ኮሮናቫይረስ፡ የኦክስፎርድ የኮቪድ-19 ክትባትን እንዴት በዚህ ፍጥነት ሊሰራ ቻለ?

የፎቶው ባለመብት, John Cairns/University of Oxford
አስር ዓመታት ይፈጅ የነበረ ሥራ በአስር ወራት ውስጥ ተጠናቋል። ነገር ግን በዲዛይን ፣ በሙከራ እና በምርት ሂደት ውስጥ የቀሩ ነገሮች የሉም።
እነዚህ ሁለት አረፍተ ነገሮች እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ይመስላሉ። ምክንያቱም የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ክትባት ኮቪድ-19ኝን በመከላከል ረገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማ ነው መባሉ አስደሳች ዜና ቢሆንም፤ በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሰራቱ ግን ደኅንነቱ ላይ በርካቶች ጥያቄ እንዲያነሱ አስገድዷል።
ስለዚህ ይህ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ክትባት እንዴት በዚህ ፍጥነት እንደተሰራ የሚገልጽ ነው።
በአፍሪካ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ምናልባት ለተመራማሪዎች በርካታ ትምህርት የሰጠ ይመስላል።
ኢቦላ በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ሰውነት ውስጥ በሚወጣ በጣም አነስተኛ መጠን ባለው ፈሳሽ ሳይቀር በመተላለፉና ያልተለመዱ ምልክቶች ስላሉት ችግሩን ከቁጥጥር ውጭ ያደርገዋል።
ምክንያቱ ደግሞ ሰዎች የሚገናኙበት፣ የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና እንቅስቃሴዎች የሚዘወተሩበት አካባቢ ለቫይረሱ የሚያጋልጥ አይነት በመሆኑ ቫይረሱ የሚዛመትበትን እድል ስለሚያፋጥነው ነው።
እንደ አውሮፓውያኑ ከ2014-2016 በምዕራብ አፍሪካ የተከሰተው ኢቦላ መነሻው ጊኒ ውስጥ በምትገኝ ትንሽ መንደር ውስጥ ሲሆን፤ መጀመሪያ በቫይረሱ የተያዘውም እደሜው ሁለት ዓመት የሚሆነው ህፃን ነበር።
በሽታው በጊኒ እንዲሁም በጎረቤቶቿ ሴራሊዮንና ላይቤሪያ በተለይ በከተሞች አካባቢ በፍጥነት ተሰራጭቶ ነበር። ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከእነዚህ አገራት በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ብትገኝም ልታመልጥ ግን አልቻለችም።
እስካሁን ኢቦላ ተገኝቶባቸዋል የተባሉ አምስት ቀጠናዎች የተለዩ ሲሆን የሞቱት ዜር በተሰኘው ቀጠና ነው። በእነዚህ ቀጠናዎች ለመጠባበቂያ የተዘጋጀው ክትባት ለድንገተኛ ክስተቶች ይውላል።
በእንግሊዝና በኖርዌይ መንግሥታት ድጋፍ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ክትባቱ ተቀባይነት ያገኘ ቢሆንም ለሰዎች እንዲሰጥ እስካሁን ሙሉ ፈቃድ አልተገኘም። ይሁን እንጂ ጠጥቅም ላይ እንዲውል ለመጠባበቂ 300 ሺህ የሚሆኑ ክትባቶች ተዘጋጅተዋል።
ክትባቱ ቫይረሱ ይኖርባቸዋል ተብለው ለተጠረጠሩ ህሙማን፣ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች መሰጠት እንዳለበት የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል።
ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ሚኒስቴር ውሳኔ ብቸኛው አማራጭ ነው።
ኢቦላ በቀላሉ ሊጠፋ እንደሚችል ተስፋ በማድረግ የሚያጋጥሙትን እያንዳንዱን ጥቃቅን ችግሮች በመፍታት ችግሩ ስር ሳይሰድ አሁን ባለበት ደረጃ ማስቀረት ይቻላል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ከ2014 እስከ 2016 ለነበረው የኢቦላ ወረርሽኝ የተሰጠው ምላሽ በጣም የዘገየ ስለመነበር 11 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
"ዓለም ከዚህ የተሻለ ማድረግ ትችል ነበር'' ይላሉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ክትባት ምርምርን የሚመሩት ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት።
''ከኢቦላ የተገኘውን ተሞክሮ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ሰው ሰውነት ውስጥ በፍጥነት ክትባቱ እንዲሰራ ለማድረግ አቅደን ነበር የጀመርነው። ምንም እንኳን እቅዱን ባንጨርሰውም በጣም አመርቂ ሥራ ነው የሰራነው።"

የፎቶው ባለመብት, John Cairns/University of Oxford
ጥር 1/2020 (እአአ)
አብዛኛው የዓለማችን ሕዝብ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት በማስመለክት በየቦታው ደስታውን ሲገልጽና በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ በዓሉን ሲያከብር ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት ግን ከወደ ቻይና አንድ አስደንጋጭ ዜና ሰምተው ነበር።
ይኽውም ከዉሃን ከተማ "አንድ ጉንፋን መሰል ቫይረስ እየተሰራጨ ነው" የሚል ነበር። በወቅቱ ተመራማሪዎች ስለቫይረሱ ማወቅ የቻሉት ብዙ ነገር ባይኖርም ከሰዎች ወደ ሰዎች ሊተላለፍ እንደሚችል ግን ገምተው ነበር።
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡድን ምንም እንኳን ለአንድ ተላላፊ ቫይረስ የሚሆን ክትባት እንደሚሰራ ቢያውቅም ነገር ግን ይህ ቫይረስ ብዙ ጉዳት ሳያደርስ እንደሚጠፋ ነበር የታሰበው።
"ልክ እንደ ማንኛውም አይነት ፕሮጀክት ነበር የያዝነው። ቫይረሱም በራሱ ጊዜ ሊጠፋ እንደሚችልም ገምተን ነበር" ይላሉ ፕሮፌሰሯ።
ከዚህ በፊት የነበሩት የኮሮረናቫይረስ ክስተቶች ለዚህ ቡድን ጠለቅ ያለ ቅድመ እውቀት ሰጥቶታል። ለምሳሌ በ2002 ተከስቶ የነበረው የሳርስ ኮሮናቫይረስ እና በ2012 የተከሰተው የመርስ ኮሮናቫይረስ የሚጠቀሱ ናቸው።
ይህ ማለት ተመራማሪዎች ቫይረሱ እንዴት እንደሚራባና ከሰው ወደ ሰው፣ ከሰው ወደ እንስሳት አልያም ከእንስሳ ወደ እንስሳ እንደሚተላለፍ አጠቃላይ እውቀት ነበራቸው።
ለሙከራ በተሰራው ክትባት ውስጥ ያለው የፕሮቲን ከፍ ማለት ቫይረሱ በሰውነታችን ሴሎች ውስጥ የሚገቡበትን በሮች ለመክፈት የሚጠቀምበት ቁልፍ ነው። ክትባቱ የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል ሥርዓትን ቫይረሱን በከፍተኛ ፍጥነት ለማጥቃት የሚያሰለጥን ከሆነ ቡድኑ እሱን ለመሳካት ዕድለኛ ይሆናል ማለት ነው።
"ይህ ሙሉ በሙሉ ያልታወቀ ቫይረስ ቢሆን ኖሮ በጣም በተለየ ሁኔታ ውስጥ እንገባ ነበር" ይላሉ ፕሮፌሰሯ።
እንዲሁም ኮሮናቫይረስ የአጭር ጊዜ ኢንፌክሽኖችን ብቻ ማስከተሉ ነገሮች እንዳይወሳሰቡ አድርጎ ነበር። ይህ ማለት ሰውነታችን ቫይረሱን የማሸነፍ አቅም አለው ማለት ነው፤ እናም ክትባቱ ወደዚያው የተፈጥሮ ሂደት ውስጥ መግባት አለበት ማለት ነው።
ባለፈው ዓመት ልክ ጥር 11 ላይ የቻይና ሳይንቲስቶች የኮሮናቫይረስ ሙሉውን የዘረመል ኮድ አሳትመው ለዓለም አጋሩ። ቡድኑ አሁን የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ አግኝቷል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ገንዘብ፣ ገንዘብ፣ ገንዘብ
ክትባት መስራት በጣም ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል።
"የመጀመሪያው ዙር በተለይ በጣም ከባድ ነበር። በአንድ ወቅት እንደውም በባንክ አካውንታችን ውስጥ ምንም አይነት ገንዘብ አልነበረም" ይላሉ ፕሮፌሰሯ።
ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ትንሽ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ቢሆንም በተቀረው ዓለም ምርምር ከሚያደርጉ ተመራማሪዎች የተሻለ ብልጫ ግን ነበራቸው። ምክንያቱም ክትባት የማግኘት ሥራውን የጀመሩት ቀደም ብለው ስለሆነ ነው።
ኦክስፎርድ ውስጥ በሚገኘው የቸርችል ሆስፒታል ውስጥ የተመራማሪዎች ቡድኑ የራሱ የክትባት ማምረቻ ማዕከል አለው።
"እስከ ሚያዝያ ወር ድረስ ለምርምሩ የሚሆን ገንዘብ ማፈላለግ ዋነኛ ሥራችን የነበረ ሲሆን ሰዎች ሥራችንን በገንዘብ እንዲደገፉ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረቶችን ማድረግ ነበረብን።"
ነገር ግን የኮሮረናቫይረስ ወረርሽ በበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ያሳረፈውን ተጽዕኖ ተከትሎ በቂ ገንዘብ ማግኘት ለቡድኑ አዳጋች ነበር። በተለይ ደግሞ በበርካታ አገራትና ከተሞች የእንቅስቃሴ ገደቦች ሲጣሉ ይበልጥ ከባድ ሆኖ ነበር።
ልክ ቡድኑ የሙከራ ክትባቱን ሲሰራ በብዛት ማምረት እንዲቻል ተብሎ የምርት ሂደቱ በጣልያን እንዲካሄድ በመደረጉ በተገኛው ገንዘብ በአውሮፓ የእንቅስቃሴ ገደቡን ተከትሎ ያጡትን ገንዘብ በመጠኑም ቢሆን እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።
ከዚህ በኋላ ተመራማሪዎቹ ወዲያው ክትባቱን በእንስሳት ላይ ወደ መሞከሩ ተሸጋገሩ። በዚህም የክትባቱን ደኅንነት እና በሰዎች ላይ ሊኖረው የሚችለውን የጎንዮሽ ጉዳት ለመፈተሽ እድል አግኝተዋል።
ሚያዝያ 23 ላይ ደግሞ ክትባቱን በሰዎች ላይ መሞከር ጀመሩ።
አንድ ክትባት ውጤታማነቱ እንዲረጋገጥና የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያስከትል ለማወቅ ወሳኝ የሚባሉ ሦስት ሂደቶችን ማለፍ አለበት።
- ሂደት አንድ- ክትባቱ ደኅንቱን ለማወቅ በጥቂት ሰዎች ላይ ይሞከራል
- ሂደት ሁለት- የደኅንነት ሙከራው በበርካታ ሰዎች ላይ ይካሄዳል። በዚያውም ክትባቱ ምን ያህል ውጤታማ ነው የሚለው ይፈተሻል።
- ሂደት ሦስት- ትልቁ ሙከራ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበትና በአርግጥም ክትባቱ ይሰራል የሚለው የሚረጋገጥበት ነው።
የኦክስፎርድ ክትባት እንዚህን ሁሉ ሂደቶች አልፎ ነው እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የቻለው። በእነዚህ ሙከራዎች ላይ 30 ሺህ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞች በሦስቱም ሂደቶች ላይ ተሳትፈዋል።
በዚህ አካሄድ ታዲያ እስከ አስር ዓመት ሊፈጅ ይችል የነበረውን ክትባት የመስራት ሂደት በአስር ወራት ውስጥ ማጠናቀቅ ተችሏል። በአሁኑ ጊዜ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሰዎችን 70 በመቶ ከቫይረሱ መጠበቅ ያስችላል ተብሎለታል።
ከዚህ ቀደም ይፋ የተደረጉት የፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶች አስተማማኝነት 95 በመቶ መሆኑ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ የኦክስፎርድ ክትባት ከሁለቱ ክትባቶች አንጻር ዋጋው ርካሽ መሆኑ እንዲሁም ኦክስፎርድ ሰራሽ ክትባትን ማጓጓዝ እና ማከማቸት ከሁለቱ ክትባቶች አንጻር እጅግ ቀላል መሆኑ በመልካም ጎኑ ተጠቃሽ ሆኗል።
በዚህም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የኦክስፎርድ ክትባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አስቀድሞ 100 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ክትባት ብልቃጦችን ለመግዛት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር ውል አስሯል።
ይህ ማለት ለ50 ሚሊዮን ሰዎች የሚበቃ ነው። ሰዎች ክትባቱን በሦስት ሳምንት ልዩነት ሁለት ጊዜ ይወስዱታል ተብሏል። የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ጥበቃ ኃላፊ ማት ሃንኮክ ለቢቢሲ፤ "ይህ ወደ መደበኛው ሕይወት ለመመለስ አንድ እርምጃ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ነዋሪነታቸው በዩናይትድ ኪንግደም እና ብራዚል የሆኑ 20 ሺህ ሰዎች ላይ የኦክስፎርድ ክትባት ሙከራው ተከናውኗል።
የዩናትድ ኪንግደም መንግሥት ደግሞ 4 ሚሊዮን ክትባቶች ተረክቧል።
96 ሚሊዮን ብልቃጦችን ደግሞ በቅርቡ ከአምራቹ ይቀበላል ተብሏል። ክትባቱ ግን የመድኃኒት ተቆጣጠሪዎችን ይሁንታ ሳያገኝ ለሰዎች አይሰጥም።
መድኃኒት ተቆጣጣሪዎች የክትባቱን አቅም ለመፈተሽ እና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደማያስከትል ለማረጋገጥ ቢያንስ ሳምንታት ያስፈልጋቸዋል።
በዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን በቅድሚያ ከሚያገኙት መካከል እድሜያቸው የገፋ ሰዎች፣ በአረጋውያን መኖሪያ ውስጥ የሚገኙ አዛውንቶች እና የተቋማቱ ሠራተኞች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ የሆናቸው አዛውንቶች ተጠቃሽ ናቸው።
የክትባቱ ዘላቂነት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እስካሁን አልታወቀም። ይህን ለማወቅ ተሳታፊዎች ላይ የሚደረገው ክትትል ይቀጥላል።
ክትባቱ በዕድሜ ለገፉ ሰዎች የተሻለ መከላከል እንደሚሰጥ ቢጠቆምም ሙሉ መረጃ ግን ያሻል ተብሏል።
ሌላው የማይታወቀው ነገር ክትባቱ ሰዎች በጣም እንዳይታመሙ ከማድረግ ያግዳል ወይ የሚለውና ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፉስ ያግዛል ወይ የሚለው ነው።
ደኅንነቱስ?
ክትባቱ እስካሁን በደኅንነት ጉዳይ ይህ ነው የሚባል ነገር አልተነሳበትም። ነገር ግን የትኛውም መድኃኒት 100 በመቶ እንከን አልባ ሊሆን አይችልም።
አንዳንድ ተሳታፊዎች ክትባቱን የወሰዱ ሰሞን መጠነኛ ድካም፣ ራስ ምታትና ሕመም እንደተሰማቸው አስታውቀዋል።
የሞዴርና እና የፋይዘር ክትባት ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆናቸው ተነግሯል። ነገር ግን የሁለቱም ድርጅቶች ውጤት የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም። ውጤታማነቱም ሊቀየር ይችላል ተብሏል።
ቢሆንም የሞዴርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ ከሌሎቹ ክትባቶች በተለየ ቀላል እንደሆነ ተነግሯል። የሞዴርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ እስከ አንድ ወር መቆየት ሲችል የፋይዘር ግን ለአምስት ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው።
ሩስያ ይፋ ያደረገችው ስፑትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትም 92 በመቶ የመከላከል አቅም እንደለው ተነግሯል።















