ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ደቡብ ሱዳን ለበጎ ፍቃደኞች አስጊ ሃገር ተባለች
ደቡብ ሱዳን ለበጎ ፍቃደኞችዎች አስጊ ከሆኑ ሃገሮች ቀዳሚነቱን ይዛለች። ደቡብ ሱዳን በበጎ ፍቃድ ለተሰማሩ ግለሰቦች እጅግ አስጊ ስትባል የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።
ኖርዌጅያን ሬፍዩጂ ካውንስል (ኤንአርሲ) የተባለ ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት ለዓመታት እርስ በእርስ ግጭት እየተናጠች ያለችው ደቡብ ሱዳን ከዜጎቿ ባሻገር በበጎ ፍቃድ ወደ ሃገሪቷ ለሚያቀኑም አስፈሪ ናት ተብሏል።
ባለፈው ዓመት በጎ ፍቃደኞች ካጋጠሟቸው 158 አደጋዎች ሶስቱ በምስራቅ አፍሪካዊቷ ደቡብ ሱዳን የተከሰቱ ናቸው።
የእርስ በእርስ ጦርነቱ እንደ አውሮፓውያኑ በ 2013 ከተቀሰቀሰ አንስቶ 100 በጎ ፍቃደኞች ህይወታቸውን አጥተዋል። ከነዚህ መካከል 24 የሚሆኑት በመሳሪያ ተመተው የሞቱ ናቸው።
የኤንአርሲ መረጃ እንደሚያመለክተው በጎ ፍቃደኞቹ በብዛት ራቅ ያሉና አስፈሪ አካባቢዎች ይሰራሉ።
በድርጅቱ ዝርዝር ውስጥ ሶርያ፣ አፍጋኒስታን፣ መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ናይጄሪያና ሶማሊያም ለበጎ ፍቃደኞች አስጊ የሆኑ ሃገሮች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
ኤንአርሲን በመወከል ጃን ኢግላንድ በቅርቡ በፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱ በጥርጣሬ ውስጥም ቢሆን ተስፋ ይሰጣል ብለዋል።