ልዑል ፊሊፕ፡ የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ ሕይወት በምስል

የኤደንብራው ልዑል እኤአ በ1977
የምስሉ መግለጫ, የኤደንብራው ልዑል የተወለዱት በግሪኳየኮርፉ ደሴት ሰኔ 10/1921 (እኤአ) ነው። የዘር ሐረጋቸው የዴንማርክ፣ የጀርመን፣ የሩሲያና የብሪታኒያ ንጉሣዊ ቤተሰብን ያካትታል።
1px transparent line
ፊሊፕ በልጅነቱ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images / Alamy

የምስሉ መግለጫ, ልዑል ፊሊፕ የግሪኩ ልዑል አንድሩ እና የባቴንበርግ ልዕልት አሊስ ብቸኛ ልጅ ነበሩ
የግሪኩ ልዑል ፊሊፕ በኋላም የኤደንብራው መስፍን በሴይንት ክላውድ ማክጃኔት የአሜሪካ ትምህርት ቤት ከክፍል ጓደኞቹ ጋር። ልዑሉ በግራ በኩል ሁለተኛው ልጅ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ልዑሉ ትምህርቱን የጀመረው በፈረንሳይ ሴይንት ክላውድ፣ ማክጃኔት የአሜሪካውያን ትምህርት ቤት ሲሆን፤ እዚህ እንደሚታየው (በግራ በኩል ሁለተኛው ልጅ) ከክፍል ጓደኞቹ ጋር እየተጫወተ ነው። በሰባት ዓመቱ ከዘመዶቹ ጋር ወደ እንግሊዝ ሞንትባተን አቀና። ከዚያም የመሰናዶ ትምህርቱን በሱሬይ ተከታትሏል።
ልዑል ፊሊፕ በ16 ዓመቱ በጎርዶንስቶን

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, በኋላም በኩርት ካሃን በሠሜናዊ ስኮትላንድ ወደተመሰረተው እና በስፖርት ከፍተኛ ብቃቱን ወዳሳየበት ጎርዶንስቶን አዳሪ ትምህርት ቤት በመግባት ተከታትሏል።
1px transparent line
እኤአ ሐምሌ 23 1939 ዳርትማውዝ ውስጥ ልዕልት ኤልዛቤት(በግራ በኩል ሶስተኛ)፣ ሮያል ናቫል ኮሌጅ የሚገኘው ቻፕል በሚጎበኝበት ወቅት ከንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛ እና ከንግሥት ኤልዛቤት ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ልዕልት ኤልዛቤት (በግራ በኩል ሦስተኛ) እና በወቅቱ የባሕር ኃይል አባል የነበረው የግሪኩ ልዑል ፊሊፕ እንዲሁም ዴንማርክ (በቀኝ ጥግ በኩል ነጭ ኮፍያ ያደረገው) በጋራ የተነሱት ፎቶ ነው ተብሎ ይታመናል። ፎቶውን የተነሱት እኤአ በሐምሌ ወር 1939 ዳርትማውዝ የሚገኘው ሮያል ናቫል ኮሌጅ ውስጥ ጉብኝት እያካሄዱ ነው።
የኤደንብራው መስፍን፣ ዘውዳዊ የባሕር ኃይል፣ ፖርትስማውዝ

የፎቶው ባለመብት, PA

1px transparent line
ልዕልት ኤልዛቤት እና ሌተናንት ፊሊፕ ሞንትባተን የቃልኪዳን ቀለበት አሰሩ

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, በ1947 ሐምሌ ወር ልዕልት ኤልዛቤት እና ሌተናንት ፊሊፕ ሞንትባተን የቃልኪዳን ቀለበት ማሰራቸው ይፋ ተነገረ
1px transparent line
ሕዳር 20 1947 ልዕልት ኤልዛቤት (በኋላም ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ) እና የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ በባኪንግሃም ቤተመንግሥት ለሰርጋቸው ፎቶ ሲነሱ

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, በዚያው ዓመት ኅዳር 20 ተጋቡ
1px transparent line
የኤደንብራው መስፍን ከውሃ ለዓእ ሲዘሉ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በ1951 የኤደንብራው መስፍን ቱርክ ውስጥ ከውሃ መንሸራተቻ ላይ ሲዘሉ
የኤደንብራው መስፍን በሮይሃምፕተን ክለብ ፖሎ ሲጫወቱ፣ በሮይሃምፕተን ዋንጫ ላይ ለግማሽ ፍጻሜ ብሪታኒያን በመወከል ሲጫወቱ

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, የኤደንብራው መስፍን በሮይሃምፕተን ክለብ ፖሎ ሲጫወቱ፣ በሮይሃምፕተን ዋንጫ ላይ ለግማሽ ፍጻሜ ብሪታኒያን በመወከል ሲጫወቱ
1px transparent line
የኤደንብራው መስፍን ከኖርፎክ መስፍን ጋር ክሪኬት ግጥምያ ሲያደርጉ

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, መስፍኑ የክሪኬት አፍቃሪ የነበሩ ሲሆን፣ ከእንግሊዝ ኮከቦች ተዋቀረ ቡድን ነበራቸው። ምስሉ ላይ ከኖርፎኩ መስፍን ከሰሴክስ ተጫዋቾች ጋር በመሆን ግጥሚያ ሲያካሄዱ
ንግሥቲቷ እና ፊሊፕ ከአራት ልጆቻቸው ጋር (በስተግራ) ኤድዋርድ፣ አንድሪው፣ አኔ እና ቻርልስ በ1960ዎቹ የተነሱት ፎቶ
የምስሉ መግለጫ, ንግሥቲቱ እና ፊሊፕ ከአራት ልጆቻቸው ጋር (በስተግራ) ኤድዋርድ፣ አንድሩ፣ አን እና ቻርልስ በ1960ዎቹ የተነሱት ፎቶ
ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ እና የኤደንብራው መስፍን የብር የጋብቻ በዓላቸውን ለማክበር ባልሞራል በሚገኘው ቤታቸው የእርሻ ስፍራን ሲጎበኙ

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, ጥንዶቹ ለብር ኢዮቤልዩ የጋብቻ በዓላቸው ባልሞራል በሚገኘው ቤታቸውእየርሻ ቦታ ሲጎበኙ
ንግሥቲቱ እና የኤደንብራው መሥፍን ኒውዚላንድ በሚገኝ የራግቢ መጫወቻ ስፍራ ባህላዊ አልባሳት ለብሰው

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, በ1977 ልዑሉ ንግሥቲቱን የብር እዮቤልዩ ሲያከብሩ አጅበዋቸው ተገኝተዋል። ሁለቱም ኒው ዚላንድ ጊስቦርን በሚገኝ የራግቢ መጫወቻ ስፍራ ባህላዊ አልባሳት ለብሰው ይታያሉ።
በ1983 የኤደንብራው መሥፍን ካናሃ ጌም ሪዘርቭን በዝሆን ላይ ተቀምጠው ሲጎበኘዑ

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, የኤደንብራው መሥፍን የተፈጥሮ ጥበቃ በሕይወታቸው የሚደሰቱበት ተግባር ነበር። በወቅቱ ወርልድ ዋይልድ ላይፍ ፈንድ ዓለም አቀፍ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል።
የዌልሱ ልዑል ከዌልሷ ልዕልት ጋር፣ ልዑል ሀሪ፣ ልዑል ዊሊያም፣ የኤደንብራው መሥፍን፣ ልዑል ኤድዋርድ፣ ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ እና ልዕለት አኔ በባኪንግሃም ቤተመንግሥት ባልኮኒ ላይ

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, በ1985 የኤደንብራው መሥፍን በቤተሰቦቹ ተከበው፣ በወቅቱ ልጅ የነበሩት ዊሊያም እና ሀሪ በባኪንግሃም ቤተመንግሥት ባልኮኒ ላይ ሆነው የሚያልፈውን ሰልፈኛ ሲመለከቱ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ከኤደንብራው መሥፍን ጋር

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, በ1996 የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩት ኔልሰን ማንዴላ ለመጀመሪያ ጊዜ በብሪታኒያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ የኤደንብራው መሥፍን አቀባበል አድርገውላቸው ነበር
(በስተቀኝ) ንግሥት ኤልሳቤት ሁለተኛ እና የኤደንብራው መሥፍን (መካከል) በንግሥቲቱ ወርቃማ እዮቤልዩ በዓል ላይ በምዕራብ ሎንዶን የሚገኝ የገበያ ስፍራ ተገኝተው

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, ልዑል ፊሊፕ ንግሥቲቷን ከ60 ዓመት በላይ በቆየው የንግሥና ዘመናቸው ከጎናቸው በመሆን ሲያግዟት ቆይተዋል
የኤደንብራው መሥፍን በኖርፎክ በተደረገ የፈረስ ግልቢያ ውድድር ላይ ሲሳተፉ

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ, የኤደንብራው መሥፍን እድሜያቸው ከገፋ በኋላም በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ ይሳተፉ ነበር
የብሪቴን ልዑል ዊሊያም ከሰርጋቸው በኋላ ባለቤቱን ኬትን በባኪንግሃም ቤተመንግሥት ባልኮኒ ላይ ሲስም፣ ሎንዶን ሚያዝያ 29 2011

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, የልዑል ፊሊፕ የልጅ ልጅ ልዑል ዊሊያም ካትሪን ሚድልተንን በ2011 ባገባበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከባኪንግሃም ቤተመንግሥት ውጪ ተሰብስበው ነበር
1px transparent line
ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ እና የኤደንብራው መሥፍን በማዕከላዊ ለንደን ዌስትሚኒስትር አቤይ የንግሥቲቱን 60ኛ በዓለ ሲመት ሲያከብሩ

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, በሰኔ 2013 የኤደንብራው መሥፍን በዌስትሚኒስትር አቤይ የንግሥቲቱን 60ኛ ዓመት ንግስ በዓል ላይ ታድመው ነበር
በቤልፋስት ሂልስብሮው ካስትል የጎብኚዎች መዝገብ ላይ ሲፈርሙ

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, በ2014 ንግሥቲቷን አጅበው ሰሜናዊ አየርላንድ ተገኝተው ነበር። በቤልፋስት ሂልስብሮው ካስትል የጎብኚዎች መዝገብ ላይ ሲፈርሙ
በ2016 ጥቅምት ወር የኤደንብራው መሥፍን (በስተግራ) እና ልጃቸው የዌልሱ ልዑል ቻርለስ

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, በ2016 ጥቅምት ወር የኤደንብራው መሥፍን (በስተግራ) እና ልጃቸው የዌልሱ ልዑል ቻርለስ
ግንቦት 23 2017 ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ እና የኤደንብራው መሥፍን በባኪንግሃም ቤተመንግሥት

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የኤደንብራው መሥፍን በብሪቲሽ ታሪክ ረዥም ዓመት ዘውዳዊውን ስርዓት ያገለገሉ ናቸው

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ልዑል ፊሊፕ

ሁሉም ፎቶዎች በባለቤትነት መብት ስር ናቸው።