ናሳ የ23 ሚሊዮን ዶላር ሽንት ቤት ወደ ጠፈር ሊልክ ነው

የፎቶው ባለመብት, NASA
ናሳ የመሬት ስበት ዜሮ በሆነበት ሕዋ ላይ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ሽንት ቤት ወደ ዓለም አቀፉ ጠፈር ማዕከል (ስፔስ ስቴሽን) ሊልክ ነው።
ሽንት ቤቱ በዓለም አቀፉ ጠፈር ማዕከል ከተሞከረ በኋላ ወደፊት ጨረቃ ላይ ለሚኖሩ የሳይንስ ጉዞዎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
በተለይ ይህ ቫኩዩም ሲስተም መሰረት አድርጎ የተሰራው ሽንት ቤት ለሴት ጠፈርተኞች ምቹ እንዲሆን የተደረገ ነው ተብሏል።
ይህንን ሽንት ቤት የሚጭነው ካርጎን ወደ ሕዋ የሚያመጥቀው መንኩራኮር ከዋሎፕስ አይላንድ፣ ቨርጂኒያ ባለፈው ሐሙስ ነበር ሊመነጠቅ የታሰበው።
ነገር ግን መንኮራኩሩ ሊመነጠቅ 3 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት አጠራጣሪ የቴክኒክ እክል በማጋጠሙ ሂደቱ ተስተጓጉሏል።
ሽንት ቤቱ ልክ እንደ ማንኛውም አነስተኛ የሕዝብ ሽንት ቤት የሕዝብ ስልክ ሳጥን የሚያህል ሲሆን አጠቃቀሙ ግን ምድር ላይ ከሚገኘው ሽንት ቤት ጋር ተመሳሳይ አይደለም።

የፎቶው ባለመብት, NASA
የምድር ስበት ዜሮ በሆነበት ስፍራ ላይ መሳሪያ መሣሪያው ከሰውነት ውስጥ ቆሻሻን ስቦ በማውጣት ጠፈርተኞች እንዲጸዳዱ ያደርጋል። የጠፈር ሽንት ቤት በአሰራሩ ልክ እንደ አቧራ ማጽጃ (ቫኪዩም ክሊነር) ነው የሚሰራው። ቆሻሻን ከሰውነት በመምጠጥ ለዚህ ወደተዘጋጀ ታንከር ወስዶ ያስቀምጣል። ሽታ እና ባክቴሪያን ሙልጭ አድርጎ ያጠፋል።
ሽንት ቤቱ 45 ኪሎ ግራም ይመዝናል። 71 ሴ/ሜ ቁመት አለው። አሁን የተሰራው ሽንት ቤት ከዚህ በፊት በ ሕዋ ከነበረው ሽንት ቤት በ65 ከመቶ ያንሳል፣ በ40 ከመቶ ደግሞ ክብደሩ ቀለል ያለ ነው።
የሽንት ቤቱ ንድፍ ሰራተኞች ይህኛው ሽንት ቤት በተለይ ለሴት ጠፈርተኞች እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።
ጠፈርተኞች ለውሀ ሽንት ሲሆን ለወንድና ሴት ጾታዎች ቅርጹ የተለያየ መጠነኛ የብርሌ አፍ የሚመስል ብልቃጥ ይጠቀማሉ።
የሚሸና ሽንት አስፈላጊውን የማጣራት ሂደት አሟልቶ ከመርዛማነቱ ተጣርቶ ለመጠጥ ውሃ ተመልሶ ያገለግላቸዋል።













