Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 36
Listen to find out how to ask someone about what sports they do.
አንድ ሰው ምን ዓይነት ስፖርት እንደሚጫወት ወይም እንደምትጫወት እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
ድምር ነጥቢ ናይዚ ክፍለ-ስራሓት 36
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
Do you play football?
Listen to find out how to ask someone about what sports they do.
አንድ ሰው ምን ዓይነት ስፖርት እንደሚጫወት ወይም እንደምትጫወት እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምፁን ያዳምጡና መልመጃውን ይመልሱ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ለማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ የሚያስፈልጉ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደምናቀርብበት Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሰዎች አንድ የጨዋታ አይነትን ስለመጫዎታቸውን እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ይማራሉ።
ሁለት ሰዎች የተለያዩ ስፖርቶችን ይጫዎቱ እንደሆነ እርስ በርስ ሲጠያየቁ ያዳምጡ።
Pam
Do you play football?
Ben
Yes, I do. How about you?
Pam
No, I don’t, but I go running.
ምህረተስላሴ
ንግግሩ ካስቸገረዎ ብዙም አይጨነቁ፤ ንግግራቸውን ከፋፍለን እንዲለማመዱ እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ “ኳስ ትጫወታለህ ወይ” ስትል ፓም ቤንን ጠየቀችው። ‘play’ የተባለውን ቃል ከማንኛውም የስፖርት አይነት ጋር እንጠቀማለን። ስለዚህ ቅርጫት ኳስ መጫዎት ‘play basketball’ እና ቴኒስ መጫዎት ‘play tennis’ እንላለን። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
Do you play football?
ምህረተስላሴ
ከዚያም ቤን “አዎ እጫወታለሁ” ‘Yes, I do.’ አለ። ለጥቆም ተከታይ ጥያቄ ሰነዘረ “አንችስ?” ‘How about you?
ይህንን አገላለጽ መጀመሪያ ጥያቄውን ላቀረበው ሰው ተመሳሳይ ጥያቄ ለመጠየቅ እንደተጠቀምንበት ያስታውሱ። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
Yes, I do.
How about you?
ምህረተስላሴ
ፓም ለቤን አዎ ወይም አይ የሚል መልስ ሰጠችው። “አይ፤ አልጫወትም” ‘No, I don’t’ ብላ መለሰች። ከዚያም ነገር ግን ‘but’ የተባለውን አያያዥ ቃል ተጠቀመችና ሌላ የምታከናውነውን ነገር አስተዋወቀች፤ እሮጣለሁ ‘I go running’ አለች። ‘go’ የሚባለውን ቃል በ‘-ing’ የሚጠናቀቁ እንቅስቃሴዎችን ለመግለፅ እንጠቀምበታለን። ስለዚህ ‘go swimming’ መዋኘት፣ ‘go hiking’ ተራራ መውጣት እንላለን። ያዳምጡ እና ደግመው ይበሉ።
No, I don’t.
But I go running.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን የተለያዩ ሰዎች ስለሚያዘወትሯቸው ስፖርቶች ሲወያዩ በማዳመጥ እርስዎ ያሉት ትክክል እንደሆነ ይፈትሹ።
Do you play tennis?
No, I don’t, how about you?
Yes, I play tennis.
Do you play basketball?
Yes, I do. How about you?
No, I don’t, but I go swimming.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ ይህንኑ ደግመን እንሞከረው። የእንግሊዝኛውን አረፍተ ነገር ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
Do you play football?
Do you play football?
Yes, I do. How about you?
Yes, I do. How about you?
No, I don’t, but I go running.
No, I don’t, but I go running.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
እግር ኳስ ትጫወታለህ?
Do you play football?
አዎ፤ አንቺስ?
Yes, I do. How about you?
አይ፤ አልጫዎትም፤ ግን እሮጣለሁ።
No, I don’t, but I go running.
ምህረተስላሴ
በጣም ግሩም፤ አሁን ሰዎች ስለሚያዘወትሩት ስፖርት መጠየቅ ተምረዋል። ለፓም ምላሽ በመስጠት ልምምድ ያድርጉ። ‘How about you?’ በማለት ተከታይ ጥያቄ ማቅረብና እና ወይይቱን ‘That sounds great!’ ብሎ መደምደም አይርሱ።
Do you play football?
No, I don’t, but I go running.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን አጠቃላይ ውይይቱን አንዴ ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Pam
Do you play football?
Ben
Yes, I do. How about you?
Pam
No, I don’t, but I go running.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሰዎች የትኞቹን የስፖርት ዓይነቶች እንደሚጫወቱ በእንግሊዝኛ መጠየቅ ችለዋል። ጓደኛ ይፈልጉና ምን ዓይነት ስፖርት እንደሚያዘወትሩ በእንግሊዘኛ በመጠየቅ ይለማመዱ። ‘How about you?’ በማለት ተከታይ ጥያቄ ማቅረብ አይዘንጉ። ለተጨማሪ የኢሰንሻል ኢንግሊሽ መሰናዶ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። Bye!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
እግር ኳስ ትጫወታለህ?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ኣመት
ኳስ ካላቸው ስፖርቶች ጋር ይሄንን ቃል እንጠቀማለንQuestion 1 of 3
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ኣመት
በመልሱ የጥያቄውን የመጀመሪያ ቃል እንደግማለንQuestion 2 of 3
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ኣመት
ከእንቅስቃሴ ጋር ሁሌም ይሄንን ቃል እንጠቀማለን።Question 3 of 3
Excellent!Great job!ሕማቕ ዕድል!ዘመዝገብኩምዎ ነጥቢ ...:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ ክፍላችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Do you ______?
ታደርጋለህ/ጊያልሽ ______ ትጫወታለህ/ቻለሽ?Yes, I do.
አዎ፤ አጫወታለሁNo, I don’t, but I ______.
አይ፤ አልጫወትም ነገር ግንplay football
እግር ኳስ መጫወትplay tennis
ቴኒስ መጫወትplay basketball
ቅርጫት ኳስ መጫወትgo running
መሮጥgo swimming
መዋኘትHow about you?
አንችስ?