የእናቱን መኪና ያሽከረከረው የአራት ዓመቱ ሕፃን መነጋገሪያ ሆነ

በኔዘርላንድስ የእናቱን መኪና ያሽከረከረው የአራት ዓመት ሕፃን 'ፎርሙላ ዋን' በተሰኘው የመኪና ውድድር ላይ የመሳተፍ ተስፋ አለው ተብሏል።

በኔዘርላንድስ ዩትሬክት ከተማ ቅዳሜ ዕለት የእናቱን መኪና እንዳሽከረከረ የተነገረው ሕፃን ሁለት የቆሙ መኪኖችን ከገጨ በኋላ አከባቢውን ለቆ መሄዱን ፖሊስ ተናግሯል።

ሁኔታውን ሲመለከት የነበረ አንድ ሰው ሕፃኑ በቀዝቃዛ አየር ብቻውን ሲጓዝ ተመልክቶ ለፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ በኢንስታግራም ገጹ በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገልጾ ሕፃኑን "አዲሱ ማክስ ቪስታፕን" ሲል ገልጾታል።

ቪስታፕን እውቅ የፎርሙላ ዋን ተወዳዳሪ እና እንድ አውሮፓውያኑ በ2021 የዓለም ሻምፒዮን የነበረ ኔዘርላንዳዊ ስፖርተኛ ነው።

ሕፃኑ የአባቱን ወደ ሥራ መሄድ ተከትሎ የእናቱን የመኪና ቁልፍ ይዞ ወደ ተሽከርካሪው ሲያመራ "እየነዳ ብዙ ለመጓዝ አስቦ" ነበር።

ፖሊስ ሕፃኑን እንዲገኝ ተደውሎ ከተነገረው አከባቢ አቅራቢያ ሁለት የቆሙ መኪኖች ግጭት እንደደረሰባቸው ሪፖርት ተደርጓል።

ግጭቱን ያደረሰው የሕፃኑ እናት መኪና መሆኑ ከታወቀ በኋላ የፖሊስ መኮንኖች ለእናቱ የደወሉላት ሲሆን፣ እናቱን እንዲያወራ ስልኩን ሲሰጡት ስልኩን እንደተሽከርካሪ መሪ አድርጎ ለመዘወር ሲሞክር ተስተውሏል።

"ያንን ስንመለከት ሕፃኑ መኪናውን አሽከርክሮት ሊሆን ይችላል" ብለን ገመትን ብሏል ፖሊስ በኢንስታግራም ጽሑፉ።

የአራት ዓመቱ ሕፃን ከእናቱ ጋር ከመገናኘቱ በፊት በፖሊስ ጣቢያ ቆይታው ጣፋጭ ቸኮሌት እና አሻንጉለት ተበርክቶለታል።

ከዚያም በኋላ መኪናው እንዴት እንደሚነዳ ላሳያችሁ ብሎ የጠየቀ ሲሆን ከፖሊስ እና ከእናቱ ጋር ግጭቱ ወደደረሰበት ቦታ ማቅናታቸው ተነግሯል።

ሕፃኑ ተሽከርካሪውን ከፍቶ ሞተር አስነስቶ የነዳጅ መስጫ እና 'ፊሪሲዎኑን' በመጫን አሳይቷቸዋል

እናቱ ልጇን ፈጣን አእምሮ ያለው ልጅ ስትል ገልጻዋልች።

ፖሊስ በቀጣይ የመኪና ቁልፍ ልጃቸው በማይደርስበት ቦታ እንዲያስቀጡ አሳስቧል።