ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ብሩንዲ 'መጥፎ ጎረቤት' ካለቻት ሩዋንዳ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች
ቡሩንዲ ለአማፂያን የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋለች በሚል ከሩዋንዳ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘግታለች ።
ባለፈው ታህሳስ ሬድ ታባራ የተባለው የብሩንዲ አማፂ ቡድን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ድንበር አካባቢ 20 ሰዎችን ገደለዋል።
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ክሱን ውድቅ ቢያደርጉም የብሩንዲ መንግሥት ግን "መጥፎ ጎረቤት" ሲል ፈርጇቸዋል።
የቡሩንዲ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ማርቲን ኒቴሬሴ "እስኪያለውጥ ድረስ [ካጋሜ] ከእሱ ጋር ያለንን ግንኙነት አቁመናል" ብለዋል።
የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጥቃቱን ተከትሎ በታህሳስ ወር ሩዋንዳን ከሰዋል።
ቡሩንዲ የድንበር በሯን በመዝጋቷ አዝኛለሁ ሲል የሩዋንዳ መንግሥት ምላሽ ሰጥቷል።
የድንበር መዘጋቱ የቀጣናዊ ትብብር መርሆዎችን እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብን ውህደት መርህን የሚጥስ "ውሳኔ" ነው ብሏል።
ሬድ ታባራ በታህሣሥ የተፈፀመውን ጥቃት መፈጸሙን ቢያምንም የተገደሉት ዘጠኝ ወታደሮችን እና አንድ የፖሊስ መኮንን ብቻ ናቸው ብሏል።
ቡድኑ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደቡባዊ አቅጣጫ ከብሩንዲ ጋር በሚያዋስነው የኪቩ ግዛት ይንቀሳቀሳል።
የድንበር መዘጋቱ የመሬት እና የአየርን ድንበርን ያካተተ ስለመሆኑ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
ብሩንዲ እአአ በ2015 በፖለቲካ ውጥረት እና በኋላም በኮቪድ-19 ምክንያት ከሩዋንዳ ጋር የሚያዋስናትን ድንበሯን ዘግታለች። ከሰባት ዓመታት በኋላ ድንበሮቹ እንደገና ተከፍተዋል።
በዚያን ጊዜ በምድር መሻገር ብቻ ተፈቅዶለታል። ነገር ግን የአገሪቱ አየር መንገድ ርዋንድ ኤየር ወደ ቡሩንዲ የሚያደርገውን የንግድ በረራ አላቆመም።
ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ ተመሳሳይ ቋንቋ፣ የዘር ስብጥር እና የቅኝ ግዛት ታሪክ ቢኖራቸውም ግንኙነታቸው የሻከረ ሆኖ ዘልቋል።