በሞት ሊቀጣ የተበየነበት ገዳይ በበሽታ ህይወቱ አለፈ

በአሜሪካን የካሊፎርኒያ ግዛት የ 12 ዓመት ታዳጊ እና ሌሎች አራት ሴቶችን በመግደል የሞት ፍርድ የተፈረደበት ግለብ በተፈጥሮ ምክንያት መሞቱን ባለስልጣናት ገልፀዋል።

የ 77 ዓመቱ ሮድኒ አልካላ በካሊፎርኒያ ኮርኮራን ግዛት እስር ቤት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ቅዳሜ ማለዳ ላይ መሞቱ ተነግሯል።

ሮድኒ አልካላ በአንድ የአሜሪካ ቴሌዢዥን ላይ ከቀረበ በኋላ "ዴቲንግ ጌም ኪለር" በሚል መጠሪያ ያገኘው ግለሰብ በአውሮፓውያኑ 2010 የተከሰሰው።

የካሊፎርኒያ ግድያዎችን ጨምሮ እንዲሁም በኒው ዮርክ ውስጥ ሌሎች ሁለት ሴቶችን በመግደል ጥፋተኛነቱን አምኗል።

አልካላ የ12 አመቷን ታዳጊ ሮቢን ሳምሶይ የገደላት በአውሮፓውያኑ 1980 ነበር። በፈፀመው አፈና እና ግድያ በኦሬንጅ ካውንቲ ውስጥ የሞት ቅጣት ተፈረደበት።

ሆኖም ፍርዱ በካሊፎርኒያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሽሮ ጉዳዩ እንደ አዲስ እንዲታይም ተበየነ።

በሁለተኛው የፍርድ ሂደት ተመሳሳይ ቅጣት ተበየነበት ነገር ግን በአውሮፓውያኑ 2003 ውሳኔው ተሻረ።

በቀጣዮቹ ዓመታት መርማሪዎች አልካራ ከሌሎች የካሊፎርኒያ ግድያ ጋር የሚያገናኘው ማስረጃዎችን አገኙ።

ግለሰቡም በአውሮፓውያኑ 2011 የአስራ ሁለት አመቷን ታዳጊ ጨምሮ ከ18-32 አራት ሴቶችን በመግደል ጥፋተኛ ሆኖ ተገኘ።

የአስራ ሁለት አመት ታዳጊን ጨምሮ አራት ሴቶችን የገደለው በአውሮፓውያኑ 1977-1979 ነው።

በአውሮፓውያኑ 1978 አልካላ የፍቅር ጓደኞችን በሚያገናኝ አንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ መቅረቡን ተከትሎ ነው ሁኔታው የተጋለጠው።

በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ አንዲት ሴት ከቀረቡላት ሶስት ወንዶች መካከል በመልሳቸው በመመርኮዝ አንድ ወንድ ትመርጣለች።

አልካላን በመልሱ ብትመርጠውም ከመድረኩ ጀርባ ባላቸው ነገሮችና ባሳየው ባህርይ ውሳኔዋን እንደሰረዘች ተናገረች።

ያንንም ተከትሎ ነው ምርመራዎች የተጀመሩት፤ ግለሰቡም ጥፋተኛነቱን ያመነው።