቅ ግምት ተሰጧቸዋል።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የእነዚህን ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው ገምቷል።

ማክሰኞ

በርንመዝ ከ ብሬንትፎርድ

ብሬንትፎርድ ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች አምስቱን አሸንፏል።

ዘንድሮ ሁለቱ ቡድኖች ሲገናኙም ብሬንትፊርድ አሸናፊ ለመሆን ችሏል።

በወቅቱ በርንመዝ በመጥፎ አቋም ላይ ነበረ ሲሆን አሁን አቋሙ በመሻሻል ላይ ይገኛል።

ይህንን ጨዋታ ባለሜዳዎቹ በአሸናፊነት ያጠናቅቃሉ።

ግምት፡ 2 - 1

ኤቨርተን ከ በርንሌይ

በርንሌይ በብሬትፎርድ በሦስት ጎል ከመመራት ተነስቶ አቻ ለመሆን ቢችልም የማታ የማታ ከሽንፈት አልዳነም።

ኤቨርተን በበኩሉ በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት ስድስት ቸዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻ ነው ማሳካት የቻለው።

ሰማያዊዎቹ በሳምንቱ መጨረሻ ኒውካስል ላይ ድል አስመዝግበዋል።

በተመሳሳይ መልኩ ከተጫወቱ በዚህ ጨዋታም ሦስት ነጥብ ማሳካት ይችላሉ።

ግምት፡ 2 - 0

ሊድስ ዩናይትድ ከ ሰንደርላንድ

ከወራጅ ዞን በስድስት ነትብ የሚርቀው ሊድስ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

ቡድኑ በሜዳው ጠናካራ ተፎካካሪ መሆኑን በማሳየት ላይ ይገኛል።

ሰንደርላንድ ላላፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ ባይችልም የግራኒት ዣካ ከጉዳት መመለስ ትልቅ መሳሳት ሆኖላቸዋል።

ጨዋተው ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት ቢሆንም ሊድስ በሜዳው ጠንካራ መሆኑን እያሳየ በመሆኑ ሦስት ነጥቡን የማሳካት ዕድል አለው።

ግምት፡ 1 - 0

ዎልቭስ ከ ሊቨርፑል

ሊቨርፑል ያለፉት ሦስት ጨዋታዎች በማሸነፍ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ መፎካከር ጀምሯል።

አርን ስሎት ቡድናቸውን ወደ ጠንካራ አቋም መለስ ቢችሉም ዎልቭስም ጥሩ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ጨዋታውን ሊቨርፑል እንደሚያሸንፍ ብገምትም ጠንካራ ፉክክር የሚከናወንበት ጨዋታ ይሆናል።

ግምት፡ 1 - 2

ረቡዕ

አስቶን ቪላ ከቼልሲ

አስቶን ቪላ በሚያሳየው ደካማ እንቅስቃሴ ምክንያት እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዞ የማጠናቀቅ ዕድሉ እየጠበበ ነው።

ቼልሲ በጥሩ አቋም ላይ ባይሆንም ትልቁ ችግሩ ጨዋታዎችን በ11 ተጫዋቾች ማጠናቀቅ አለመቻሉ እየሆነ መጧል።

አሸናፊውን ቡድን ለመለየት አስቸጋሪ በመሆኑ አቻ የሚለያዩ ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 - 1

ብራይተን ከ አርሴናል

አርሴናል ጥሩ መጫወት ባይችልም ጠንካራ የቡድን ጥልቀት አለው።

ከተቀያሪ ወንበር ተነስተው ጨዋታ መቀየር የሚችሉ ተጫዋቾችን ይዟል።

ብራይትን ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ቢያሸንፍም ይህን መርሐ ግብር በአርሴናል የበላይነት ይጠናቀቃል።

ግምት፡ 1 - 2

ፉልሃም ዌስት ሃም

የዌስት ሃሙ አሰልጣኝ ኑኖ ስፕሪንቶ ሳንቶ በቡድናቸው አቋም ቢደሰቱም በሊቨርፑል 5 - 2 ከመሸነፍ አልዳኑም።

በመጀመሪያው ዙር በፉልሃም የተሸነፉ ሲሆን ከዚህ ጨዋታም ነጥብ ማግኘት የሚችሉ አይመስለኝም።

የማርኮ ሲልቫ ቡድን ጥሩ ተጫውቶ ቶተንሃምን በሳምንቱ መጨረሻ ማሸነፍ ችሏል።

ግምት፡ 2 - 1

ማንቸስተር ሲቲ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ቪቶር ፔሬራ ፎረስትን ከመውረድ ለማዳን ቢቀጠሩም እስካሁን ሦስት ነጥብ ማሳካት አልቻሉም።

ኧርሊንግ ሃላንድ ከጉዳቱ ተመለሰም አልተመለሰም ሲቲ አሸንፎ ሦስት ነጥብ ያሳካል።

ፎረስት የተለያዩ አሰልጣኞችን እና አጨዋወት መከተሉ ለሽንፈቱ ሌላኛው ምክንያት ነው።

ግምት፡ 2 - 0

ኒውካስል ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ኒውካስል ወጥ ያልሆነ አቋሙን በተደጋጋሚ በማሳየት ላይ ይገኛል።

ዩናይትድም ቢሆን ከክሪስታል ፓላስ ጋር ጥሩ ባይሆንም ባገኘው ፍጹም ቅጣት ምት እና በፓላስ ተጫዋች ከሜዳ መባረር ተጠቅሞ አሸንፏል።

ቤንጃሚን ሼሽኮ ድንቅ አጥቂ መሆኑን እያሳየ ሲሆን ኒውካስሎች እሱን የማቆም ሥራ ይጠብቃቸዋል።

ይህ ጨዋታም በሁለቱ ቡድኖች መካከል ከታዩት ድንቅ ፍልሚያዎች አንዱ ይሆናል።

ግምት፡ 2 - 2

ሐሙስ

ቶተንሃም ከ ክሪስታል ፓላስ

ቶተንሃም በሜዳው ያስመዘገበው ውጤት ከዎልቭስ ብቻ የሚሻል ነው።

ቡድኑ በሜዳው ሲጫወት ያለው ድባብ ከባድ ሲሆን በዚህ ጨዋታ መሸነፍ ለቱዶር ነገሮችን ውስብስብ ያደርገዋል።

ክሪስታል ፓላስ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ጥሩ ቢንቀሳቀስም ከሽንፈት አልዳነም።

በዚህ ጨዋታ ስፐርስ እንደሚያሽንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 2 - 1