ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በአነሰተኛ አውሮፕላን ሁሉንም አህጉራት በመዞር የመጀመርያው ለመሆን ያቀደው አሜሪካዊ በአንታርቲካ ደሴት ታሰረ
ወደ ሁሉም አህጉራት በአነስተኛ አውሮፕላን ለመብረር የሞከረ አንድ አሜሪካዊ ፓይለት በፈጠረው የበረራዎች ማዘግየት በአንታርቲክ በሚገኝ አነስተኛ ደሴት ታስሯል።
ይህንን የጉዞ ሂደት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበይነ መረብ ሲከታተሉት ነበር።
በደሴቷ የቺሊያን አስተዳደር የ19 ዓመቱ ኢታሃን ጉዋ ሐሰተኛ የበረራ ዕቅድ አቅርቧል በሚል በቁጥጥር ስር መዋሉን በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ ዘግቧል።
የቺሊያን የሲቪል ኤሮኒስቲክስ ዋና ዳይሬክተር ወጣቱ ከዕቅድ ውጪ መጓዙ የአየር ማስጠንቀቂያ ሥርዓቱ እንዲበራ ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል።
ጉዎ በርካታ ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች እና ሠራተኞች በሚገኙበት ኪንግ ጆርጅ ደሴት ሲደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል። ይህ የሐምሌ ወር በደሴቱ እጅግ ቀዝቃዛ የሚባለው ሲሆን ከፍተኛ በረዶ የሚከሰትበትም ነው።
የጉዎ አነስተኛ አውሮፕላን ከቺሊያን የመጨረሻው ደቡባዊ ነጥብ (መነሻ) አቅራቢያ ከሚገኘው ፑንታ አሪና በመነሳት ወደ ወደ ኪንግ ጆሪጂያ ደሴት ባሕር ዳርቻ በሯል። ይህ ሥፍራ በእንግሊዙ ንጉስ ጆርጂያ ሦስተኛ ስም የተሰየመ ሲሆን በቺሊያን ደሴት የይገባኛል ጥያቄ ይቀርብበታል።
ጉዎ ባቀረበው የበረራ ዕቅድ መሠረት ከፑንታ አሬና አይሻገርም ነበር። ከዚህ በተቀራኒ በመጓዙ ቴኒናት አየር ማረፊያ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ወጣቱ ፓይለት የአገሪቱን ሁለት የአየር ክልል ሕጎች በመጣስ የተከሰሰ ሲሆን አንደኛው ክስ ለአጭር ጊዜ በእስር እንዲቆይ የሚያደርገው ነው።
የቺሊያን የሲቪል ኤሮኒስቲክስ ዋና ዳይሬክተር በጽሑፍ በሰጡት መግለጫ ጉዎ ከአገሪቱ ሕግ በተጨማሪ የአትላንቲክ ሰምምነትን ሳይጥስ እንዳልቀረ ገልጸዋል። ይህ ስምምነት ሰዎች እና ማንኛውም ነፍስ ያለው ነገር የማይኖርበትን ቦታ ከማክበር ጋር የሚያያዝ ነው።
ወጣቱ በኤክስ ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ "አለሁ! በቅርቡ ያለውን ነገር አሳውቃችኋለሁ" ብሏል።
ኢትሃን ጉዎ በአነስተኛው አውሮፕላን 6 አህጉራትን በመዞር ከ140 በላይ ቀናትን እንዳሳለፈ በማኅበራዊ ገጾቹ ያመለክታሉ።
ፓይለቱ ሴስና በተሰኘው አውሮፕላን ብቻውን 7 አህጉራትን የዞረ የመጀመሪያው ሰው የመሆን ተስፋ ሰንቋል። በዚህ ጉዞ አማካኝነት ለሴትን ጁድ የሕጻናት ሕክምና ምርምር ሆስፒታል ለካንሰር ጥናት 1 ሚሊዮን ዶላር ለማሰባሰብም አቅዷል።