መሳሳም የፍቅር መግለጫ ነው? በሰው ልጆች ዘንድ መሳሳም እንዴት እንደተጀመረ ሳይንስ ምን ይላል?

ተደብቀው የሚሳሳሙ ጥንዶች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

እውን ከንፈር ለከንፈር መሳሳም የፍቅር መገለጫ ነውን?

ሰዎች ከህጻንነታቸው ጀምሮ ከንፈራቸው ሲነካ ደስ ይላቸዋል የሚል ሃሳብ አለ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከጡት መጥባት ጀምሮ ከንፈር ከአዎንታዊ ነገሮች ጋር ስለሚያያዝ ነው የሚል ነው።

ጉዳዩን ወደ ዝግመተ ለውጥ የሚወስዱትም አሉ። በፊት በፊት ልጆች ከጡት መጥባት በኋላ ምግብ እንዲለምዱ የሚደረጉበት መንገድ ነበር።

ይህም እናቶች ምግቡን አኝከው ከላመ በኋላ ከአፋቸው ወደ ልጆቻቸው አፍ ያስተላልፋሉ። ይህ አካሄድ በጦጣዎች ዘንድም መለመዱ ነው ነገሩን ከዝግመተ ለውጥ ጋር ያገናኘው።

ሁለተኛው ደግሞ ከንፈሮቻችን በጣም ስስ መሆናቸው ነው። በልብሳችን ከማንሸፍናቸው ጥቂት የሰውነታችን ክፍሎች መካከልም ናቸው።

“ብዙ ልብስ በለበስክ ቁጥር የመሳም ድግግሞሹ ይጨምራል” ሲሉ አንትሮፖሎጂስት ፕሮፌሰሩ ዊልያም ጃንኮዊያክ ተናግረዋል።

“የምትለብሱት ልብሶች ቁጥር ባነሰ ጊዜ ደግሞ የመሳሳም ድግግሞሹ ይቀንሳል። አዳኞች እና በፍራፍሬ ሰብሳቢዎች ዘንድ መሳሳም የለም። ይህ ግን በአርክቲክ ክልል የሚገኙ ኢኑይትስን አያካትትም።”

“ሲሳሳሙ የምናገኛቸው ብቸኛዎቹ አዳኞች እና ፍራፍሬ ሰብሳቢዎች እነሱ ናቸው። አፋቸውን ከሌላኛው አፍ ጋር የሚያሻሹበት መንገድ ነው።”

ጫጩቶቿን በአፏ የምትመግብ ወፍ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ወፎች ጫጩታቸውን ከአፋቸው እያወጡ እንደሚመግቡት ሁሉ ሰዎችም እንዲሁ ያደርጉ ነበር

ይህ ደግሞ ለምን? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

“አዳኞች እና ፍራፍሬ ሰብሳቢዎች ባሉባቸው ሌሎች ቦታዎች ምንም ዓይነት ልብስ አይለብሱም። ይህ ማለት መላው አካላቸው የተጋለጠ በመሆኑ ከማንኛውም የሰውነት ክፍላቸው ጋር የቀረበ ስሜታዊ ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል ማለት ነው” ሲል ጃንኮዊያክ አክለዋል።

“ልብስ ከተለበሰ ግን ስሜትን የሚገዛው ብቸኛው አካል የሰው ፊት ነው።”

ከመሳም ጋር የተያያዘ የዝግመተ ለውጥ ዓላማም ሊኖር ይችላል።

በአካል ስንቀራረብ አንዳችን የሌላኛችንን ጠረን ማግኘት እንችላለን። ይህም ከሰው ልጅ ባህሪያት አንዱ ከንፈር ለከንፈር መሳሳም የፍቅር ግንኙነት መገለጫ እንዳልሆነ ሊያሳይ ይችላል።

ዓለም ላይ ከግማሽ በታች በሚሆኑ ባህሎች ከንፈር መሳሳም መኖሩን አንድ ጥናት አሳይቷል። በዓለም ዙሪያ ካሉ 168 ባህሎች ከከንፈር ለከንፈር መሳሳምን ለፍቅር መገለጫነት የሚጠቀሙት 46 በመቶ ብቻ እንደሆኑ ጃንኮዊያክ አግኝተዋል።

“ዋናው ነገር የሰዎች ስሜታዊነት መቀራረብ ከመሳሳም ባለፈ በብዙ መልኩ ማሟላት የሚቻል ይመስለኛል። በሚያስደንቅ ሁኔታ ግን ጠንካራ ማኅበራዊ ስብጥር ባለበት ብዙ ጊዜ መሳሳም ይኖራል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ።

በቀዝቃዛ አካባቢ የሚኖር ሰው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሚኖሩበት አካባቢ ምክንያት ምክንያት በርከት ያለ ለብስ የሚለብሱ እና አብዛኛው አካላቸውን የሚሸፍኑ ሰዎች ባሉባቸው አካባቢ የመሳሳም ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑን ጥናት አመልክቷል
Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ከመሳሳም ጋር በተያያዘ በታወቀ ደረጃ የሚገኘው ጥንታዊው የጽሑፍ ማስረጃ ሦስት ሺህ 500 ዓመት ባስቆጠረው የሂንዱ ቪዲክ ሳንስክሪት ጽሑፎች ላይ ነው።

“ዛሬ እንደምናደርገው ከንፈር ለከንፈር መሳሳምን የሚጠቀሙ ብዙ ባህሎች አሉ” ሲል የሳይንስ ኦፍ ኪሲንግ ደራሲ ሸርል አር ክሪሽንባውም ተናግረዋል።

“ነገር ግን [ቻርልስ] ዳርዊን የገለጹት የማላይ መሳሳምም አለ። ሴቶች መሬት ላይ ቁጭ ብለው ወንዶችም በላያቸው ላይ ተንጠልጥለው በፍጥነት እየተሳሳሙ የአጋራቸውን ጠረን ያሸታሉ።”

በፓፑዋ ኒው ጊኒ ምሥራቃዊ የባሕር ጠረፍ አቅራቢያ በምትገኘው ትሮብሪያንድ ደሴቶች ደግሞ ፍቅረኛሞች ፊት ለፊት ተቀምጠው ይሳሳማሉ። “ዛሬ ለብዙዎቻችን ይህ የፍቅር ጥግ ባይመስለንም ለእነሱ ግን ሁሉም ነገር ነው” ብለዋል ጃንኮዊያክ።

“ይህ ሁሉ የመተማመን ስሜትን የሚያመለክት ነው። አንዱ ወደ ሌላው ሰው ስለመቅረብ እና እኛ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንድንቀራረብ የሚያስችል ዓላማ ያለው ነው” ሲሉ አክለዋል።

ከንፈር ለከንፈር መሳሳም ከሞላ ጎደል የሰው ልጅ ባህሪ ነው። መሳሳም የዝግመተ ለውጥ ነገር ከሆነ ለምን ብዙ እንስሳት ሲሳሙ አናይም?

ሜሊሳ ሆገንቦም በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ለቢቢሲ ኧርዝ እአአ በ2015 ምላሽ ሰጥተዋል።

“ወደ አጋራችን ፊት ለመቅረብ ከሚያደርጉን ምክንያቶች አንዱ ጥሩ መዓዛ ነው።”

“መዓዛ እንደአመጋገብ፣ የበሽታ መኖር፣ ስሜት እና ተዛማጅነት የመሳሰሉ ጠቃሚ መረጃዎችን ሊገልጽ ይችላል። ብዙ እንስሳት ከእኛ የበለጠ የተራቀቁ የማሽተት ስሜቶች ስላላቸው መቀራረብ አያስፈልጋቸውም።”

ስለዚህ መሳሳማችንን እንቀጥላለን? አንዳንድ ባህሎችስ ለምን ግድ አይሰጣቸውም?

“በተለያዩ ምክንያቶች ዓለም ላይ መሳሳም ሲጨምር እና ሲጠፋ አይተናል። ከበሽታ በተጨማሪ ሕዝባቸው ሊኖረው ሚገባቸው መብት አይደለም በማለት መሳሳም የሚከለክሉ ንጉሠ ነገሥታት ነበሩ” ይላሉ ክሪሸንባም።

“ነገር ግን አንድ ነገር በእርግጠኝነት መናገር ይችላሉ። መሳሳም በአዋጅ ቢታገድ ወይም በበሽታ ምክንያት ቢከለከለም ሁልጊዜ ተመልሶ ይመጣል።”

ብዙ እንስሳት ሲሳሳሙ የማንመለከተው ለምንድነው?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ብዙ እንስሳት ሲሳሳሙ የማንመለከተው ለምንድነው?