Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1Essential English Conversation
- 2Essential English Conversation
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 1
Listen to find out how to introduce yourself to new people.
ለአዲስ ሰው ራስዎን እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ያድምጡ።
ድምር ነጥቢ ናይዚ ክፍለ-ስራሓት 1
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
My name is...
Listen to find out how to introduce yourself to new people.
ለአዲስ ሰው ራስዎን እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ያድምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምፁን አድምጠው ሙከራውን ያድርጉ።

ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያጠናቸው የሚገቡ የቋንቋ መሠረታዊያንን ወደሚያስተምረው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ሐና እባላለሁ። በዚህ ክፍል ራስዎን ማስተዋወቅን ይማራሉ።
ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ለመገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙ ሁለት ሰዎችን ያዳምጡ።
Sian
Hello, I'm Sian. What's your name?
Phil
Hi. My name's Phil. Nice to meet you.
Sian
Nice to meet you, too!
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎ፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያዋ ሴት ‘ሄሎ፣ ሻን እባላለሁ’ ‘Hello, I’m Sian’ ብላለች። እርስዎ ‘Hello, I’m….’ ብለው ከዚያ ስምዎትን ማስከተል ይችላሉ። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Hello, I'm Sian.
. . . ከዚያም ሌላኛውን ሰው ‘ስምህ ማነው?’ ‘what’s your name?’ ስትል ትጠይቀዋለች። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
What's your name?
ሁለተኛው ተናጋሪ ስሙን ለማስተዋወቅ የተጠቀመው ሌላ መንገድን ነው፤ ‘ስሜ እከሌ ይባላል’ ‘my name is’ ነው ያለው። ስምዎትን ለመጥቀስ ‘I’m…’ ወይንም ‘my name is…’ የሚሉትን ሐረጋት መጠቀም ይችላሉ። ለምሳሌ ‘I’m…’ ወይንም ‘My name is…’ ማለት ይችላሉ። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
My name's Phil.
ፊል ስሙን ከተናገረ በኋላ ‘nice to meet you’ ሲል ጨምሮ ተናግሯል። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
Nice to meet you.
ከዚያም ሻን ‘nice to meet you’ በማለት ከመለሰች በኋላ የሐረጉ መጨረሻ ላይ ‘too’ የሚል ቃል ጨምራለች፤ ይህም ለሌላኛው ሰው ተመሳሳይ ነገርን ስንመልስ የምንጠቀመው ነው። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
Nice to meet you, too.
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሌሎች ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ የተባባሉትን በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
Hi, I'm Pete. What's your name?
Hi, my name's Mark. Nice to meet you.
Nice to meet you, too!
Hi, I'm Alice. What's your name?
Hi, my name's Claire. Nice to meet you.
Nice to meet you, too!
ይህንን ምሳሌ እንደገና እንሞክራለን። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዱን አረፍተ ነገር አንዳንድ ጊዜ ይሰሙታል።
Hello, I'm Sian. What's your name?
Hi, my name's Phil. Nice to meet you.
Nice to meet you, too!
በጣም ጥሩ! አሁን ደግሞ እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱት እንመልከት። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጧቸውና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይናገሩ።
ሄሎ፥ ሻን እባላለሁ።
Hello, I’m Sian.
ስምህ ማነው?
What’s your name?
ሃይ፥ ስሜ ፊል ይባላል።
Hi, my name’s Phil.
ስላተዋወቅኩሽ ደስ ብሎኛል።
Nice to meet you.
እኔም ስላተዋወቁክህ ደስ ብሎኛል።
Nice to meet you, too.
በጣም ጥሩ አሁን ጠቅላላውን ውይይት እንደገና ያዳምጡ።
Sian
Hello, I'm Sian. What's your name?
Phil
Hi, my name's Phil. Nice to meet you.
Sian
Nice to meet you, too!
በጣም ጥሩ። አሁን በእንግሊዝኛ ስምዎትን መናገር እና የሌሎች ሰዎችን ስም መጠየቅ ይችላሉ። የተማሩትን ደጋግሞ መለማምድን ያስታውሱ። ጓደኛ ይፈልጉና ስም መጠየቅና መናገርን ይለማመዱ። ‘Nice to meet you!’ ማለትንም ይጨምሩ። ለተጨማሪ የ Essential English Conversation ዝግጅቶች በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛው መንገድ በማስቀመጥ ምን እንደተማሩ ይወቁ።
My name is...
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛው መንገድ አስቀምጡ።
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛው መንገድ አስቀምጡ።
ኣመት
ሁለት ክፍሎች አሉ።ሮቢን ራሱን አስተዋውቆ ከዚያ የሌላውን ሰው ስም ይጠይቃል።Question 1 of 3
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛው መንገድ አስቀምጡ።
ኣመት
እዚህ ጋር ሁለት ክፍሎች አሉ።በመጀመሪያው አረፍተ ነገር ሜጋን ራስዋን ታስተዋውቃለች።Question 2 of 3
ሓገዝ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛው መንገድ አስቀምጡ።
ኣመት
እኔም ማለት እኔም እንደዚያው ማለት እንደሆነ ያስታውሱ።Question 3 of 3
Excellent!Great job!ሕማቕ ዕድል!ዘመዝገብኩምዎ ነጥቢ ...:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ይበልጥ ጠቃሚ የሆኑ አገላለፆችን የምንማርበትና የመስማት ክህሎትን የምናዳብርበትን የአስፈላጊ እንግሊዘኛ ክፍለ ጊዜን ይከታተሉ።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Hello.
ሰላምHi.
እንደምን ናቹI'm _______.
እኔWhat's your name?
ስምህ/ሽ ማን ነው?My name's _______.
ስሜNice to meet you.
ስላገኘሁዎ ደስ ብሎኛል
Nice to meet you, too!
እኔም ስላገኘሁዎ ደስ ብሎኛል