ለጉብኝት ክፍት የተደረገው የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት በፎቶ

የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት ዛሬ ለጉብኝት ክፍት ተደርጓል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2011 ዓ. ም. እሥር ቤቱ ለሕዝብ እይታ ክፍት እንደሚሆን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል።

ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጸምበት ነበር የሚባለው ማዕከላዊ እሥር ቤት፤ ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ. ም. የሚከበረውን የፍትህ ቀን ምክንያት በማድረግ ለሕዝብ እይታ ክፍት መደረጉንም የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እሥር ቤቱን ጎብኝተዋል።

በቦታው የሚገኘው ባልደረባችን ካነሳቸው ፎቶግራፎች ጥቂቱን እናካፍላችሁ፦