ኮሮና ቫይረስ፡የቤት እንስሳት ኮሮናን ያመጡብናል ብላችሁ እንዳትሰጉ ተባለ

ድመት

የፎቶው ባለመብት, Victoria Gill

በዙሪያችን ያለው ሁሉ ስጋት የሚያጭር እንጂ ልብን የሚያሳርፍ አይመስልም። በተለይ በዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ዘመን ትክክለኛ መረጃ ከሌለዎች ሁሉም ነገር ስጋት ያጭራል።

ርቀትዎን ጠብቀው፣ እጅዎን ታጥበው ከማንም ጋር ሳይጨባበጡ ቤትዎ ሲገቡ ጭራዋን እያወዛወዘች የምትተሻሽዎ ውሮ ወይም እየዘለለ የሚቀበልዎ ቡቺ በኮሮና ተጠቅተው ይሆን? ኮሮናስ ሊያሲዝዎት ይችላሉ?

የእንስሳት ሕክምና ተመራማሪዎች ኮሮና በቤት እንስሳቶታችሁ በኩል ይመጣብኛል ስትሉ ስጋት አይግባችሁ እያሉ ነው።

ነገር ግን የድመት ባለቤቶች በእንስሳት መካከል የሚኖረውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል ሲባል በቤት ውስጥ ብቻ እንዲቆዩ አድርጉ ሲሉ መክረዋል።

ይህ "የድመቶቻችሁን እሰሩ" ምክር የመጣው ያለምክንያት አይደለም፤ በሆንክኮንግ የሲቲ ዩኒቨርስቲ ምሁሩ ዶ/ር ኤንጅል አልሜንድሮስ " አንድም ውሻ ወይንም ድመት ወደ ሰው ኮቪድ-19 አስተላለፈ የሚል ማስረጃ የለም" ይላሉ።

በርግጥ ይላሉ ተመራማሪው ድመቶች ከሌላ ድመት በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ። ስለዚህ በማለት ዶ/ር ሳንቶስ "በዚህ በወረርሽኝ ወቅት ራሳችሁን ብቻ ሳይሆን ድመቶቻችሁን በቤታችሁ ብትይዙ መልካም ነው"

ዳንኤላ ዶስ ሳንቶስ የብሪታኒያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ናቸው። ቢቢሲ በዘህ ጉዳይ ላይ አነጋግሯቸው ሲመልሱ በዶ/ር ኤንጅል ሃሳብ እንደሚስማሙ ገልፀዋል።

አክለውም "ከቤተሰብ አባላቶቻችን መካከል አንዱ የኮሮና ምልክት ካሳየ ድመቶችን በቤት ውስጥ መያዝ ተገቢ ነው ብለዋል"። ለምን?

ይህም ቫይረሱ ለሌሎች ድመቶችም እንዳይተርፍ በማለት ይመስላል። በተጨማሪም የቤት እንስሳቶችን የሚንከባከቡ ባለቤቶች እጃቸውን በሚገባ መታጠብ እንዳለባቸው መክረዋል።

" እንስሳቶቹ በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ካላቸው በፀጉራቸው ውስጥ ቫይረሱን ሊይዙ ይችላሉ" በሆንክ ኮንግ አንድ የ17 ዓመት ውሻ በኮሮና ተይዞ የነበረ ሲሆን የተያዘው ደግሞ ከባለቤቱ ነው ተብሏል።

" ነገር ግን ምንም እንኳ እንስሳቱ ቫይረሱ ቢገኝባቸውም አይታመሙም" ይላሉ ሐኪሞቹ።

" በ2003 በሆንክኮንግ በነበረው የሳርስ-ኮቭ ወረርሽኝ ወቅት እንደየው በርካታ እንስሳት በሳርስ ቫይረስ ተይዘው ነበር። ነገር ግን አልታመሙም፤ ውሻ ወይንም ድመት ይታመማሉ ወደ ሰውም ያስተላልፋሉ የሚል ማስረጃ የለም"

ታዲያ ቫይረሱ ከሰው ወደ እንስሳ እንዴት ይተላለፋል? ድመቶች ሰዎች ሲያስሉ፣ ሲያስነጥሱ ወይንም ሲተነፍሱ ከአፍንጫ ለሚወጡ ፈሳሾችና ለመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ ሳይሆኑ አይቀሩም ተብሎ ይታመናል።

በቤልጂየም አንድ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ማሳየት ከጀመረ ከሳምንት በኋላ ድመቱ መያዟ ተረጋግጧል። በቻይና በተደረገ ጥናት ደግሞ አንድ ድመት ለሌላ ድመት ቫይረሱን ያስተላልፋል።

" በላብራቶሪ የተደረገ ሙከራ እንደሚያሳየው ከሆነ ድመቶች በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ" ይላሉ በዩናይትድ ኪንግግደም ፒርብራይት ኢንስቲትዮት ዳይሬክተር የሆኑትና ተላላፊ በሽታዎች ላይ ነው የሚመራመሩት ፕሮፌሰር ብሪያን ቻርልስተን።

ፕሮፌሰሩ በቅርብ በኮሮና ተይዞ የነበረውን ነብር በመጥቀስ "ከድመት ወደ ድመት ተላላፊ መሆኑም ማስረጃ አለን" ብለዋል።

አክለውም የሰው ልጅ ለጦጣ የመተንፈሻ አካል ሕመም እንደሚያስተላልፍ ማስረጃ አለ ብለዋል። ይህም ከምድራችን ላይ በመጥፋት ላይ ላሉ እንደ ጎሬላ ያሉ የዱር እንስሳት ስጋት መሆኑን አልሸሸጉም።

እስካሁን ባለው ምርምርና በተገኘው ማስረጃ የሰው ልጅ ብቻ ነው ወደ ሌሎች እንስሳት ቫይረሱን የሚያሰራጨው።

ይህ ወረርሽኝ ሲጀምር ቫይረሱ ከእንስሳ ወደ ሰው መተላለፉን እናውቃለን የሚሉት ዶ/ር አልሜንድሮስ ደግሞ ነገር ግን ይህ የሚሆነው እንስሳውን በሚመገቡ ሰዎች አማካኝነት ነው ብለዋል።

ስለዚህም የቤት እንስሳት ወደ ባለቤቶቻቸው ቫይረሱን ስለማስተላለፋቸው ምንም ማስረጃ የለም ሲሉ ያረጋግጣሉ።

"የቤት እንስሳዎቻችሁን ከቤታችሁ እንዳለ እንደ አንዱ አድርጋችሁ ተንከባከቡ፤ ስለዚህ ከታመማችሁ ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አይኑራችሁ" ዶ/ር አልሜንድሮስ።

ኮሮና