ቫያግራ የወሰዱ ኔዘርላናዳውያን እናቶች ልጆቻቸውን አጡ

ኔዘርላንድ ውስጥ እየተሰራ የነበረ ጥናት ተሳታፊ የነበሩ እርጉዝ ሴቶች ቫያግራ እንዲወስዱ ከተደረገ በኃላ የተወለዱት 11 ጨቅላዎች ህይወታቸው አልፏል።

እንክብሉ ለሴቶቹ የተሰጠው የጽንስ እድገት ለማፋጠን ነበር። መድሀኒቱ የደም ዝውውርን ስለሚያፈጥን የተረገዙትን ልጆች ሳንባ ከጥቅም ውጪ አድርጓል።

እናቶቹ የእንግዴ ልጅ እድገት መዘግየት ገጥሟቸው ነበር ወደ ሙከራዊ ህክምና ያመሩት።

የእንግዴ ልጅ እድገት መዘግየት መድሀኒት ያልተገኘለት የጽንስ ወቅት እክል ነው።

ጽንስ መወለድ ካለበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ ከማድረጉም በላይ ጨቅላዎች በቶሎ እንዲቀጩም ምክንያት ይሆናል።

በሙከራው ወቅት ምንም ስህተት እንዳልተሰራ ቢገለጽም ችግሩ እንዴት እንደተከሰተ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ነው።

ከዚህ በፊት በእንግሊዝ፣ በአውስትራሊያ እና በኒው ዚላንድ ተመሳሳይ ሙከራዎች ተድርገው ነበር። ሙከራዎቹ ጥቅምም ጉዳትም አላስከተሉም።

በ 11 የኔዘርላንድ ህክምና መስጫዎች ውስጥ ይካሄድ የነበው ጥናት እንደ ፈረናጆቹ በ 2020 ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር።

ከሴቶቹ መሀከል 93ቱ ሲልደፊል የተሰኘ የቫያግራ አይነት 90ው ደግሞ ተመሳሳይ የሙከራ መድሀኒት ወስደው ነበር።

ከተወለዱት ልጆች መሀከል 20ው የሳንባ ህመም ገጥሟቸዋል። እናቶቻቸው ሲልደፊል የተሰኘ የቫያግራ አይነት የወሰዱት 11 ጨቅላዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

ፕሮፌሰር ዛሮክ አልፌሪክ የተባሉ የእንግሊዙን የዛያግራ ምርምር የመሩ ባለሙያ ከደቹ ጥናት በኃላ የተከሰተው የጨቅላዎች ህልፈት ያልተጠበቀ መሆኑን አስደርተዋል።

በሌሎች ሀገሮች ሞት ያላስከተለው እንክብል ለምን ኔዘርላንድ ውስጥ ህይወት እንደቀጠፈ መጠናት አለበትም ብለዋል።