Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 16
Listen to find out how to ask someone where they live.
ሰዎች የት እንደሚኖሩ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ያዳምጡ።
ድምር ነጥቢ ናይዚ ክፍለ-ስራሓት 16
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
Where do you live?
Listen to find out how to ask someone where they live.
ሰዎች የት እንደሚኖሩ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊተዋቸው የማይቻላቸውን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation በደህና መጡ። ምህረትእባላለሁ። በዚህ ክፍል የት ቦታ እንደሚኖሩ መናገርን ይማራሉ።
ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ለማወቅ ሁለት ሰዎች የት እንደሚኖሩ ሲጠያየቁ ያዳምጡ።
Sian
Hi Phil, where do you live?
Phil
I live near the market. How about you?
Sian
I live in London.
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ‘የት ነው የምትኖረው?’ ‘Where do you live?’ ብላ ነው የጠየቀችው። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
Where do you live?
ሁለተኛው ተናጋሪ ገበያው ‘the market’ አጠገብ እንደሚኖር ነው የተናገረው። ‘I live near…’ ብለው ከቤትዎ አጠገብ ያለ ስፍራን መጨመር ይችላሉ። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
I live near the market.
ከእነዚህ ስፍራዎች ከአንደኛው አጠገብ ይኖራሉ?
የከተማዋ እምብርት/ማዕከል
I live near the city centre.
የአውቶብስ መናኸሪያው
I live near the bus station.
ከዚያም የመጀመሪያዋን ተናጋሪ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቃት። አንድ ሰው የጠየቀዎትን ጥያቄ እራሱን እንዲመልስልዎት ከፈለጉ ‘እንችስ/አንተስ?’ ‘How about you?’ በማለት መጠየቅ ይችላሉ። ያዳምጡና ሐርጉን ደግመው ይበሉ።
How about you?
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ የምትኖረው ለንደን ውስጥ ስለሆነ ‘እኔ የምኖረው’ ‘I live in…’ አለችና ለንደንን ጨመረች። እርስዎም ‘እኔ የምኖረው’ ‘I live in…’ የሚለውን ሐረግ ከትናንሽ ከተሞች፥ ከትላልቅ ከተሞች፥ ከክልሎች ወይንም ከአገራት ጋር መጠቀም ይችላሉ። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
I live in London.
በጣም ጥሩ- አሁን የተለያዩ ሰዎች ስለሚኖሩበት ቦታ የሚናገሩትን በማዳምጥ እርስዎ ያሉትን ይፈትሹ።
ማርክ የሚኖረው ከሐይቁ አጠገብ ነው።
Hi Mark, where do you live?
I live near the sea. How about you?
I live in Manchester.
ክሌር የምትኖረው ከሆስፒታሉ አጠገብ ነው።
Hi Claire, where do you live?
I live near the hospital. How about you?
I live in Birmingham.
እሽ፥ አሁን ያንን ደግመን እንሞከር። የእንግሊዝኛውን አረፍተ ነገር ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
Where do you live?
Where do you live?
I live near the market.
I live near the market.
How about you?
How about you?
I live in London.
I live in London.
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንፈትሽ። አረፍተ ነገራቱን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ሃይ ፊል፥ የት ነው የምትኖረው?
Hi Phil, where do you live?
ከገበያው አጠገብ ነው የምኖረው።
I live near the market.
አንችስ?
How about you?
እኔ የምኖረው ለንደን ውስጥ ነው።
I live in London.
በጣም ግሩም! አሁን የት እንደሚኖሩ በእንግሊዝኛ መናገር እንደሚቻል አወቁ ማለት ነው። ለመጀመሪያዋ ተናጋሪ ምላሽ በመስጠት የት እንደሚኖሩ እየተናገሩ ይለማመዱ።
Hi, where do you live?
I live in London.
አሁን ጠቅላላውን ንግግር ደግመው ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Sian
Hi Phil, where do you live?
Phil
I live near the market. How about you?
Sian
I live in London.
በጣም ጥሩ። አሁን በእንግሊዝኛ የሚኖሩበት ቦታ የት እንደሆነ መናገር እና የሌሎች ሰዎችን መኖሮያ መጠየቅም ይችላሉ። የተማሩትን መለማምድን ያስታውሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ስማችሁን መጠየቅና መናገርን ይለማመዱ። ለተጨማሪ የEssential English Conversation ዝግጅቶች በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል በማስቀመጥ ምን ያህል እንደተማሩ ልብ ይበሉ።
Where do you live?
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
የሚጠይቁት ሰዎች የት እንደሚኖሩ እንጅ በንግግሩ ቅፅበት የሚገኙበትን ቦታ አይደለም።Question 1 of 3
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
በመጀመሪያ የት እንደሚኖሩ ይናገሩ። ከዚያ ስለሌላኛው ሰው ይጠይቁ።Question 2 of 3
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ኣመት
ከከተሞች እና አገራት ጋር “ውስጥ” የሚለውን እንጠቀማለን።Question 3 of 3
Excellent!Great job!ሕማቕ ዕድል!ዘመዝገብኩምዎ ነጥቢ ...:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የFacebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Where do you live?
መኖሪያሽ/ህ የት ነው?
I live near ______.
የምኖረው . . . አጠገብ ነው
How about you?
አንችስአ/አንተስ?
I live in ______.
የምኖረው . . . ውስጥ ነው
the market
ገበያው
the bus station
አውቶብስ መናኸሪያው
the hospital
ሆስፒታሉ
the city centre
የከተማው ማዕከል