ኮሮናቫይረስ፡ ፌስቡክ ከእንግሊዛውያን የኮቪድ-19 ምልክቶች ከታዩባቸው መረጃ ሊሰበስብ ነው

ፌስቡክ ተጠቃሚዎቹን የኮቪድ-19 ምልክት ታይቶባቸው እንደሆነና ስለማህበራዊ ርቀታቸው ይጠይቃል

የፎቶው ባለመብት, FACEBOOK

በዩናይትድ ኪንግደም ፌስቡክ የተመረጡ ተጠቃሚዎቹን የኮቪድ-19 ምልክት እንደታየባቸውና እንዳልታየባቸው ዛሬ ሊጠይቅ መሆኑ ተሰማ።

ፌስቡክ ይህንን የሚያደርገው ከካርኒጌ ሜለን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለማወቅ ይረዳል ተብሏል።

ፌስቡክ የተጠቃሚዎቹን የጤና መረጃ እንደማይዝና በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲው እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል።

አንድ ባለሙያ የሚገኘው መረጃ ለተመራማሪዎች ጠቃሚ ነው ያሉ ሲሆን ነገር ግን በራሱ ምልክቱ መታየቱ ብቻ ሳይሆን ስለ በሽታው የበለጠ በመግለጽ መሆን አለበት ብለዋል።

የዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፌስቡክ በአሜሪካ እንዲህ አይነት የዳሰሳ ጥናት ያደረገ ሲሆን በሳምንት ውስጥ በሚሊየን የሚቆጠር ምላሽ አግኝቷል።

የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ስለጤንነታቸውና መሰረታዊ የሆኑ የኮቪድ-19 ምልክቶችን እንደ ሳልና ትኩሳት ያሉ ታይቶባቸው ከሆነ ይጠየቃሉ።

የካርኒጌ ሜለን ዩኒቨርስቲ ምሁራን በሳምንት ውስጥ መረጃውን ከወሰዱ በኋላ ደግሞ በየአካባቢው ያሉ ኮቪድ-19 የሚያክሙ ሆስፒታሎችና የጽኑ ሕሙማን ክፍሎች ምን ያህል ሕሙማን ሊጎበኟቸው እንደሚችሉ ትንበያ ይሰራሉ።

ፌስቡክ በአሜሪካ በየአካባቢው ምልክቱን ያሳዩ ሰዎችን የሚያሳይ ካርታ አትሟል።

በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ማሪቺዮ ሳንቲላና ፕሮጀክቱ " በጣም ጠቃሚ ነው" ብለዋል።

" ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የስርጭት መጠን በመገመት ረገድ ትልልቅ ተግዳሮቶችን ከፊታችን እየደቀነ ነው" ሲሊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"በርካታ መረጃ ባገኘን ቁጥር እጅግ የተሻለ ይሆናል" ሲሉም ያክላሉ።

ነገር ግን አንድን የመረጃ ምንጭ ብቻ ማመን መልካም አለመሆኑን በመጥቀስ የፌስቡክ መረጃንም ለሌሎች መረጃዎች እንደ ግብዓት ብንጠቀመው ይሻላል ይላሉ።

ዶ/ር ሳንሪላና ህብረተሰቡን ስለጤናው የሚጠይቁ መተግበሪያዎችና የዳሰሳ ጥናቶች ሰፊ ምላሽ አያገኙም ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

"በየሳምንቱ ስለጤንነታችን የሚጠይቀን መተግበሪያ አይተናል። መጀመሪያ ላይ ሁሉም ሰው በንቃት ይሳተፋል፤ ከዚያም ቀናት እየጨመረ ሲሄዱ የተሳታፊዎቹ ቁጥር እየቀነሰ ይሄዳል" ብለዋል።

ስለዚህም ቫይረሱ በህብረተሰቡ ውስጥ በቆየ ቁጥር መተግበሪያዎቹን የመሰልቸት ስሜት ኣዳብራል ሲሉ ተናግረዋል።

ኮሮና