የቢቢሲ አማርኛ ዋትስአፕ ቻናል፡ የተመረጡ ዜና እና ታሪኮችን ለማግኘት እንዴት የቻናሉ አባል መሆን ይቻላል?

አሁን ሰበር ዜናዎችን፣ ትንታኔዎችን እና የተለያዩ ታሪኮችን ከቢቢሲ አማርኛ በቀጥታ በዋትስአፕ በኩል ማግኘት ይችላሉ።

ቢቢሲ አማርኛ የተመረጡ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ታሪኮችን በጽሑፍ እና በቪዲዮ እያዘጋጀ በአዲሱ የዋትስአፕ ቻናሉ በኩል ለተከታዮቹ በቀጥታ ያቀርባል።

በአውሮፓውያኑ 2023 የተጀመረው የዋትስአፕ ቻናል፣ ተጠቃሚዎች ከሚፈልጓቸው ሰዎች እና ድርጅቶች አዳዲስ መረጃዎችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። በመስከረም 2023 የተጀመረው በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኘው የቢቢሲ ዋትስአፕ ቻናል የተከታዮቹ ቁጥር ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ደርሷል።

አሁን በኢትዮጵያ እና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ አንባቢዎቻችን የተመረጡ የቢቢሲ አማርኛ ዜናዎችን እና ታሪኮችን በቀጥታ በስልካቸው ማግኘት ይችላሉ።

  • የሞባይል ስልክዎትን ወይም በበይነ መረብ ዋትስአፕ የሚጠቀሙ ከሆነ ይህንን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቢቢሲ አማርኛ ዋትስአፕ ቻናል አባል ይሁኑ።
  • በዋትስአፕ ላይ በሚገኘው "Updates" ክፍል ላይ የቢቢሲ አማርኛን የተረጋገጠ ቻናል በመፈለግ ያግኙ።
  • በተጨማሪም ይህንን ጽሑፍ በኮምፒውተር እያነበቡ ከሆነ ቀጥሎ ያለውን ኪውአር ኮድ ስካን ካደረጉ በቀጥታ ወደ ቢቢሲ አማርኛ የዋትስአፕ ቻናል ይወስድዎታል።

"Updates" የሚለውን ክፍል ለማግኘት አይፎን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ከስክሪንዎ ግርጌ በግራ በኩል፤ እንዲሁም አንድሮይድ ስልክ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ በስክሪንዎ ከላይ በኩል ይገኛል።

ከሌሎች መደበኛ "Chats" ከሚለው ክፍል በተለየ በዚህ ቦታ ላይ ከቢቢሲ አማርኛ የሚላክልዎትን ዜና እና ታሪኮችን ያገኛሉ።

ከቢቢሲ አማርኛ የሚቀርቡ ዜና እና ታሪኮች እንዳያመልጥዎ ከቻናሉ አናት ላይ ያለውን ደወል በመጫን ምልክት እንዲሰጥዎ ያድርጉ። ከፈለጉ ምልክቱ እንዳይሰማ ማስቆም ወይም ከቻናሉ አባልነት በፈለጉት ጊዜ መውጣት ይችላሉ።

በተጨማሪም ከቢቢሲ አማርኛ በሚደርስዎት ዜና እና ሌሎች ታሪኮች ላይ ኢሞጂዎችን በመጠቀም ስሜትዎን መግለጽ፤ እንዲሁም የወደዷቸውን ታሪኮች በቀላሉ ለወዳጆችዎ እና ለሌሎች ማጋራት ይችላሉ።

የቢቢሲ አማርኛ ዋትስአፕ ቻናል አባል ሲሆኑ እንደ እርስዎ ያሉ የቡድኑ አባላት ዝርዝር አድራሻዎን፣ ፎቶዎን፣ ስምዎን ወይም የስልክ ቁጥርዎን ማየት እንደማይችሉ የዋትስአፕ፣ የፌስቡክ እና የኢንስታግራም ባለቤት የሆነው ሜታ ይገልጻል።

የቢቢሲ ዋትስአፕ ቻናል እና ቡድኖች ላይ ስላለ የግላዊ መረጃዎች አጠቃቀምን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃን እዚህ ያገኛሉ።