ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሞዛምቢክ ሰላሳ ሺ የማይታወቁ ሰራተኞች አሏት
የሞዛምቢክ መንግሥት፣ የመንግሥት ሰራተኞችን ክፍያ ኦዲት በተደረገበት ወቅት 30ሺ የማይታወቁ ሰራተኞች አግኝቻለሁ ብሏል።
አንዳንዶቹ ላልሰሩበት ስራ ደመወዝ የሚከፈላቸው፣ የሞቱና ሐሰተኛ ስሞች ተገኝተውበታል።
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስተሯ ካርሜሊታ ናማሹሉ እንደገለፁት ከሆነም ለነዚህ ሰራተኞች የተጭበረበረ ክፍያ ለመክፈል 250 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣቸው ነው።
በሀገሪቷ ላይ ያለውን የመንግሥት ባለስልጣናት የስራ አፈፃፀም ለመገምገም በተከናወነው ኦዲት ላይ ነው ይህ ክፍተት የተገኘው።
ይህ የማጭበርበር ሂደት ሙስናን በሚገመግመው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ኢንዴክስ ዝርዝር ውስጥ ሀገሪቷን 153ኛ ደረጃ ያስቀምጣታል።
ሚኒስትሯ ጨምረው እንደተናገሩት 348ሺ ሰራተኞች ግምገማው ውስጥ ተካተዋል።
የሞዛምቢክ መንግሥት የተለያዩ ተቋማት የሚያወጡትን ገንዘብ ለመቆጣጠር እቅድ እንደነደፈም አስታውቋል።