ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የጥምቀት በዓል በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተከበረ
ዛሬ ጥር 11/2016 ዓ. ም. የጥምቀት በዓል በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።
የጥምቀት በዓል ከዋዜማው ጥር 10 ጀምሮ ጥር 11 የሚከበር ሲሆን ጥር 12 ደግሞ የቃና ዘገሊላ በዓል እንዲሁ በድምቀት ይከበራል።
ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ካሰባሰብናቸው ፎቶዎች መካከል ከጎንደር፣ ከአዳማ፣ ከድሬ ዳዋ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከሐረር እና ከመቀለ የተወሰዱት ይህን ይመስላሉ።