ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሞ ሳላህ ለሊቨርፑል መፈረሙ በከተማዋ ሙስሊም ጠልነት ቀነሰ
ሞሃመድ ሳላህ ለሊቨርፑል መፈረሙን ተከትሎ በከተማዋ ሙስሊም ጠልነት መቀነሱን አንድ ጥናት ጠቆመ።
ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ጥናት ሞሃመድ ሳላህ ለሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ መፈረሙ በሊቨርፑል ከተማ ሙስሊም ጠልነት በቀጥታ እንዲቀንስ ማድረጉን አረጋግጧል።
ሳላህ ከሁለት ዓመት በፊት ለሊቨርፑል ከፈረመ በኋላ በሊቨርፑል ከተማ የሙስሊም ጠል የሆኑ የወንጀሎች ቁጥር በ18.9 በመቶ ቀንሰዋል።
ታዋቂ ግለሰቦችን ማወቅ እና ማድነቅ ጭንፍን ጥላቻን ይቀንሳል ወይ?
ሞሃመድ ሳላህ በሙስሊም ጠልነት በባሕርይ እና አመለካከት በመቀየር ረገድ የለው ተጽዕኖ ምን ይመስላል በሚል እርዕስ ነው ጥናቱ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሠራው።
በእንግሊዝ ጥላቻን መሠረት ያደረጉ ወንጀሎች እና 15 ሚሊዮን የትዊተር መልዕክቶችን በጥናቱ ተንትነዋል። ጥናቱ ሊቨርፑል እግር ኳስ ቡድን በሚገኝበት ግዛት ውስጥ ሙስሊም ጠል የሆኑት ወንጀሎች ከመቀነሳቸው በተጨማሪ የሊቨርቱል ክለብ ደጋፊዎች ፀረ-እስልማና ይዘት ያላቸውን የትዊተር መልዕክት በግማሽ ቀንሷል።
ጥናቱ ይህ አዎንታዊ ለውጥ የመጣው ሰዎች ስለ እስልምና ያላቸው እውቀት በመጨመሩ ነው ይላል።