የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሳርኮዚ በሙስና ክስ አስር ተፈረደባቸው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ፍርድ ቤት የቀድሞውን የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኒኮላስ ሳርኮዚ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ናቸው በማለት የሦስት ዓመት እስር ፈረደባቸው።
የ66 ዓመቱ ሳርኮዚ የተከሰሱት ጊልበርት አዚቤርት የተባሉ ዐቃቤ ሕግ በፓርቲያቸው ላይ የሚደረገውን የወንጀል ምርመራን በተመለከተ መረጃ እንዲሰጧቸው በምላሹም ጉቦና ሞናኮ ውስጥ የተሻለ ሥራ ለመስጠት በመሞከር ተከስሰው ነው የተፈረደባቸው።
ሳርኮዚ ግን የቀረበባቸውን ክስ ያስተባበሉ ቢሆንም ውሳኔው ለእስር ሳይዳርጋቸው እንደማይቀር ተነግሯል።
በሳርኮዚ ላይ የተላለፈው የጥፋተኝነት ውሳኔ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በፈረንሳይ በቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣን ላይ የተሰጠ ተጠቃሽ ፍርድ እንደሆነ ተነግሯል። ቀደም ሲል ሟቹ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዣክ ሺራክ ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ ለወዳጆቻቸው የሥራ ዕድል አመቻችተዋል በሚል በገደብ የሁለት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው ነበር።
ዐቃቤ ሕግ በሳርኮዚ ላይ የአራት ዓመት እስር እንዲበየን ጠይቆ ሁለቱ ዓመት በገደብ እንዲሆን ሲከራከር ነበር።
ሳርኮዚ አሁን ውሳኔ ካገኘው ክስ በተጨማሪ በመጋቢትና በሚያዚያ ወራት ውስጥ በፍርድ ቤት የሚታይ ሌላ ክስ አለባቸው። ይህም ሳርኮዚ ከዘጠኝ ዓመት በፊት ለፕሬዝዳንትንት በሚወዳደሩበት ጊዜ ለምርጫ ዘመቻቸው የተጭበረበረ ወጪጪን አውጥተዋል የሚል ነው። በምርጫውም ሳይሳካላቸው በድጋሚ ሳይመረጡ ቀርተዋል።
ቢሆንም ግን በሚቀጥለው ዓመት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ዕቅድ በያዘችው ፈረነረሳይ ውስጥ ኒኮላስ ሳርኮዚ በቀኝ ክንፍ የፖለቲካ አራማጆች በኩል ከፍ ያለ ድጋፍ አላቸው።








